በትግራይ ሕዝቡ እየታሰረ እና እየተገደለ መሆኑ ተጋለጠ፤


የሕወሀት ካድሬዎች መለስ ከሞተ በሁዋላ ለመጀመሪያ ግዜ በየወረዳው እየተዘዋወሩ የሕዝቡን ስሜ ለማጤን ባደረጉት
ሙከራ እንደተረዱት ከሆነ ህወሀት ደክሞ እራሱን መምራት ያልቻለ በመሆኑ ክልሉ ለከፋ 
አስተዳደራዊ በደሎች እየተዳረገ ነው ሲሉ ሕዝቡ መናገሩ ታውቆዋል፡፡
ዛሬ በትግራይ ክልል የወረዳና የቀበሌ አመራሮች የሚቆጣጠራቸው ጠፍቶ በህዝቡ ላይ እንደልባቸው
ከመጨፈራቸውም ባሻገር ያለ አንዳች ጥፋት ከደርግ ግዜ በባሰ ሁኔታ ሕዝቡን ያስራሉ .....ያሰቃያሉ....ይገድላሉ
ሲሉ የክልሉ ነዋሪዎች በምሬት ሲናገሩ እንደነበር ከስፍራው የደረሰን ጥቆማ ገልጾዋል፡፡
ለፖለቲካ መጠቀሚያ ሲሉ የሀውዜን ከተማን በደርግ የጦር አውሮፕላን ሲያስደበድቡና ሕዝቡን
ሲያስጨርሱ የነበረ ቢሆንም ዛሬም ያች ከተማ እንደወደመች እና አንዳችም የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴ
ያልተደረገባት ከመሆኑም በተጨማሪ ሕዝቡ የልማት ጥያቄ በማንሳቱ ሴት ወንድ.... ወጣት ሽማግሌ ሳይሉ እያሰሩ
እየገደሉዋቸው እንደሆነና ከደርግ ጅምላ ጭፍጨፋ ያልተናነሰ በደል እየተፈጸመባቸው መሆኑን ነዋሪዎቹ እየገለጹ
ይገኛሉ፡፡
የመለስን ራዕይ እናስፈጽማለን እያሉ እየዳከሩ የሚገኙትን የወያኔን የወረዳና የቀበሌ መሪዎች የትግራይ
ሕዝብ በቁጣ አሳፍሮ የመለሳቸው ሲሆን በተለይ የሽሬ እና የሁመራ አውራጃ ነዋሪዎች መለስ በሕይወት እያለም
አንዳችም የረባ መሰረተ ልማቶች እንዲከናወኑ ሳያደርግ አሁን ከሞተ በሁዋላ በሙት መንፈስ ራዕዩን
እናስፈጽማለን ማለታችሁ አስገራሚ ብቻ ሳይሆን ከሞተው ግለሰብ ጋር ሀሳባችሁ አብሮ የተቀበረ በመሆኑ በእኛ
ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም ብሎ አሳፍሮ እንደመለሳቸው ከስፍራው የደረሰን ጥቆማ ገልጾዋል፡፡
ወትሮም ሀገራዊ አጀንዳ ያልነበረው.....የሀገሪቱን ሕዝቦች ለአገዛዙ እንዲመቸው በጎጥ እና በመንደር
እየከፋፈለ ሲያምሰን እንዳልነበር...የትግራይን ሕዝብ ከተቀረው የሀገሪቱ ሕዝቦች ለያይቶ ዳግም እንዳ
ንገናኝ
እንዳላደረገ ዛሬ በመለስ ራዕይ የተጀመሩትን እናስፈጽማለን መባሉ የማይሆንና የማይዋጥልን ነው ሲሉም
መናገራቸውን ከስፍራው የደረሰን ጥቆማ አስረድቶዋል፡፡
የትግራይ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ እንዳይገናኝ እና ጨርሶ እንዲለያይ ያላሰለሰ ጥረት
ስታደርጉ ነበር ያለው ሕዝቡ ለሰራችሁት ስህተት እና ጥፋት በይፋ ይቅርታ ካልጠየቃችሁ አሁንም ሆነ ወደፊት
ከናንተ ጋር አብረን አንጉዋዝም በማለት ሕዝቡ ለ‹ድሬዎቹ አስደንጋጭ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ታውቆዋል፡፡
በሕዝቡ ሀሳብ ተስማምተው የተመለሱ የወረዳ ካድሬዎች በቀጥታ ለክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት የህዝቡን
ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም ሕዝቡን ያሳመጻችሁ እናንተ ናችሁ በሚል ከስልጣናቸው መባረራቸውን ከስፍራው
የደረሰን ጥቆማ አብራርቶዋል፡፡
መቀሌ የሚገኘው በአባይ ወልዱ የሚመራው አንዱ የወያኔ ክንፍ ካድሬዎቹን ወደ ተ
ለያዩ ወረዳዎች እናቀበሌዎች ልኮ የህዝቡን የልብ ትርታ አድምጠው እንዲመለሱ የላካቸው 
 ቢሆንም ይዘው በመጡት መልስበመደናገጥ ከአዲስ አበባው ቡድን ጋር ወግናችሁዋል በሚል
ከስልጣናቸው ያባረታቸው መሆኑን ከመቀሌ የደረሰንጥቆማ አስረድቶዋል፡፡
ከፍተኞቹ የህወሀት ባለስልጣናት እርስ በርስ መተማመን ተስኖዋቸው አንዱ አንዱን በጥርጣሬ እያየ
ባለበት በዚህ ግዜም ባለፈው ሳምንት በመቀሌ በተደረገው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሎች ስብሰባ ላይ
ንትርክ እና ጭቅጭቅ የነበረ ሲሆን በቅርቡም የተለያዩ  ሹም ሽሮች ይደረጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የመቀሌው በአባይ ወልዱ የሚመራው ቡድን የትግራይ ክልል መንግስታዊ መዋቅሩን
ተጠቅሞ የአዲስ አበባውን ቡድን ከህዝቡ ለማራቅ ሙከራ እያደረገ ሲሆን በአንጻሩ በደብረጽዮን የሚመራው
ይመራል እየተባለ የሚነገርለት የአዲስ አበባው ቡድን ደግሞ በሙስና ሰበብ እያሰረና ከስልጣናቸው እያነሳ
በመገኘቱ በህወሀት ውስጥ የተፈጠረው ሽኩቻ እየሰፋና እየገዘፈ መምጣቱ እየተነገረ ይገኛል፡፡
በቅርቡም በመቀሌ ከተማ በተደረገው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የእነ አባይ ወልዱ ቡድን በእነ
ደብረጽዮን ላይ የበላይነቱን ለመያዝ ሲል አዲስ አደረጀጃጀት እና አዳዲስ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሎችን ለማምጣት
በስውር ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሚገኝምተጠቁሞዋል፡፡
የእነ ደብረጽዮን ቡድን ደግሞ ለሀገር ሳይሆን ለስልጣን ....ለሕዝብ ሳይሆን ለግለሰቦች በማሰብ እና
ያኛውን ለማዳከም የሙስና ምንጠራ እያደረጉ ሲሆን የህወሀት ቁልፍ ሰው ከተባለለት የገቢዎች እና ጉምሩክ
ባለስልጣኑ ገብረዋህድ ቀጥሎ የደህንነት ምክትል ኃላፊ የሆነውን ግለሰብ ጭምር ዘብጥያ በማውረዳቸው ትንቅንቁ
እንደቀጠለ፤ አመላ‹ች ሆኖዋል፡፡
መለስ በሕይወት እያለ የሚስቱን ገመና ለመሸፈን ሲል በሙስና እስከ አንገታቸው ድረስ የተዘፈቁ
ቁጥራቸው የበዙ የወያኔ ባለስልጣኖች መኖራቸውን እያወቀ ስልጣኔን ካልተጋፉ ምን ቸገረኝ በሚል ስሜት የነበረ
ቢሆንም እሱ ከሞተ በሁዋላና አሁን በህወሀት መሀከል በተፈጠረ ትርምስ ምክንያት በተጀመረው የሙስና
ምንጣሮ ከፍተኛ ፈላጭ ቆራጭ የሆኑ ግለሰቦች ዘብጥያ የወረዱ ሲሆን ከነዚህ ግለሰቦች ጋር በሽርክና ስትሰራ
የነበረችውና በቢሊዮንየሚቆጠር የሀገር ሀብት ያሸሸችው አዜብ መስፍን ጉዳይም ለግዜው በሚል በእንጥልጥል
የቆየ ይሁን እንጂ የደብረጽዮን ቡድን ከተጠናከረ ሴትዮዋም ዘብጥያ መውረድዋ አይቀሬ እንደሆነ በስፋት
እየተነገረ ይገኛል፡፡ለዚህም ማሳያ ከኤፈርት ዋና ስራ አስኪያጅነት ተነስታ ከሌሎችም ወሳኝ ቦታዎች ተገድባ የመለስ
ፋውንዴሽን ላይ ብቻ ተመድባ እንድትሰራ መደረጉ ወደፊት የነደብረጽዮን አቁዋም እየጠነከረ ከመጣ
ያለማወላወል ከጉዋደኞችዋ ጋር እስር ቤት ልትቀላቀል ትችላለች ተብሎዋል፡