የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም::ሃገሪቱ ካለፈው የባሰ አደጋ ተጋርጦባታል:: MUST READ !!!

"አገሪቱ በልማት ጎዳና ላይ እየነጎደች ...." ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ በትእዛዝ የካዱት
"የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም::ሃገሪቱ ካለፈው የባሰ አደጋ ተጋርጦባታል::" ሪፖርተር ርእስ አንቀጽ 
የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የሕወሓት ሪፖርተር መግለጫ ግጭት #1 ምንሊክ ሳልሳዊ

ኖሚናል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የተባሉት እና በህገመንግስት የተሰጣቸውን ስልጣን በትእዛዝ ብቻ የሚሰሩበት ምንም አይነት አገራዊ ፋይዳ የማያደርጉት ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እና የሕወሓት ታማኝ የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ ያሰፈረው ርእስ አንቀጽ የሃገሪቷ ላይ የሰፈነው አብዮታዊ ዲሞክራሲ አምባገነንነት እያደረሰ ያለውን ችግር እና መጪውን አደጋ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃገሪቱ ምንም አይነት ችግር እንዳሌለ እና ሁሉም ነገር በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዳለ በዲሞክራሲ እና በልማት እየነጎድን ህዝባዊ ድሎችን እየተጎናጸፍን ..ምናምን...የሚሉ እና ሃሰትን የተሞሉ የማደናገሪያ እና የማስፈራሪያ ቃላት ፍርሃት በሚነበብበት ፊታቸው እያስገመገሙ ደስኩረዋል:: የእርሳቸው ንግግር እንደተጠበቀ የሕወሓት ሪፖርተር ጋዜጣ ደሞ እንዲህ ብሎናል::የኢሕኣዴግ ባለስልጣናት ፕሮፓጋንዳ እና የሚከተለውን የሪፖርተር ወቀሳ ይመዝኑት::ሪፖርተር እንደውስጥ አዋቂነቱ ያየውን እና የታዘበውን ሃይለማርያም ደሳለኝ ግን በትእዛዝ የካዱት እኛ ደሞ ያነበብነውን የተከፋፈልነው የታዘብነውን እንደራሳችን እይታ እንደሚከተው በዝርዝር ለማየት እንፈቅዳለን::

ሰብሰብ፣ ጠንከርና ነቃ ያለ የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሌለ እና እንደሚያስፈልግ በግልጽ አስቀምቷል:: የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በሞት ሲለዩና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሰየሙ ምንም ችግርና ብጥብጥ እንዳልነበር ይህ ማለት መሪ አልተተካም ሳይሆን ሰብሰብ፣ ጠንከርና ነቃ ያለ መንግሥትና አመራር ስላሌለ አገራችን ያያስፈልጋል እያልን ዓለም የኢኮኖሚ ቀውስ እኛንም እየጐዳን ነው፡፡ ትላልቅና በርካታ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ሲደረጉ በደመነፍስ ባጀት ተመድቦ ከፍተኛ ፋይናንስ ሳይኖር ወደ ላማት ይገባል ፡፡ ከዚህ በፊት ያልነበረ የሃይማኖት ግጭትና ልዩነት እየታየ ነው፡፡ ችግሩ ካልተፈታ አስጊ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ዕድገት የማይሹና የማይመኙ ጠላቶች በእጅጉ እየተፈታተኑን ናቸው፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ጠንካራ መንግሥትና ጠንካራ አመራር የግድ ይላል፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ተንካራ መንግስት እና አመራር እንደሌለ በግልጽ ሪፖርተር አስቀምጧል::

ገዥው ፓርቲ እርስ በኤርሱ እየተዋከበ እና እየተፈረካከሰ በውስጡ መተማመት እንደጠፋ በገሃድ መካሪ መስሎ የመሰከረው ሪፖርተር ኢሕኣዴግ ውስጣዊ አንድነቱን ማጠናከር አለበት፡ሲል በአደረጃጀቱ ምክንያት አራት አባል ድርጅቶች ቢኖሩትም ሲሠራና ሲንቀሳቀስ እንደ አንድ መሆን አለበት፡፡ኢሓዴግ አራት ድርጅቶችን አክፎ በተለያዩ አሰራሮች በመጠመድ እርስ በራሱ እየተዋጋ እና እየተሸበር መሆኑን ሪፖርተር ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል::ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን የጠላት ወሬ ሲሉ ክደዋል::በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከልመራራቅ እና መፈረካከስ እየታየ ነው የሚለው ይሄው ዘገባ እንኳን እየተራራቁ አንድ ተሁኖም ለመፍታት የሚያስቸግሩና የሚፈታተኑ ችግሮች እያጋጠሙ ናቸው፡፡ሲል ጠላቶችና አንዳንድ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ተጣሉና ተሰነጣጠቁ እንደሚባለው ሳይሆን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ተገቢና የሚጠበቅ አንድነት፣ መቀራረብ፣ የዓላማ ፅናትና ለመስዋዕትነት ዝግጁነት እየታየ አይደለም፡፡በማለት መክሯል ሆኖም ያለው ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር በሚሉ ቃላቶች ተክቶ አቅርቦታል::


የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የሕወሓት ጋዜጣ ሪፖርተር ግጭት === #2 ምንሊክ ሳልሳዊ
 
-ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን የሚያሳብቁ ተተኪ ቃላቶች ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር
-ሙሰኞችን ማደን - ‘እንትና ይደናገጣል እከሌ ያኮርፋል’ ተብሎ የሚቆምና የሚቀዘቅዝ ትግል
-የትም ሥፍራ፣ የትም መሥሪያ ቤት በማንኛውም ጊዜ መልካም አስተዳደር እየተጣሰ፣ ፍትሕ እየጠፋ፣ የሕዝብ ጩኸትና ጥሪ ተቀባይ አልባ ሆኗል፡፡

ገዥው ፓርቲ እርስ በእርሱ እየተዋከበ እና እየተፈረካከሰ በውስጡ መተማመት እንደጠፋ በገሃድ መካሪ መስሎ የመሰከረው ሪፖርተር ኢሕኣዴግ ውስጣዊ አንድነቱን ማጠናከር አለበት፡ሲል በአደረጃጀቱ ምክንያት አራት አባል ድርጅቶች ቢኖሩትም ሲሠራና ሲንቀሳቀስ እንደ አንድ መሆን አለበት፡፡ኢሕኣዴግ አራት ድርጅቶችን አቅፎ በተለያዩ አሰራሮች በመጠመድ እርስ በራሱ እየተዋጋ እና እየተሸበር መሆኑን ሪፖርተር ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን የጠላት ወሬ ሲሉ ክደዋል::በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከል መራራቅ እና መፈረካከስ እየታየ ነው የሚለው ይሄው ዘገባ እንኳን እየተራራቁ አንድ ተሁኖም ለመፍታት የሚያስቸግሩና የሚፈታተኑ ችግሮች እያጋጠሙ ናቸው፡፡ሲል ጠላቶችና አንዳንድ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ተጣሉና ተሰነጣጠቁ እንደሚባለው ሳይሆን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ተገቢና የሚጠበቅ አንድነት፣ መቀራረብ፣ የዓላማ ፅናትና ለመስዋዕትነት ዝግጁነት እየታየ አይደለም፡፡በማለት መክሯል ሆኖም ያለው ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን በሚያሳብቁ ተተኪ ቃላቶች ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር በሚሉ ተክቶ አቅርቦታል::

ሙስናው በስፋት ተንሰራፍቷል ያልው የሪፖርተር ጋዜጣ "አገር በሙስና እየተጨማለቀች ናት" ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተናገሩት በተቃራኒ ጎኑ መጭውን አደገኛ የሃገር ኢኮኖሚ የዳግም ስርኣተቀብር ሙስናው እያሳየን መሆኑን ጠቁሟል:: ሙስናን ለመዋጋት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የውስጥ የፖለቲካ ባላንጣዎችን ለማፈን እና ለማስወገድ የእጅ አዙር መጥረቢያነት ከማገልገል ውጭ ምንም አይነት እርምጃ በሙሰኞች ላይ ሲወሰድ አልታየም ይባስ ሙስና በሃገሪቱ እየተስፋፋ እና እያበበ ነው::‘እንትና ይደናገጣል እከሌ ያኮርፋል’ ተብሎ የሚቆምና የሚቀዘቅዝ ትግል እንደሆነ ይጠቁማል::ሙስና ኢትዮጵያን እያጨማለቀ ሲሆን ከስርቆትና ከዝርፊያ በፊት ሙስናን የሚያስቆሙና የሚያጋልጡ አሠራሮች፣ ሕጐች፣ መዋቅሮችና የሥነ ምግባር ደንቦች እንዳይወጡ የመንግስት ባለስልጣናት እንቅፋት ሁነዋል::የመንግስት ባለስልጣናት በራሳቸው ለሙስና የሚያመች ሁኔታ እየፈጠሩ ሙስናን እንዋጋለን ማለት አያስኬድም፡፡ ከአሿሿም ጀምሮ፣ ከቁጥጥር ጀምሮ፣ ከቅጥር ጀምሮ አሠራሩ ሁሉ ሙስናን የሚያስወግድ ሳይሆን የፖለቲካ ታማኝነትን የጠበቀ ነው፡፡

አገሪቷ በሙስና መጨማለቋ የመልካም አስተዳደር እጦት ፈጥሯል:: ጠቅላያችን እንዳሉን ማንጫውንም ነገር መልካም አስተዳደርን ጨምሮ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መኖራቸው እና በሂደት እየተሻሻሉ እንደሚሄዱ ነግረውናል ይህ ነገር ላለፉት 22 አመታት ሲነገረን የነበረ እና ምንም አይነት ለውጥ ከማየት ይልቅ በካድሬዎች ብልሹ አሰራር እና ቢሮክራሲ የመልካም አስተዳደሩ እየተበላሸ ገደል መግባቱን ብቻ ነው::የመልካም አስተዳደር እጦት ሕዝቡን ተስፋ እያስቆረጠ ነው ብሎናል ለገዢው ፓርቲ ቅርብ የሆነው ሪፖርተር- አዎን ገዥው ፓርቲ መልካም አስተዳደር አለመኖሩን እያመነ ነው፡፡ ዕርምጃም እወስዳለሁ ቢባልም ለስልጣኑ ማራዘሚያ የሚጠቀምባቸው በጥቅም የተተበተቡ ካድሬዎቹ ይገለበጡብኛል በሚል ፍራቻ ምንም አይነት ርምጃ ሳይወስድ የመልካም አስተዳደር እጦቱ እንደቀጠለ ነው ፡፡

መልካም አስተዳደር ይኑር ይስፋፋም የሚሉ የመንግስት ሚዲያዎችም ይሁኑ ፕሮፓጋንዲስቶች ቃላቶችን ህዝብን ለማጭበርበር እየተጠቀሙበት ነው ፡፡ በቃላት ላይ ችግር የለም፡፡ በተግባር ግን መልካም አስተዳደር እውን ሊሆን አልቻለም፡፡ የትም ሥፍራ፣ የትም መሥሪያ ቤት በማንኛውም ጊዜ መልካም አስተዳደር እየተጣሰ፣ ፍትሕ እየጠፋ፣ የሕዝብ ጩኸትና ጥሪ ተቀባይ አልባ ሆኗል፡፡ ሕገ መንግሥቱና የተለያዩ ሕጎች ተግባር ላይ የሚያውላቸው አጥተዋል፡፡ የሙስና ተጠርጣሪዎች ታሰሩ ቢባልም ፈጥረውታል የተባለው በደል ግን ሲስተካከል አይታይም፡፡ ይህ ችግር በእጅጉ አደገኛ ነው፡፡ ዜጋ አገሩን እንዲጠላና ተስፋ እንዲቆርጥ እያደረገ ያለ ችግር ነው፡፡ #3 ምንሊክ ሳልሳዊ 
በአንድ አገር ላይ ሁለት አገር የለም ሃይለማርያም ደሳለኝ ስለ የትኛው አገር መግለጫ እንደሰጡን አሁንም አልገባንም::ሪፖርተር ጋዜጣ ደሞ የታዘብኩት ያየሁት የሰማሁት በሚል አበይት ብሎ ያለውን የሃገርቱን እውነታዎች በከፊት አስቀምጧል:: በርግጥ የተሸፋፈነ ቢሆንም ፍንጭ ግን አገሪቷ አደጋ ላይ እንዳለች ጋዜጣው መስክሯል:: እኛም ያየነውን የምናውቀውን ጤቅላይ ሚኒስትሩን እና ጋዜጣውን ይዘን ተንትነናል ::

የሃይለማርያም ደሳለኝ መግለጫ እና የሪፖርተር ጋዜጣ ግጭት
- የመንግስት የጥንቃቄ ጉድለት እና የፖለቲካ አጀንዳ ሃይማኖቶችን እየበረዘ ነው:;
- የኢኮኖምው ድቀት አገሪቷን ወደማትወጣበት አደጋ ውስጥ የከተተ ሲሆን ከፍተኛ ስራ አጥነት ፈጥሯል::
- በወያኔ መንግስት የመወያየት የመነጋገር የመቀራረብ መንገዶች ስለተዘጉ ችግሮች እየበረከቱ ነው::

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የድርጅታቸው የበላይ አካሎች በሰጧቸው ኦረንቴሽን መሰረት አጥንተው ገብተው በሃገሪቱ የተከሰቱ የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄዎችን እና መሰረታዊ የዲሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎችን በተለመደው አሸባሪ አክራሪ እና ጽንፈኛ በሚሉ ወያኔያዊ ቃላት ተጠቅመው ሲያስፈራሩ ... ይህን መሰል የመንግስት ማስፈራሪያ በህዝቦች መብት ላይ መስጠት በሃገሪቱ ያሉ ሃይማኖቶች ነጻነታቸውን መጋፋት ሲሆን ዋናው የችግሩ ፈጣሪ ወያኔ የፈጠረው የስልጣን ማስረዘሚያ የወንጀል ቃላቶች መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል :: ሃይማኖቶች በመርሃቸውም ይሁን በተግባራቸው አይጋጩም፡፡ ሁሉም ፍቅርን፣ መተሳሰብንና ሰላምን የሚሰብኩ ናቸው፡፡ ችግሩ ያለው እምነት ላይ አይደለም፡፡ ችግሩ ያለው የዚህ ሃይማኖት ጠበቃና አለኝታ እኔ ብቻ ነኝ፣ አንተ ወይም ያኛው አይደለም በሚል ሃይማኖትን ተገን በማድረግ በሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ስለዚህ የችግሩ መንሴ የሆነው ወያኔ የሃይማኖቶ ጠበቃ በመምሰል በህገመንግስት ንግድ ውስጥ ተጀቡኖ እጁን ወደ ሃይማኖቶች በማስገባት ራሱን የሃይማኖት አለኝታ በማስመሰል ሃይማኖቶችን ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋሉ የህዝብ ጥያቄዎች በአደባባይ መሰማት ከጀመሩ አመታት ተቆጥረዋል::
የክርስትና፣ የእስልምናና የአይሁድ እምነቶች በጋራ በሚኖሩበት አገር ውስጥ፣ ጋብቻ ፈጽመውና ተፋቅረው መኖር የሚችሉ የተለያዩ የሃይማኖት እምነት ተከታዮች ያሉበት አገር አለን እያልን፣ የወያኔ መንግስት በፈጠረው የፕሮፓጋንዳ እና የከፋፍለህ ግዛ ድርጊት ተጋጨ፣ ጠንካራ የነበረን ሕዝብ ተፋጀ ወደሚል አሳፋሪ ታሪክ እየቀየርነው ነው፡፡ ወያኔ ለስልጣን ማስረዘሚያ ብሎ የተጤቀመበት ስልት ነገ ለቁጭት የሚዳርገን እና ወደማንወጣበት ውድቀት የሚከተን ሲሆን ታሪካችንን፣ ማንነታችንና ደኅንነታችንን ለአደጋ እያጋለጠ ነው::

የሃገሪቷ ኢኮኖሚ በወያኔ ባለስልታናት እና በብሄራዊ ጥቅም በታወሩ ምእራባውያን እንደሚወራል ሳዮን እጅግ በጣም እየተንኮታኮተ መሆኑ እሙን ነው::በመንግስት ካዝና ውስጥ ከባድ የሆነ የገንዘብ ችግር አለ:: የመንግስት ካዝና ባዶ ነው ቢባል የሚያስኬድበት ደረጃ ላይ ተኩኖ የሃገሪቷን በጀት ማጽደቅ እንደት እንደሚቻል ግራ እየገባን ነው:: በጀት ሲጸድቅ እንጂ ሲለቀቅ የማይታይባት ኢትዮጵያ አስደንጋጭ የኢኮኖሚ ውጥንቅጥ ውስጥ እየዳከረች ነው:: የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ብቻ ከጥቂት ነጋዴዎች እና ብሄርተኞች ጋር በሙስና ተጨማልቀው የሚሰሩት የአየር በአየር ንግድ የሃገሪቷ ኢኮኖሚ አይደለም የመንደር ኢኮኖሚ ሊባይ አይችልም::ክፍያ አፈጻጸም ላይ እንኳን ግለሰብ መንግሥትም እየተቸገረ ነው፡፡ የግል ባንኮች እየተዳከሙ ናቸው፡፡ የብድርና የውጭ ምንዛሪ ችግርና እጥረት አለ፡፡ ግሽበትን ለመቆጣጠር የሚወሰደው ዕርምጃ የራሱን ችግር እየስከተለ ነው፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ፣ የውኃ መጥፋት፣ የኔትወርክ አለመኖር፣ በሁሉም ዘርፍ ችግር እያስከተለ ነው፡፡ ገንዘብ ማሸሽና መደበቅ እየታየ ነው፡፡ ሌባው ሲፈራ ባይገርምም፣ ንፁኃን ሲሸማቀቁና ብታሰርስ እያሉ በመፍራት ከቢዝነስ እንቅስቃሴ ሲቆጠቡ እየታየ ነው፡ ይህንን ወያንኤ አምኖ ሊቀበለው አይደለም ጭራሽ በጠላይ ሚኒስትር ደረጃ መካድ ተጀምሯል:: ከሕዝብ ብዛትና ከሚመረቁ ተማሪዎች አንፃር በቂ የሥራ ዕድል አልተፈጠረም፡፡ ሥራ ለማግኘት ወደ ዓረብ አገሮች የሚደረገው ስደት በአስፈሪ ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ ወደ ወንጀል እየተገባ ነው፡፡ ለባለ ገንዘብ ራስን ለሽያጭ ማቅረብ እየተስተዋለ ነው፡፡ ይህ ችግር ካልተፈታ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ያሰጋል፡፡ ልዩ ትኩረትና መፍትሔ ይደረግበት፡፡ የተራበ ሆድ አደገኛ ነውና፡፡

በወያኔ መንግስት የመወያየት የመነጋገር የመቀራረብ መንገዶች ስለተዘጉ ችግሮች እየበረከቱ ነው:: በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉ ችግሮች ኢትዮጵያዊያን ሊፈቱዋቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ በመንግሥትና በሕዝብ፣ በመንግሥትና በተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ፣ በመንግሥትና በሲቪል ማኅበረሰቡ፣ በመንግሥትና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች መካከል መቀራረብ፣ መወያየትና መመካከር ስለሌለ በቀላሉ የሚፈቱ ችግሮች እየተባባሱ ናቸው፡፡ ችግሮችን ለመንግሥት ማቅረብ አልተቻለም፡፡ መንግሥትም የሕዝብን ችግርና ስሜት ማወቅ አልቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት ቀላል ችግሮች እየተካበዱና ወደማያስፈልግ አቅጣጫ እየተሸጋገሩ ናቸው፡፡ መንግሥት በአስቸኳይ ቲንክ ታንክ ያቅድ፣ የጋራ መድረክ ይፍጠር፣ የሕዝብና የመንግሥት፣ የመንግሥትና የባለሙያዎችን ግንኙነት ያጠናክር፡፡ መጠራጠርንና መራራቅን ወደ መቀራረብና መተማመን ይቀይር፡፡ አድዮስ ዲሞክራሲ!!!