ወያኔ ነሃሴ 26 የጠራው የድጋፍ ሰልፍ ወደ ሰላማዊ ተቃውሞ እንዳይለውጥ ስጋት ፈጥሮበታል::
አንቺው ታመጭው - አንቺው ታሮጪው...
ወያኔ ነሃሴ 26 የጠራው የድጋፍ ሰልፍ ወደ ሰላማዊ ተቃውሞ እንዳይለውጥ ስጋት ፈጥሮበታል::

የሰማያዊ ፓርቲን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የወያኔ ጁንታ ለእሁድ ነሃሴ 26 የጠራው የድጋፍ ሰልፍ ወደ ሰላማዊ ተቃውሞ ቢለወጥስ በማለት ስጋት እና ጥርጣሬ ውስጥ መግባቱን የኢሕኣዴግ ጽ/ቤት አከባቢ የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል:: ለጽ/ቤቱ ከበላይ አመራሮች በወረደው የፐርቲ መመሪያ መሰረት በጥንቃቄ እንዲቀሰቅሱ እና አስፈላጊውንም አበል ከተቃውሞዎች ጋር ግንኙነት ለሌላቸው ሰዎች እንዲሰጡ እንዲደረግ የተነገር ሲሆን .. የሚተራጠሩትን እና የሚሰጉትን ሰው የአከባቢው ካድሬዎች ወደ ሰልፉ እንዳይጠሩ ታዘዋል::

ዋናው ወያኔን ያሰጋው ጉዳይ የሙስሊሙ የሃይማኖት ነጻነት እና የኑሮ ዉድነት ጥያቄዎች የህዝቡን አቅጣጫ ያስቀይሳሉ የሚል ከፍተኛ ጥርጣሬ አሳድሮበታል::እንዲሁም በቂ የቅስቀሳ ስራ አለመሰራቱ የህዝቡ ንቃተ ህሊና ለሰማያዊ ፓርቲ የተጠሩ ሰልፈኞች እንዳይቀላቀሉ መስጋት በህዝቡ ዘንድ ወያኔ ያለው ተቀባይነት መውረዱ የኑሮ ውድነቱ የውሃ የመብራት እና የሌሎች አገልግሎቶች መዳከም የመንግስት ሰራተኛው ስብሰባ ግምገማ ፍዳዎች የእስረኞች መበራከት.....ህዝቡ የተገኘውን አጋጣሚ ተጠቅሞ ድጋፉን ወደ ተቃውሞ እንዳይቀይረው ተሰግቷል::
ስለዚህ ይህንን ስጋት እና ጥርጣሬ ተከትሎ ለቀስቃሽ ካድሬዎች መመሪያ ሲወርድ ደህንነቱ እና ፖሊሱ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ በትጋት እየተሰራ መሆኑ ሲገለጽ ይህ የቶሎ ቶሎ ሰልፍ ወያኔን ሌላ የቅርብ ርቀት አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን ተጠቁሟል::
— at Minilik Salsawi.