የናረው የኮንዶሚኒየም ግብር-የመኖሪያ ቤት ኪራይ እና የወያኔ ሚና

የሚሰበሰበው ግብር የት ነው የሚገባው??

የናረው የኮንዶሚኒየም ግብር-የመኖሪያ ቤት ኪራይ እና የወያኔ ሚና

የወያኔ ጁንት የሃገሪቷን አንጡረ ሃብት በማሟጠጥ የህዝብን ካዝና ባዶ አድርጎ በልማት ስም ከፍተኛ የሆን ብድሮችን ከተለያዩ አለም አቀፍ አበዳሪዎች በመውሰድን ሃገሪቷ ለማትወጣው እዳ የዳረጋት ሲሆን የድንጋይ ቁልሎችን እያየን ሳያልፍልን እየተራብን የአበዳሪዎችን ገንዘብ ከነወለዱ ስንከፍል ስንት አመት ልንዘልቀው እንደሆነ አጠያያቂ ሆኗል::ያለንን በግብር እና በልማት ስም እየተበዘበዝን በትዕግስት በምንኖርበት አገር የወያኔ ጁንታ የቤት ኪራይን በማረጋጋት የኑሮ ውድነቱ አንድ አካል የሆነውን የቤት ችግር ለመቅረፍ መጣር ሲገባው፣ በዜጎች መካከል ያለመተማመንና መልካም ያልሆነ ግንኙነት በመፍጠር ከአንድ ስግብግብ ደላላ ያልተናነሰ ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡

የአንድ አገር ልማት የሚወሰነው አብዛኛውን አንድ መንግስት ከዜጎቹ ከሚያገኘው ግብር እና ሃገሪቷ ካላት የገቢ ቀረጦች እንዲሁም ከተለያዩ ምንጮች ከሚገኙ ገቢዎች ሆኖ የአገሪቷን አቅም በፈቀደ መልኩ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብድር ሊወሰድ ስምምነት ሊደረግ ይገባል:: አንድ የልማት ስራ ሳያልቅ አንዱን በላይ በላይ የስልጣን ጥማትን በግንባታዎች ስም የህዝብን ቀልብ ለመግዛት የሚደረግ ሩጫ በተራራቆተ ህዝብ ላይ የማይሳካ ሲሆን በልማት ስም ባልተጠና ሂደት መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ እየተደረገ መሆኑ ሌላው የህይወት እንቅፋት ነው::የወያኔ መንግስት የሚለፈልፈው ነገር ቢኖር የልማት ሃሳዊ ፕሮፓጋንዳዎች ባልተጠና እና በቶሎ ቶሎ ግንባታ ለነገው ትውልድ የብድር እዳን እና ሙያዊ የምህንድስና ግዴታ ያላሟሉ ፍርስራሽ ግንባታዎችን ከማስቀመጥ ውጭ ምንም የሚፈይደው ነገር የለም::

የወያኔው መንግስት የሚሰበስባቸው ባለ ብዙ ዘርፎች ግብሮች ከተላያዩ አቅጣጫዎች እየጨመሩ ሲሆን የግብሩን አይነት በማባዛት አዳዲስ ስልቶችን በመንደፍ ሃገሪቷን እና ደሃ ህዝቧን የማይመጥኑ የሌሎች ሃገራትን የግብር ህጎች እየኮረጀ እየተገበረ ይገኛል::እነዚህ በየፈርጁ የሚሰበሰቡ ግብሮች ወዴት ሄደው ነው መንግስት ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት ገጠመው እየተባልን ያለነው?? መንግስት የገጠመው የገንዘብ እጥረት የባለስልታናቱ የሙስና ውጤት መሆኑ እሙን ነው::

በሃገሪቱ በተለይ በከተሞች አከባቢ ያለውን የመኦሪአ ቤት እጥረት ተከትሎ በመንግስት ባለስልጣናት እየተሰራ ያለው ከፍተኛ ደባ በግብር ስም ሀገሪቷን ለማይቀረፍ አደገና ችግርም እየዳረጋት ነው:: ከዚህ አንዱ መንግስት በራሱ ስም ከፈጠራቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ኮሚቴዎች ጋር በጋራ ተቀናጅቶ የሚሰበስበው ግብር ደስ ባለው ሁኔታ የግብር ተመን በማውጣት ከፍተኛ ነጠቃ እያደረገ ነው::የአከራዮችን እና አቅመ ቢስ ተከራዮችን ባላገናዘበ መልኩ ከኪራዩ በላይ ግብር በመጠየቅ መንግስት በየመንደሩ እየዞረ እንደ ተራ ደላላ የቤት ኪራዮችን ዋጋ ግምቶች እየሰለለ እያጠና መገኘቱ ትዝብት ላይ ጥሎታል:: በዚህም አቅመ ደካማዎችን፣ በብዙ አቅጣጫ ተቆራርጦ ጥቂት ብር እጃቸው ላይ የሚገባ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ ሴቶችን፣ የልጆች አሳዳጊ ቤተሰቦችን፣ በግለሰብ የቤት ኪራይ የተማረሩና በየጓሮ ከመኖር የወጡትን ዜጎች ሕልውና በሚፈታተን ሁኔታ፣ ለአከራዮች ይህንን ብቻ እንዴት ታስከፍላላችሁ አስተካክሉ በማለት ህልውናችንን እየተፈታተነ ይገኛል፡፡

እንደ ዜጋ በየወሩ ከ13 እስከ 35 በመቶ የገቢ ግብር እየከፈሉና በየጊዜው ከሚለዋወጠው የኑሮ ውድነት ጋር እየታገሉ በየሰበቡ በሚቆረጠው ደሞዛቸው ሳይማረሩ፣ ለተባሉት ተባባሪ የሆኑ የግልም ሆነ የመንግሥት ሠራተኞች ቤት ሳይሰጣቸው፣ አንድም አስተዋጽኦ ሳያደርጉ የቤት ባለቤት የሆኑ ግለሰቦች እንዳሉ የታወቀ ነው፡፡ እንግዲህ ምንም ዓይነት የግብር ሆነ የሌላ ህዝባዊ አካል ሳይሆኑ የቤት ባለቤት ለሆኑ ሰዎች የተረፈንን እየሰጠን በትዕግስት በምንኖርበት አገር፣ እንዴት ይህንን ብቻ ይከፍላሉ በማለት በጎ ሐሳብ ያላቸውን አከራዮችን ወሽመጥ ይቆርጣል? ይህ የሚጠበቅ አይደለም፡፡ የወያኔ ጁንታ የቤት ኪራይን በማረጋጋት የኑሮ ውድነቱ አንድ አካል የሆነውን የቤት ችግር ለመቅረፍ መጣር ሲገባው፣ በዜጎች መካከል ያለመተማመንና መልካም ያልሆነ ግንኙነት በመፍጠር ከአንድ ስግብግብ ደላላ ያልተናነሰ ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡
— at Minilik Salsawi.