ወያኔ ሆይ ራስ ምታት የሆነብሽን የገንዘብ እጥረት ለዲያስፖራው ተይው::

የሰብኣዊ መብቶች ይከበሩ!!...የህዝብ ጥያቄዎች ይመለሱ!!..እንጂ


ህዝብን ያገለለ የፍትህ ስርኣት እና መሰረት የሌለው ልማት ሃገሪቷን ለእዳ የዳረጋት ሲሆን ህዝብንም በድህነት አንገቱን ሰብሮታል::ይህ ደግሞ ሊስተካከል የሚችለው በሰብኣዊ መብት እና በህዝቦች ጥያቄ ዙሪያ የፖለቲካ ቁርጠኝነት የያዘ ለውጥ ሲኖር ነው::

===ወያኔ ሆይ ራስ ምታት የሆነብሽን የገንዘብ እጥረት ለዲያስፖራው ተይው::=====

ኢሕኣዴግ -አንድነት-መድረክ-ኢዴፓ-ሰማያዊ ፓርቲ ..ምናምን የምትባሉ ምናምንቴ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገደል ግቡ :: የህዝብ ጥያቄ የነጻነት እና የፍትህ ጥያቄ ነው:: አለመታደል ሆኖ ባለፉት 22 አመታት በኢትዮጵያ ስጥ የተከሰቱ የፖለቲክ ድርጅቶች እና ሰዎች የህዝብን ጥያቄ ፈረንጆችን ለማባባል ለመለን እና ለፖለቲካ ፍጆታ አዋሉ እንጂ ምንም ያመጡት የፖለቲካ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ለውጦች የሉም::

ከፖለቲካ ፓርቲዎች ነጻ ሆነን አበቱታችንን የምናሰባ ዜጎች ጥያቄያችን አቤቱታችን :-

"የሰብኣዊ መብት ይከበር .. የህዝብ ጥያቄዎች ይመለሱ..ዜጎች በገዛ ሃገራቸው ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ እና ነጻነታቸውን ስለጠየቁ በየወህኒ የታሰሩ ይፈቱ.....የሚሉ ህዝባዊ መሰረት ያላቸውን ጥያቄዎች..."

ወያኔ መመለስ ከቻለች ለልማት እና ለገንዘብ እጥረት ፈረንጆችን ልመና በየሃገሩ እየተንከራተተች የነጭ አይን አይገርፋትም::በአሁኑ ጊዜ የሰብኣዊ መብትን በተመለከተ በውጭው አለም ያለው ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ እጅግ እንዳሳሰበው ለመግለጽ ደጋግመን እንፈልጋልን::ወያኔ ባለስልጣኖቿ በየሄዱበት አገር በኢትዮጵያውያን እየተዋረዱ ይርሚመለሱትም የዚሁ ህዝባዊ ጥያቄ ውጤት እንጂ ሌላ ጥላቻ አይደለም::

ህዝቦች አደባባይ ወተው የሚጮሁትም ይህንኑ የሰብኣዊ መብት ጥያቄ ይዘው ነው::ሁሉም ነገር በህግ አግባብ ይሁን የሚሉ ዜጎች በበረከቱባት ኢትዮጵያ ህገመንግስቱን የማያከብሩ የወያኔ ባለስልጣናት በህገመንግስት ስም እየነገዱ ነው::ህዝብን ያገለለ የፍትህ ስርኣት እና መሰረት የሌለው ልማት ሃገሪቷን ለእዳ የዳረጋት ሲሆን ህዝብንም በድህነት አንገቱን ሰብሮታል::ይህ ደግሞ ሊስተካከል የሚችለው በሰብኣዊ መብት እና በህዝቦች ጥያቄ ዙሪያ የፖለቲካ ቁርጠኝነት የያዘ ለውጥ ሲኖር ነው::

የሰብኣዊ መብት እና የህዝቦች ጥያቄ .....የፖለቲካ ለውጥ ማምጣት ከተቻለ የልማቱን እና በሀገሪቱ የተንሰራፋውን የገንዘብ እጥረት የኢኮኖሚ ድህነት ለዲያስፖራው መተው ነው:: ህዝባዊ ጥያቄዎች የሚመለሱ ከሆነ ሰብኣዊ መብቶች የሚከበሩ ከሆነ በፖለቲካ ስርኣቱ በሚደረጉ ጫናዎች በየወህኒ ቤቱ የታጎሩ ዜጎች የሚፈቱ ከሆነ .... ዲያስፖራው በአንድ ወር ጊዜ ከአንድ ትሪሊዮን ዶላሮች በላይ ለልማት እና ለሃገር እድገት ሰብስቦ በተግባር ላይ ያውላል ::ይህም የወያኔን የፈረንጆቹን ደጅ መጽናት እና በየሃገሩ የባለስልጣናትን ውርደት ያስቆማል::

ስለዚህ እንደግመዋለን ቅድሚያ ለሰባዊ መብት እና ለህዝቦች ጥያቄ መልስ መስጠት የማያፈገፍጉት ጉዳይ ስለሆነ ወያኔ ይህንን ማድረግ ከቻለች ኢትዮጵያዊ ለሃገሩ የማይሰራበት ሃገር ከልመና የማትወጣበት ምንም ምክንያት የለም::የወያኔ ራስ ምታትም ይፈወሳል::...ቀሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ደሞ የወያኔ ችግር ፈጣሪነት እና የፖለቲካ አጭበርባሪነትን ለማቆም በሚደረገው ትግል ውስጥ ምንም አይነት አስታውጾ አይታይባችሁም ይልቅ የህዝብን ጥያቄ በተለጣፊነት ለፖለቲካ ፍጆት እየተጠቀማችሁ ገዢው ፓርቲ በህዝብ ጀርባ ላይ ጅራፉን እያሳረፈ ስቃይ እያበረታ ስለሆነ በሰለጠነ ፖለቲካ ህዝብ መሃል ግቡ::

ስንደመድምም እንደግመዋለን ለሰብኣዊ መብቶች እና ለህዝብ ጥያቄዎች ቅድሚያ ይሰጥ::
ስንደመድም እንደግመዋለን ልማት የስልጣን ማስረዘሚያ ሳይሆን የህዝብ እድገት መለኪያ ነው::
ስንደመድም እንደግመዋለን ይህች አሸባሪነት የሚሏት የዜጎች ማፈኛ መሳሪያ ፈጥና ትወገድ!!!

ሁሉ ሙሉ ከሆነ .... ልማቱን ለኛ ተዉት