ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳንኞች እየተሸጠ ነው::

ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳንኞች እየተሸጠ ነው::
ባለፉት 2 ወራት ብቻ የ16 ሰወች አስከሬን በተለያየ አካባቢ ወድቆ ተገኘ::
Minilik Salsawi Blog
ከደቡብ ጎንደር ; ከምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ; ከሴሜን ወሎ ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚመጡ ወገኖቻችን ባሰሪወቻቸው አና ባካባቢው በዚህ ሥራ በተሰማሩ ( የትግራይ ተወላጆች ) ግፍ እየተሰራባቸው ነው ::

ባለፉት 2 ወራት ብቻ የ16 ሰወች አስከሬን በተለያየ አካባቢ ወድቆ የተገኘ ሲሆን ጎዳዩን ቀለል በማድረግ እና እውነቱን ሰው እንዳይገነዘብ ሲባል የተለያዩ መላምቶች በመንግስት ሆን ተብሎ ተሰጦታል ::ለምሳሌ በአንድ ሳምንት ዉስጥ በተደጋጋሚ የተፈፀመውን እሄን ድርጊት በቀጥታ በብሔሮች መካከል በተነሳ ግጭህት ( የወሎ እና የጎጃም በሚል ) እርስ በርስ በጩቤ እየተዋጉ ነው በማለት ጉዳዩን አድበስብሶት የቀረ ሲሆን ሌሎች ገለልተኛ ሚዲአወችም እሄንኑ በማስተጋባት እውነቱ ተደብቆ ወንጀሉ ግን ቀጥሏል ::

በሁመራ ከተማ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ የህገወጥ መሳሪያ ዝውውር በስፋት የሚፈፀም ሲሆን በዚህ ሥራ የተሰማሩት ሁሉም የትግራይ ተወላጆች ከሱዳኖች ለሚቀበሉት መሳሪያ ክፍያ እንዲሆን የሚሰጠው የገበሬወችን ኩላሊት ነው ::
እንዲህ አይነት ሥራ በሱዳን በኩል ወደ እስራኤለ በህገወጥ መልኩ የሚጉዓዙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለ እንደሆነና አልፎ አልፎም በሱዳን በገድሃሪት እና አጎራባች አካባቢወች ድረስ በመምጣት ካምፕ ዉስጥ በመግባት ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች አፍኖ በመያዝ ብዙ እሺ ዶላር በማስከፈል ይለቁአቸዋል መክፈል ያልቻሉትን ግን ኩላልታቸውን በማውጣት ለእልፈተሞት ይዳረጋሉ ::
ለወገኖቻችን እንድረስላቸው !!
የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ 
ሰሜን ጎንደር