ወያኔ ቀይ መስመር ላይ ነው:: አስረአንደኛው ሰአት አልፎአል!! 11:55 ..ህዝቡ አድፍጧል!!

"እያለማን ነው ስንል ከፊታችን እጅግ ትልቅ አደጋ ተጋርጦብናል::" አቶ ጌታቸው አሰፋ
ወያኔ ቀይ መስመር ላይ ነው::
አስረአንደኛው ሰአት አልፎአል!! 11:55 ..ህዝቡ አድፍጧል!!
Minilik Salsawi Blog
ወያኔ ሊቆጣጠረው የማይችል ከባድ የህዝብ ማእበል እንደሚገጥመው የደህንነት ሰዎች ያቀረቡት ሪፖርት ማመልከቱን ተከትሎ በዶክተር ደብረጺሆን እና በአቶ ጌታቸው የሚመራ ከባድ ስብሰባ በአዲስ አበባ ካሳንችስ ኢሲኤ ጀርባ ከሚገኝ አንድ የደህንነት ቢሮ ውስጥ ተቀምጠው እንደነበር ተጠቁሟል::

መጭው ጊዜ ያሰጋው ሕወሓት መራሹ መንግስት ወደ ትግራይ አፋር እና ሶማሌ ክልል በከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣኖቹ የሚመራ ምስጢራዊ ቡድኖችን መላኩ ታውቋል::እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በደቡብ ክልል ያሉ የደህንነት መዋቅሮቹ በተጠንቀቅ እንዲሰሩ የታዘዙ ሲሆን በምእራብ በኩል ላሉ የደህንነት መምሪያዎቹ ግን እስካሁን ያወውረደው መመሪያ የለም::

የፈንጂ ወረዳ ውስጥ በራሱ ሰው ሳይጠራው የገባው ወያኔ ህዝቡ ያምጻል የሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የገባበትን ሪፖርት እየመረመረ ሲሆን የህዝቡ የፍትህ እጦት እና የኑሮ ውድነት የሚያስከትለው ችግር ምን አይነት መፍትሄ ሊሰጠው ይችላል መፍትሄ የምንለው ነገር እኛን ይጎዳናል ስለዚህ የሃይል እርምጃዎች መጠቀም እንዲሁም ካድሬዎች ላይ ያለን እምነት ጥርጣሬ ላይ ስላለ አስፈላጊ ክትትሎችን በማድረግ በጥቅም ካድሬዎችን ማኮላሸት የሚሉ እና የተቃዋሚ ሃይሎች ውስጥ ያሉ ሰርጎ ገቦችን ማጠናከር በድንበር ከተሞች በቤተክርስቲያኖች በመስኪዶች እና በወታደራዊ ተቋማት ውስጥ አስፈላጊውን ሁሉ ፋይናንስ በማፍሰስ የመረጃ ሰዎቻችንን በማስረግ ሊከሰት የሚችለውን ችግር ማስወገድ አለብን ሲሉ ተሰምቷል::