መፍትሄ ያጣው ህዝብን ተስፋ ያስቆረጠው የፍትህ አካላቱ ፖለቲካዊ ንቅዘትምንሊክ ሳልሳዊ - ላለፉት ሃያ አመታት በሃገሪቱ የተንሰራፋው የእሓዴግ መራሹ መንግስት የፍትህ ስራቱ እንዲቀበር እና በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዲሞት በማድረግ ህዝቦች በፍትህ አካላት ላይያላቸው እምነት ተስፋ እንዲያጣ አድርጓል::የፍትህ አካላት ለሃገሪቱ ዜጎች ማገልገል ሲገባቸው ለጥቂት ባለስልጣናት እና ለጥቅማ ጥቅም በመገዛት ህጎች እንዲፋለሱ በማድረግ ላይ ይገኛሉ :;ሊሻሻል እና ሊለወጥ በማይችልበት ደረጃ ላይ የደረሰው ይህ የፍትህ አካላቱ ንቅዘት አለኝታነቱን እና ታማኝነቱን በማጉደል ከፍተኛውን ወንጀል በመፈጸም ላይ ይገኛል::

በጥቅም የነቀዙት የፍትህ አካላቱ በሙስና ላይ እርምጃ እንዲወስዱ መቀመጣቸውን ዘንግተው በፓርቲ ካድሬነት ብቻ የሰለጠኑ እና ታማኝነታቸው ለአንድ አካል እና ተጠሪነታቸውም ለገዢው በመሆኑ ህዝብ ትክክለኛ ፍትህ እንዳያገኝ በማድረግ ላይ ሲገኙ ይህንንም ላላቸው የፓርቲ ቀረቤታ በማናለብኝነት በሙስና ተዘፍቀው ፍትህ በማጓደል ህገመንግስቱን እና ተከታይ ህጎችን እያጣመሙ በመተርጎም የዜጎች መንፈስ እንዲበላች እና በፍትህ ሂደት ላይ እምነት እንዳይጣል እያደረጉ ይገኛል:: የፖለቲካ ታማኝነታቸውን መከታ በማድረግ ከፍትህ ማጓደል በተጨማሪ በጉቦ ቅሌት ላይ ተሰማርተው የሙስና ሰለባ የሆኑት የፍትህ አካላቱ በሚያገኙት ጥቅማጥቅም መዝገቦችን በመዝጋት እና ሰነዶችን በማጥፋት በተዘዋዋሪ ፍትህ ፈላጊዎችን በህገወጥ መንገድ በሃይል በማስደንገጥ በአጭሩ ሊፈቱ የሚችሉ እና ውስኔ የሚገባቸውን ጉዳዮች ቀጠሮ በማስረዘም እና የፍርድ ውሳኔዎችን በማዛባት ፍትህ ከቁጥጥር ውጪ ወቶ ህገወጥነት እንዲስፋፋ አድርገዋል::

በዳኝነት ወንበር ላይ መቀመጥ የፖለቲካ ደላልነት የሚመስላቸው የእሕኣዴግ ካድረዎች ካለምንም በቂ የህግ እውቀት በፖለቲካ ፓርቲ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ፕሮግራም ተገርተው የገረፍ ገረፍ ህግን ሰልጥነው በህግ ባለመብሰል ካለ አቅማቸው ወንበሩን ስለያዙት ከፍተኛ የፍትህ መበላቸት በመስፋፋቱ ህዝቦች ላይ ከፍተኛ የስነ ልቦና ችግር እያደረሱ ነው:: እነዚህ በህግ እውቀት የአቅም ማነስ የተጠለፉ የፖለቲካ አገልጋዮች ተቆጣጣሪ አካል ሳይሆን ፍርድ እንዲያዛቡ ያስቀመጣቸው አካል የስልታን እድሜው እንዲረዝም ምንም አይነት እርምጃ ባለመውሰዱ ዜጎችን እያስለቀሱ ይገኛሉ::

ለፍትህ አረም የሆኑት የኢሕኣዴግ ባለስልጣናት እጅግ በወረደ መልኩ ከአንድ ህዝብ አስተዳድራለሁ ከሚል አካል በማይጠበቅ አካሄድ በፍትህ ስርኣቱ ላይ ጣልቃ በመግባት ሕግ አውጪው፣ ሕግ አስፈጻሚውና ሕግ ተርጓሚው ነፃ ሆነው እንዳይንቀሳቀሱ እንዳይሰሩ በየፍርድ ቤቱ ዳኞች ላይ በስልክ እና በተለያዩ ዘደዎች ትእዛዝ በማስተላለፍ አደገኛ ሽብር እየፈጸሙ ይገኛሉ::የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትን እና ጫና በመሸሽ ሽብር ስጋት እና ፍርሃት ስለተፈጠረባቸው ቁጥራቸው ብዙ የሆነ እና በቂ የህግ እውቀት ያላቸው ዳኞች ተሰደዋል-ከስራ ተባረዋል-በገዛፍቃዳቸው ስራ ለቀዋል-ታስረዋል..::ይህ ማስፈራራት እና ሽብር በፍትህ አካላት ላይ የሚፈጠረው በባለስልታናት ብቻ ሳይሆን ባለስልጣናቱን መከታ ባደረጉ ሰዎችም ጭምር ነው::ባለስልጣናቱ በየፍርድ ቤቱ ዳኛ አድርገው የመደቧቸውን ካድሬዎቻቸውን በማዘዝ በህሊና እና በፖለቲካ እስረኞች ላይ ካለምንም ማስረጃ እንዲፈረድ የወዳጅ ዘመዶቻቸው መዝገብ እንዲዘጋ ሰነድ እንዲበላሽ እንዲቃጠል በማድረግ ጫና እየፈጠሩ የፍትህ ስርኣቱ እንዲነቅዝ አድርገውታል::