ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን !!! አንዳርጋቸው ጽጌ የጊዜ ጀግና ሳይሆን የሰው ጀግና ነው !!!!ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለሰው ልጆች ሕልውና ስኬት ... ለነጻነት ለዲሞክራሲ ለፍትህ እና ለኢትዮጵያዋይት ታላቅ ትንሳኤ ደፋ ቀና ሲል በጅቦች እጅ የገባው ታላቅ ሰው አንዳርጋቸው ጽጌ ዘላለም በትውልድ ሃረግ ውስጥ ሲታውስ የሚኖር የጊዜ ጀግና ያልሆነ የሰው ጀግና የሆነ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ነው።

አንዳርጋቸው ጽጌ ወያኔዎችን ከውስጣቸው ጀምሮ የታገለ ተነጥሎም በቅንጅት እና በግንቦት ሰባት ድርጅቶች ውስጥ እስከ ወታደራዊ አዛዥነት የሰራ ወንድ ታሪክ የማይሽረው በፍጹም ሊረሳ የማይችል የ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያዊ ጀግና ነው። አንዳርጋቸው ብዙ ያልተጻፉለት እና ያልተነገሩለት የትግል ስኬቶቹን የያዝ ታላቅ ታጋይ ነው። አንዳርጋቸው ለማንም ያልተበገረ ለግል ጥቅሙ ያላጎበደደ ለስልጣን ጥማት ያልተገዛ ቁምጣውን ለብሶ ቤተሰቡን ትቶ በኤርትራ በረሃዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ታላላቅ ወጣት ታጋዮችን ያፈራ የትግል ሰው ነው።

አንዳርጋችው ቆራጥ ለምንም የማይበገር ሲሆን ወያኔዎች ቢይዙትም አንዳርጋቸው አንድ ጊዜ እጃቸው እንደገባ እና ተመልሰው እንደማይለቁት ስለሚያውቅ እንዲሁም አንድ ታጋይ መዘጋጀት ያለበትን ዝግጅት ያደረገ ታላቅ ሰው ስለሆነ በፍጹም አያሸንፉትም በተቃራኒው በከባድ የቃላት ቀውስ ውስጥ ሊከታቸው እንደሚችል እንጂ በፍጹም ከአንዳርጋቸው አንደበት የግንቦት ሰባትን ገበና አገኛለሁ ማለት ዘበት ነው። ይህም ያልተሳካለት ወያኔ አንዳርጋቸው ራሱን እስኪስት ቶርች ቢያደርገዉም ሃቅን ማግኘት አልቻለም ። አይችልምም።

አንዳርጋቸው ጽጌ ራሱን ዝቅ አድርጎ እንደ ሌሎች የተቃዋሚ መሪዎች ሳይኮፈስ የአውሮፓን ምርጥ ከተሞች በመተው የግል ዝና እና ስም ሳያስጨንቀው የኤርትራን ተራሮች ክላይ ታች በመውረድ እሾህ ወጋኝ ጸሃይ አቃጠለኝ ሳይል ለሃገሩ ነጻነት ዝንተ አለም የማይረሳ ታላቅ አስታውጾ ያበረከተ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ