ታሪክ ይቅር የማይለው ከባድ መንግስታዊ ወንጀል !!!

በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ የደረሰው ግርፍት እና መከራ ቁስሉ የኔም ነው።ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች (እደግመዋለው) የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ህገመንግስቱን ተመርኩዘው የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄዎችን በመያዝ ወኪሎቻቸውን በመምረጥ ህጋዊ ውክልን በመስጠት ወደ ገዢው መንግስታዊ ቡድን ህግን አንብበው ለይተው አውቀው መብታቸውን እና ግዴታቸውን ተረድተው አቤቱታቸውን ለማሰማት በሄዱበት የወይኔው ስርአት እንኳን ደህና መጣችሁ በሚል የህሰት ወንበዴያዊ ፈገግታ በአስመሳይ ሰላም እና ፍቅር አቅርቦ እውቅና የሰጠ በማስመሰል ደም በተለወሱ ጥርሶቹ ነክሶ ለመያዝ እና ለአገዛዙ በሚያመቸው መንገድ ሃይማኖታዊ የፖለቲካ አደረጃጀት በመፍጠር ለዘመናት የቆየውን የሃይማኖት ቀኖና ትላንትና እንደ አይሁድ ባሉ መርዘኛ መንግስታት በተፈጠሩ ዘመን አመጣሽ እምነቶች ለመተካት እና የኢትዮጵያውያንን የሰላም እና የፍቅር ተምሳሌት የሆነውን እስልምናን ለማደፍረስ ደፋ ቀና በማለት ትላንት እውቅና ለሰጣቸው የሙስሊም ምሁራን ወገኖቻችን የአሸባሪነት ታርጋ በመለጠፍ በጠፍ ጨረቃ መኖሪያቸውን በመስበር በከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት ወደ እስር ቤት አግዞ ካለምንም ማስረጃ እና ካለበቂ ሰነድ አግቶ በማንገላታት ላይ ነው።

የወያኔ ስርአት ራሳቸውን አክብረው እና ሃይማኖታቸውን ጠብቀው ከፖለቲካ እድፍ ነጻ ነን ያሉ ምሁራንን እንደ ተቃዋሚ .... ሕገመንግስታዊ ጥያቄ ያቀረቡ ዜጎችን እንደ አሸባሪ .... በነጻነት ማምለክ መጸለይ እንፈልጋለን ያሉ ትን እንደ አክራሪ ... ወዘተ በመፈርጅ ከፍተኛ የሆነ ሰቆቃ እና ስቃይ እያደርሰባቸው መሆኑ በዚህ ሰሞን ከወንድሞቻችን ከሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች እየቀረበ ያለው የመከላከያ የፍርድ ቤት ቃላቸውን ሰምተናል ። እጅግ አስደንጋጭ እና አሳዛኝ የሰው ልጆች በገዛ አገራቸው ዜጋ አይደለንም እንዲሉ በፍርሃት ተሸብበው እንዲኖሩ ለማድረግ የተቀናጁ አሰቃቂ ወንጀሎች በኢትዮጵያውያኑ ሙስሊም ምሁራኖች ላይ ተፈጽሟል። ታሪክ ይቅር የማይለው ከባድ መንግስታዊ ወንጀል ማንንም ከተጠያቂነት እንደማይመልስ ትውልድ በተግባር ያሳያል።

ማእከላዊ ተብሎ በሚጠራው የአዲስ አበባው ጓንታናሞ ውስጥ ከቀድሞ ስርአቶች ጀምሮ ከባድ የሆኑ ወንጀሎች በኢትዮጵያውያን ላይ ቢፈጸምም የዚኛውን ግን ለየት የሚያደርገው በሃሰት ውንጀላ አሸባሪ አክራሪ ተብለው ያለስማቸው ስም ወቶላቸው ከየቤታቸው በጨለማ እየተጎተቱ ባልሰሩት ወንጀል እና ባላዋሉበት ጉዳይ ስቃይ የደረሰባቸው ሙስሊም ወገኖቻችን ጉዳይ በገሃድ አደባባይ መውጣቱ የስር አቱን ጋጥወጥነት እና ለዜጎቹ ደንታቢስ መሆኑን አንድን ህዝብ እመራለሁ ከሚል መንግስት የማይጠበቅ ድርጊት እንደተፈጸመ የሃይማኖት ሙሁራኑ ካቀረቡት የመከላከያ ቃል ለማዳመጥ ችለናል። በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ሰቆቃ የማእከላዊ ቶርች እና ስቃይ እያንዳንዳችን እንዳንተኛ እና ነገ በኛ በማሰብ ለኮሚቴዎቹ ፍትህ በንቃት እንድንሰራ ብርታት ሰቶናል።

አንድ አምባገነን ስርአት ታግለን ለመጣል የግዴታ እያንዳንዱ ዜጋ እስር ቤት ገብቶ መታሰርን እና መገረፍን መመልከት ሳይሆን ወንድሞቻችን በ እስር ቤት ያሳለፉት መከራ እንደመከራችን አይተን ሲነጋ ደሞ ወደ እኛ ቤት እንደሚመጣ አስበን ለታሰሩት ሃቀኛ ፍትህን ለኛም የማይሸራርፍ መብቶቻችንን ለማግኘት መታገል ግዴታችን መሆኑን ማወቅ ያስፈልገናል።ለዘመናት ተሳስሮ እና ተከባብሮ የኖረን ህዝብ ለማፋጀት ዘመን በወለዳቸው የአይሁዶች ቋንቋ አሸባሪ አክራሪ እየተባሉ ዜጎች የሚደርስባቸው መከራ እንዲቆም እያንዳንዳችን መስእዋት መሆን አለብን። የአብሮነታችን ተምሳሌት ለአለም ያስተማረውን የአያቶቻችንን የአንድነት ፍቅር ደግመን በዚህ ትውልድም ማሳየት አለብን ። አምባገነኖች ጠንክረን ከታገልናቸው ቀዳዳው ሁሉ ስለሚጠብባቸው ተፍረክርከው ይጠፋሉ። በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ የደረሰው ግርፍት እና መከራ ቁስሉ የኔም ነው። ምንሊክ ሳልሳዊ