የምናየው ሌላ የምንሰማው ሌላ .. ተወናበድን - ተደናገርን - ግራ ገባን።የታክሲ ላይ ራዲዮ - ኑሮው መንግስት  እና አዲስ አበቤው

@ምንሊክ ሳልሳዊ
ብሶት የወለደው የወያኔው ሰራዊት ሌላ ብሶት ያርገዘ ትውልድ እየፈጠረ መሆኑን አላወቀውም ይሁን አውቆ የተኛን እንደሚሉት ብቻ ... ኢትዮጵያውይን ዳግብ ብሶት የወለደን ሊሉ አፋፍ ላይ መሆናቸውን እያየን ነው፡፤ድርሰዋል እስከመሽ እየተሸዋወዱ መኖር ይቻላል እያለ ነው ወጣቱ።

ንቃት ሕሊናችንን በውሸት ማደፍረስ አንፈልግም በዙሪያችን ያለው እና የምናየው ሌላ ነው የወያኔ መንግስት ደግሞ የሚያሰማን ሌላ ንው .. የሚነግረን ያሌለች ኢትዮጵያን ነው እኛ የምንኖራት ደግሞ ያደፈች ኢትዮጵያን ነው ሲል የለውጥ ስሜቱን ማስተጋባት የጀመረው ወጣት ብሶት የወለደኝ ብሎ አደባባይ ሊወጣ አሰፍስፏል። ጠዋት ተነስተን በምሬት በብስጭት በውሃ እጦት ውሃ ሳይነካን ከቢታችን ስንወጣ ታክሲ ውስጥ የተከፈተ ራዲዮ 97 ከመቶ የውሃ ሽፋን ተረጋግጧል ይለናል ... አለማበዳችንም  ሲያንስ ነው። ..... 

ምነው ታክሲዎች በኤሌክትሪክ እና በውሃ ሰርተው ቢሆን ኖሮ እኮ ራዲዮውንም አንሰማም ነበር ራሳቸው ያወሩትን ራሳቸው ይሰሙት ነበር ... የምናየው ሌላ የምንሰማው ሌላ መንግስት አጭበርብሪ ነው ግራ አጋባን እኮ .. ኑሮ ያጦዘን አንሶ መንግስታችን ያወናብደናል ያደናግረናል፤ ስም አታጥፉ  የሚሉን ካድሬዎች ምንም አይታያቸውም እንዳትል፡ጠዋት ሲወጣ ከሚስቱ ጋር ሲናከስ ትሰማዋለህ ኑሮ ሳያሸንፍ ለውሃ እና መብራት ጉዳይ ባልና ሚስት ካድሬዎችን ሳይቀሩ ይናከሳሉ።

ወያኔዎች በሚዲያቸው የሚነግሩን ነገር ስል ሃገራችን የማወቅ መብታችንን የሚጋፋ ብቻ ሳይሆን ጆሮ አለን የለንም ብለን ራሳችንን ወዳለማመን ደርስናል። በውኃ፣ በኤሌክትሪክ፣ በስልክና በትራንስፖርት አገልግሎቶች መቆራረጥና አለመሟላት ምክንያት ሥራውና ኑሮው አሳር እያየበት ያለው ሕዝብ የአገልግሎቱ ተደራሽነት በዚህን ያህል በመቶ አደገ ወይም ደረሰ ሲባል ቀልድ የተያዘ ይመስለዋል፡፡ ለሳምንታት ውኃ አጥቶ የሚንከራተት ሕዝብ የውኃ ተደራሽነት ከዘጠና በመቶ በላይ ሆኗል ተብሎ ሲለፈፍበት እንዴት ይቀበላል? በኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ምክንያት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ማምረት እያቃተውና ሕዝቡ በጨለማ ሲሰቃይ ተደራሽነቱ ይህን ያህል ደርሷል ሲባል ማን ያምናል? በሌሎች ዘርፎችም ተመሳሳይ ማደናገሪያዎች ሞልተዋል፡፡

ከአዲስ አበባና ከተለያዩ ክልሎች ገበያዎች የተገኙ ተብለው የሚቀርቡ የሸመታ ዋጋዎች መጣረስ የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ጤፍ፣ በርበሬ፣ ጥራጥሬና የተለያዩ የግብርና ምርቶች ዋጋ በመገናኛ ብዙኃኑ ሲተነተን፣ በፍፁም ገበያ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አያሳይም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ማደናገሪያ ማንን እንደሚጠቅም አይገባንም፡፡

ሕዝቡ በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት እየተንገላታ በየቦታው ምሬት በበዛበት በዚህ ወቅት፣ የመልካም አስተዳደር ተግዳሮቶች በመቀረፍ ላይ ናቸው ይባላል፡፡ በፋይሎች ላይ ውሳኔ መስጠት አቅቶት ወይም በቸልተኝነት አልወስንም ብሎ የሚኮፈስ ቢሮክራሲ ዜጎችን ሲያስለቅስ በአደባባይ እየታየ መፍትሔ እየተገኘ ነው የሚል ማደናገሪያ ሲቀርብ ያሳዝናል፡፡ ያሳፍራል፡፡

በፍትሕ ሥርዓቱ አካባቢም ሲታይ እየወጡ ያሉ መግለጫዎችና ሪፖርቶች የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ፍትሕ ዘገየብን፣ ፍትሕ ተነፈግን የሚሉ በርካታ ዜጎች ባሉበት አገር ውስጥ የፍትሕ ሥርዓቱ ተደራሽነት ወደር የለውም ዓይነት ሪፖርቶች ይቀርባሉ፡፡ ሕዝቡ በየፍርድ ቤቱ በተጓደለ ወይም በተነፈገ ፍትሕ ምክንያት ከላይ ታች ሲቅበዘበዝ እየታየ የማይመስል ነገር ይነገራል፡፡ በዚህ መስክ ያለው ማደናገር ራስ ያሳምማል፡፡

በአጠቃላይ በበርካታ ዘርፎች የሚወጡ ሪፖርቶች መሬት ላይ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አልዛመድ እያሉ ናቸው፡፡ በአኃዝና በመጠን ሊገለጹ የማይችሉ ጉዳዮች ዕቅዳቸው ከነአፈጻጸማቸው ተቀባብተው ሲቀርቡ ከማደናገራቸውም በላይ ወዴት እየሄድን ነው ያሰኛሉ፡፡