የሰማያዊ ፓርቲ የውጭ ጉዞ ውዝግብ

( ከእውቀቱ አበበ )
በተመሠረቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይዘዋቸው ብቅ ባሉት ህዝባዊ ጥያቄዎችና ጥያቄውን አስከትለው  በፈጠሩት ንቅናቄዎች የተነሳ በፍጥነት የህዝብን ልብ ለማንበርከክ ከቻሉ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አንደአንዱ የሚቆጠረውና የፈጠሩትን ህዝባዊነት በመጠቀም ሩቅ ሳይራመዱ እንደደከሙ ፓርቲዎች ሁሉ ስማቸውን በታሪክ ድርሳን ላይ አስፍሮ ለማክተም ጫፍ የደረሰው የሰማያዊ ፓርቲ ዕጣ ፈንታ አሳሳቢ ሆኖ መታየቱ ተስፋ የማይቆርጠውን ህዝብ መፃኢ ዕድል  የተለመደውን ጨዋታ እንዲጠብቅ እያደረገው መገኘቱ በተጨባጭ በመታየት ላይ ይገኛል።

በውስጣዊና በውጫዊ ችግሮቻቸው በመሪዎቻቸው ድርጅታዊ አምባገነንነትና የፓርቲ ወንበር ጠሜነት፣ ለሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ባላቸው ንቀት አዘል አመለካከትና ትግሉን በመተሳሰብ የአንድዮሽ አቋም ከመምራት ይልቅ እኔነታዊ መንፈስ ማዕከል ያደረገ የተሰባጠረ ጉዞን ለመራመድ ከመፈለግበሚነሱ ችግሮች የትም ለመድረስ ካልቻሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተሻለ መልኩ አደራጅቶ ወደ ውጤታማ አቅጣጫ ያደርሰናል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ሰማያዊ ፓርቲ፤ ያማረለትን አጀማመር በማጠናከር፣ ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ድክመት በመማር ራሱን ለማጠናር ሳይችል የቀረበበትን ስህተት እያጠናከረው መሆኑ የህዝብ ተስፋ የሆኑት የተቃዋ ፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች ማዞሪያቸወ ካልሆነ በቀር የሚጋግሩበት ምጣድ አንድ እንደሆነ እያሳየ ነው።

ጅማሬውም በህዝባዊ ጥያቄዎች ላየ በማድረግ ህዝባዊ ንቅናቄ ለመፍጠር የበቃው ይህ ፓርቲ ቢያንስ ረዥም ዓመታትን ካስቆጠረው የተቃውሞ ትግል አንፃር ጊዜያቸውንና ዕድሜያቸውን በዚህ መስመር ውስጥ በማድረግ ያልሰለቹ አመራሮችን መያዙና ወቅቱ የሚፈልገውን የፖለቲካ ስልታዊ ዳንኪራ ይዞ በመምጣት መፍትሔ ለማግኘት የሚንቀሳቀስ ሆኖ መታየቱ፣ ረዥም ዓመት ለውጥ ባላመጡ ፓርቲዎችና ከድርጅት ወንበራቸው ላይ ጠጋ ለማለት እንኳን ባልደፈሩ መሪዎች የተሰላቸውንና ተስፋ የቆረጠውን ህዝብ በአጭር ጊዜ ለማነቃነቅ በቅቷል። የብዙዎቻችን ተስፋም ሆነ ሰላማዊ የትግል አማራጭ ለመሆን የበቃው ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ መንፈስና በአዲስ ጉልበት ብቅ ያለ ፓርቲ የመስለበትን የፖለቲካ ስብዕና የያዘ ቢመስልም፣ ከቀን ቀን እየታዩ የመጡት የውስጥና የውጭ ችግሮች ሥር እየሰደዱና እየተባባሱ መምጣቱ አዲስ መስመር ፈልጎ ከፓርቲው ጀርባ የተሰለፈውን ለውጥ ናፋቂ ህዝብ ከወዲሁ ማስኮረፉ አልቀረም።

ገና በማለዳው በተደረገው አንድ ሰላማዊ ሰልፍ ራስን በትግሉ መስመር ረዥም ዓመት ከዘለቁ ፓርቲዎች አስበልጦ የመኮፈስ አዝማሚያን ለማሳየት የበቃው ይህ ፓርቲ፣ በተናጠል በመሪዎቹ ላይ የበለጠነው መታበይና ራስን ከታላላቅ ፓርቲ አመራሮች አስበልጦ የማየት፣ ድርጅቱን ከሌሎች ፓርቲዎች አግዝፎና መሪ አድርጎ የማስቀመጥ አባዜ በተሰባጠረ ትግሉ ተስፋ የቆርጠውን ህዝብ ከማሳዘኑም በላይ ፓርቲው በገዥው ፓርቲ ላይ መሥራት የሚገባውን የቤት ሥራ በማዳፈን ከአቻ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በሚያደርገው “የእኔ እበልጥ” ሽኩቻና እሰጥ እገባ ላይ ለመቆም መገደዱ ህዝባዊ እምነቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲኖረው በማስገደድ ላይ ይገኛል።

በዕድሜም ሆነ በተቃውሞ ትግል ልምድ እጅግ ከሚበልጡት ፓርቲዎች የጠነከረ ትምህርት በመውሰድ፤ የድካማቸውን ማዕከል ደግሞ የመማሪያ መጽሐፍ ማድረግ ይጠበቅበት የነበረው ሰማያዊ ፓርቲ ይህንን ታላቅ ዕድል ችላ በማለት የቀደሙት ፓርቲዎች በተጠመዱበት የውስጥና የውጭ ችግሮች ትብታብ
በመተብተብ የችግሩን ቀዳዳ እያሰፉ መጓዙ በተጨባጭ በሚታይበት በአሁኑ ሂደት በፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ እያናፈሰ ያለው ተስፋ አስቆራጭ መንፈስ ፓርቲው ያጣው ህዝባዊነት የተጠናከረ የአመራር ሚና ስህተት መሆኑን እያረጋገጠ ነው። አንድነትን ከመሳሰሉ ታላላቅ ፓርቲዎች ጋር የተለያዩ ውጫዊ ውዝግብ ውስጥ በመግባት “እኔ የተቃዋሚው ጎራ መምህር፣ እናንተ ደግሞ ደቀመዛሙርቴ ናችሁ” የሚል ዓይነት መታበይ ውስጥ የገባው ሰማያዊ ፓርቲ ከሰሞኑ በወርሃ ሰኔ በሰሜን አሜሪካ በሚደረገው የስፖርት ውድድር ላይ በተጋባዥነት የሚገኙ ሁል ተወካዮችን ለማሳወቅ የእርስ በርስ ሽኩቻ ላይ መሰንበቱ የፓርቲውን አመራሮች ህዝባዊነት አጠያያቂ አድርጎታል።

በሰሜን አሜሪካ ከሚገኘው የፓርቲ ድጋፍ ሰጪ አባላት በተላከ የግብዣ ጥሪ መሠረት በዚያው በሚካሄደው የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የሚገኙትን ሁለት አባላቱን ለመምረጥ በተደረገ ጥረት በአመራሮቹ መካል ሰፊ ክፍተትና ልዩነት የታየበት የሰማያዊ ፓርቲ፣ ከሥራ አስፈፃሚ መካል ብቸኛዋ ሴት ሥራ አስፈፃሚ የሆነችውን ሀና ዋለልኝንና ሌላ አንድ ተወካይ ለመምረጥ ግላዊ መጎናነጥ ድረስ የወረደ ችግር ውስጥ ለመግዛት ተገድዷል። ከድርጅቱ ዓላማና ግብ በዘለለ መልኩ ግላዊ የበላይነትን ለማጠናከር ብርቱ ጥረት በተደረገበት በዚህ ሂደት “በግሏ ለመሄድ በቂ ዝግጅት አድርጋለች፣ ፓስፖርት በማውጣትም
ቪዛ ይዛለች፣ ይህ አቋሟ እዚያው የመቅረት አዝማሚያዋን ያሳያል፣ እዚያው ከቀረች ደግሞ ትግሉን
ታኮላሸዋለች” የሚል ተቃውሞ የተሰነዘረባት ብቸኛዋ ሥራ አስፈፃሚ ከአሜሪካ ጉዞ ውጭ ተደርጋለች።

የፓርቲው ሁለንተናዊ ፈጣሪና ገዥ በመሆን በብቸኝነት አቆጥቁጠው የወጡትና የሌሎች ተቃዋሚዎችን
ገድል አንኳስሶ በመናገር የሚታወቁትን የፓርቲውን ሊቀመንበር ኢንጂነርይልል ጌትነትን የሚደግፉ አካላት
ብቸኛዋ ሴት ሥራ አስፈፃሚ ከላይበተጠቀሰው አቤቱታ ከጉዞው ውጭቢያደርጉም የፓርቲው ወቅታዊ
እውነታ እንዲሚያረጋግጠው ግን ሀቁ ከዚህ ተገላቢጦሽ መሆኑ የፓርቲውን አባላት እያነጋገረ ነው።
የፓርቲው የፋይናንስ እንቅስቃሴ በኢንጂነሩ የግል ጣቶች የሚሽከረከሩ በመሆናቸውና ይህም
ተደጋግሞ በላዕላይ ም/ቤት አባላት በኩል ቅሬታ የቀረበበት ከመሆኑ አንፃር ፓርቲው የኢንጂነሩ “ኃላፊነቱ
የተወሰነ የግል ማህበር” እስመሆን መድረሱ ላይታለም የተፈታ የፀሐይ ላይ እውነታ ሆኗል።

ያለምንም ተወዳዳሪ ኢንጂነሩ በብቸኝነት እንዲያልፉ በተደረገው ጥረትአይነተኛ ሚና የተጫወተውና ኢንጂነሩየቀኝ እጅ መሆኑ የተረጋገጠለት አቶ ወሮታው ዋሴ ቀሪውን አንድ ቦታ ለመያዝ ከአቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ጋር ቢፎካከርም “ብርሃኑ ህፃን ነው” በሚል ሽፋን እንዳይመረጥ በማድረግ የቡድን ሥራ ለመሥራት ችለዋል። በሁለቱ ሴራ ከአሜሪካ ጉዞ የቀሩትና ከጉዞው በመቅረታቸው የተነሳ “እኔ ገና ወጣት ነኝ እንደናንተ አላረጀሁም ሌላ ጊዜ ዕድል አለኝ” የሚል አቋም የያዘውን አቶ ብርሃኑን “ህጻን ነው” በሚል አቋም ከጉዞ ውጭ ያደረጉት እነ ኢንጂነር ይልቃል ከወጣት ፎረም በመውጣት ባለራዕይ የግል ድርጅት አቋቁመው የነበሩትንና በኋላም ወደ ሰማያዊና አንድነት የተቀላቀሉትን አቶ ብርሃኑንና አቶ ሃብታሙን አናምናቸውም የኢህአዴግ አባል ነበሩ፤ አሁንም ውስጣዊ አባል ናቸው” የሚል አቋም በመያዛቸው  መሆኑ ግልፅ ነው።

ከኢንጂነር ይልቃል ውጭ ሌሎቹ የሥራ አስፈፃሚ አባላት በዚያው እንደሚቀሩ መታመኑ ፓርቲው ምንያህል የግለሰቦች ብቻ እንደሆነ በተጨባጭ ማሳየቱ ገረሜታን የፈጠረባቸው አባላት ባነሱት የተቃውሞ
ድምፅ የተበሳጬት ኢንጂነሩ “ምን ትንጫጫላችሁ አሁንም በዚህ ጉዳይ መተማመን የማይኖረን ከሆነ ፓርቲው ቢፈርስ የእኔ ጉዳይ አይደለም” ሲሉ በግልጽ መናገራቸው የፓርቲውን ጥግ ፈልጎ የተሰበሰበውን ደጋፊውን ብቻ ሳይሆን፤ በቅርቡ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተገኘው ሰልፈኛ ቁጥር እጅግ አነስተኛ በመሆኑ የተነሳ እሳቸውም መደናገጣቸውንና ተስፋ መቁረጥ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን በተጨባጭ አመልክቷል።

የፓርቲውን ሥራአስፈፃሚ አባላት በተለያዩ ምክንያቶች በመጥለፍ ከአሜሪካ የመጣውን ግብዣ ማጨናገፍ
የሰማያዊ ፓርቲ የጥርስ መገርጎሪያቸው እስከማድረግ ለደረሱ አንድና ሁለት አመራሮች የስኬት ያህል ቢያስቆጥርም ብዙዎች ግን ታላላቅ የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎችና ምሁራ “ህዝብን ለመቀስቀስ”፣ “ህዝብን ለማደራት” ፣ “ዲያስፖውን ለማመስገን” በሚሉ የተለያዩ ማወናበጃዎች ወደ አሜሪካ ሄደው መቅረታቸውን ታላቅ መስታወሻሊሆን እንደሚገባ በመወትወት ሁለቱየፓርቲው አመራሮች በፓርቲው የገቢናየወጪ ሂሳብ ላይ የኦዲት ሪፖርትሳያደርግ ከዚህ ቀደም ወጥተውእንደቀሩት የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ምሁራን ደብዛቸውን ሊያጠፉ እንደሚችሉ ስጋታቸውን እያራገቡ ይገኛሉ።

ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ