የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ነጻነት በህግ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው::

 

ኮሚቴዎቻችን አሸባሪ እና አክራሪ ሳይሆኑ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተገሩ የሃይማኖት ምሁራን ናቸው::ምንሊክ ሳልሳዊ:- የወንድሞቻችን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በገዛ አገራቸው አፈራቸው እና በነጻነታቸው ላይ የተቃጣ አደገኛ መንግስታዊ ሴራ ካለተግባራቸው ተወንጅለው የህሊና እስረኛ ከሆኑ ጀምረው ድምጻችንን እያሰማን እንገኛለን ;;አሁንም እስከመጨረሻው ድረስ ነጻነታቸው ተረጋግጦ ጥያቄቸው እንዲመለስላቸው አጥበቀን በመጠየቅ በኢህኣዴግ መራሹ መንግስት ላይ ሕዝባዊ ጫናዎቻችንን ከመፍጠር ወደኋላ የምንልበት እና የምናፈገፍግበት አንዳችን ምክንያት ስለሌለ የሙስሊሙ ወገናችን መብት በይፋ የሃይማኖት ነጻነት በአደባባይ በተግባር እንዲውል አጥብቀን እንጠይቃለን::

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ለመንግስት ያቀረቡት ጥያቄ ግልጽ እና የማይገሰስ የመሰረታዊ ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጥያቄ መሆኑ እየታወቀ እና በመንግስታዊ ስርኣቱ እውቅና ከተሰጠው በኋላ የፖለቲካ ዝማሬውን በሃይማኖት ውስጥ አጥልቆ ማስገባት የሚፈልገው የአብዮታዊው ዲሞክራሲው ባላባት ኢሕኣዴግ ባልታሰበ እና ባልተጠበቅ ሁኔታ ንፁሃኑን በአሸባሪነት ፈርጆ በእስር በማንገላታት ትክክለኛውን ህጋዊ ፍርድ እንዳያገኙ በማድረግ ፖለቲካዊ ውሳነ ለመስጠት አሰፍስፏል::

የኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቻችን ትግል የፖለቲካ ጥያቄ ያለው በማስመሰል የተለያዩ ፕሮፓጋንዳዎችን በመንዛት ተግባር የተሰማራው ስርኣት የኮሚቴዎቻችንን በግፍ ማሰሩን ተከትሉ ሙስሊሙን ህብረተብ በማፈስ በመግደል በማሰር በማንገላታት በመዝረፍ እና ተመሳሳይ ችግሮችን አስከፊ በመፈጸም በህዝቦች ላይ ከአንድ መንግስት ነኝ ከሚል አስተዳደር የማይጠበቅ ሽብር በመፈጸም ላይ ይገኛል::በህገወጥ መንገድ ያስቀመጣቸውን ታማኝነታቸው ለፓርቲ ተጠሪነታቸው ለአሸባሪ ባለስልጣናት የሆኑ ዳኞችን በመጠቀም በኮሚቴዎቻችን ላይ የፖለቲካ ውሳኔ ለመስጠት ታህሳስ 3 2006 አውሬያዊ አፉን ከፍቶ ንጹሃንን ለመዋጥ ተዘጋጅቶ ይገኛል::

ታህሳስ 3 2006 በንጹሃን ላይ ሊሰጥ የታሰበው የፖለቲካ ፍርድ ዘር ቀለም ሃይማኖት ሳይለይ በ80 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሊደረግ የታቀደውን ፖለቲካዊ ጣልቃገብነት ያለበትን ፍርደገምድልነት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በይፋ ይቃወመዋል::
ኮሚቴዎቻችን እያንዳንዳቸው በኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተገሩ እና ምንም አይነት የሽብር ተግባር ያልፈጸሙ መሆናቸውን ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን አለም ያረጋገጠው ጉዳይ ስለሆነ እንዲሁም እነሱን ተከትሎ በየእስር ቤቱ የታጎሩ ወገኖቻችን ሙስሊሞች ሁሉ በነጻ እንዲለቀቁ እና ሃገሪቱ አላት በተባለው ህገመንግስት መሰረት ነጻነታቸው እንዲከበርላቸው አጥብቀን እናሳስባለን::በሀገሪቱ እስርቤቶች የታሰሩ ሙስሊም ወንድሞቻችን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቀ በህግ መስመር መሰረት ደግመን አጥብቀን እንጠይቃለን:;ምንሊክ ሳልሳዊ
ድል ለመላው ኢትዮጵያውያን!!!