የብኣዴን እና የኦሕዴድ ባለስልጣናት ቅርርብ ለሕወሓት አልተመቸውም::# "...አደጋ ውስጥ ነን::" የሕወሓት የደሕንነት መሪዎች የኦህዴድ ውስጥ ውስጡን መደራጀት ሕወሓትን አሳስቦታል::ምንሊክ ሳልሳዊ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ የሆኑ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት መቀራረብ እና አብሮ መዋል የሕወሓት ሰዎችን ማሳሰቡን እና የደህንነት ክትትል እያደረጉባቸው መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል:: ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደመቀ መኮንን እና ከሙክታር ከድር ጀምሮ እስከ በታች የፌዴራል ባለስልጣኖች ላይ ከፍተኛ ስለላ እየተካሄደ መሆኑን ታውቋል::

ሃገሪቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሳለች ከፊታችን አደጋ ተደቅኗል::የሚሉ የተቆጡ ድምጾች በስፋት በእሕኣዴግ አባላት እየተሰሙ ያለበት አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው ሕወሓት በግል እና በጋራ ባለስልጣናቱ ላይ ከፍተኛ ማስፈራራት እና ዛቻ እያደረገባቸው መሆኑን የተናገሩት ምንጮቹ ኢሓዴግን ለመናድ ብትሞክሩ ሃገሪቷ ትበታተናለች ;እንደ ሱማሊያ መንግስት አልባ ሆና ትበጠበጣለች እያሉ ከማስፈራራትም አልፎ በግል የተነከራችሁበት ሙስና አደባባይ እናወጣዋለን:: እኛን ማንም ሊተይቀን አይችልም ቁልፉ እኛ ጋር ነው የሚሉ በኣደገኛ መርዞች የተሞሉ ማስፈራሪያዎች በመሰንዘር ላይ ናቸው ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል::

የብኣዴን እና የኦሕዴድ ባለስልጣናት የየቀን ሪፖርት እና ግንኙነት በተመለከተ ማን ከማን ጋር እንደዋለ ማን እነማን ቤት እንደሄደ በመከታተል እየቀረበ ሲሆን የሃገሪቱን የደህንነት ቢሮ በጋራ የሚመሩት አቶ ጸጋዬ አቶ ጌታቸው እና ዶ/ር ደብረጺሆን በየቀቱ ለትግሪኛ ተናጋሪ ደህንነቶች በአጫጭር ስብሰባዎች መመሪያ እያወረዱ ከመሆኦኑም በላይ አደጋ ውስጥ መሆናቸውን እየደጋገሙ እንደሚናገሩ ምንጮቹ አክለዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ ቀደም በእሕዴድ ወጣቶች የተጀመረው እና የሌንጮ ለታ ወደ አገር ቤት የሚለውን ዜማ ተከትሎ የለውጥ ጥያቄ እያንሰራራ መሆኑ ታውቋል:: በዚህም ምክንያት የኢሕኣዴግ አጋር ድርጅት የሆነው ኦሕዴድ ወጣት አባላት እና ለውጥ ፈላጊዎች ራሳቸውን ውስጥ ውስጡን እያደራጁ ነው በሚል ሕወሓት የድርጅቱን መዋቅር ሊበርዘው መሆኑ ተሰምቷል:: በተለያዩ ፖለቲከኞች ዘንድ ኦሕዴዶች ድምጻቸውን አጥፍተዋል እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት ሕወሓት አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ነው ሲል ይነጋገርበት ጀምሯል::

በወጣቶቹ የኦሕዴድ አባላት መሃከል በተፈጠሩ መግባባቶች እስከመቼ ድረስ የፖለቲካ አሽከር ሆነን እንቀጥላለን የሚሉ የድርጅቱ ካድሬዎች በዙሪያቸው እየተቧደኑ ሲሆን ይህ ያሰጋው ሕወሓት የእነዚህ ሰዎች ዝምታ ይህን ሰሞን በአመራሮቹ ደረጃ በቢሮ ስብሰባ እየተነጋገረበት ይገኛል::

ጥርሳቸውን ነክሰው አድፍጠው ያሉት የኦሕዴድ አባላት በስልጣን ክፍፍሉ እና ራሳችንን መምራት ያለብን ራሳችን ነን በሚል እንዲሁም በተያያዥ የፖለቲካ ጉዳዮች በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ያሉት የህዝብ ሃብቶች ላይ የሕወሓት ባለስልጣናት የሚሰጡት ውሳኔ እንደፖለቲካ ባርነት ነው የሚሉ ሮሮዎች በመደመጥ ላይ ሲሆኑ ነጻነታችንን መረጋገጥ አለብን የሚሉ ቢሊሶማ2 የተሰኙ ወጣት ባለስልጣናት ሕወሓትን አጣብቂኝ ውስጥ ከተውታል::ምንሊክ ሳልሳዊ