ሕወሓት በትግራይ አሯሯጭ ተለጣፊ ፓርቲ ሊመሰርት ነው።Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የትግራይ ስብስቡ በጂጁ ሆቴል እቅዳቸው የህወሓትና የደህንነት ሰዎች ባሉበት ኣውጥተዋል ::
ሕወሓት በትግራይ ከዚህ ቀደም በሚደረጉ ምርጫዎች ካለምንም ተወዳዳሪ በብቸኝነት ተወዳዳሪ ሲመጣ ደሞ ስም በማጥፋት እና በጉልበት በመደቆስ በብቸኝነት ምርጫዎችን እያሸነፈ ላለፉት 23 አመታት ዘልቋል። ካለፉት 6 አመታት በኋላ አረና ትግርያ ብሎ የሚጠራ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲ ተመስርቶ በትግራይ ውስጥ እንቅስቃሴውን እያስፋፋ ባለበት ሰአት በመጭው ምርጫ እሸነፋለሁ ሕዝቡ በድምጹ ይጥለኛል የሚል ከባድ ስጋት ስላለበት ከአረና ፓርቲ ጋር ይመሳሰላልኛል ያለውን ተለጣፊ ፓርቲ ለመመስረን እንቅስቃሴ መጀመሩን ታውቋል።

በዚህ ዓመታት ውስጥ ከ 4 ግዜ በላይ የህወሓት ዓረናን የማፍረስ እቅዶች ተመኩረው በኣባላቱና በኣመራሩ ጥንካሬና ክትትል ሊከሽፍ ችልዋል ::ህወሓት በተደጋጋሚ እንደ ትልቅና መሰረታዊ ጥያቄ ኣድርጎ የሚልካቸው  ሰርጎ ገቦች የወጣቶች ድርጅት ብናቅዋቁም ፣ህወሓት እየተከታተለ ኣይመታንም ፣ በቂምበቀል የተደራጁ ኣንባልም ፣ ምርጫው ሙሉበሙሉ አይዘርፈውም ፣ ከመድረክ ብንወጣ እናሸንፍ ነበር ወዘተ የሚሉ ሕወሕታዊ ሃሳቦችን በማምጣት አረናን ለመበታተን ያደረጉት ተሞክሮ ሃሳባቸው ተቀባይነይ በማጣቱ ሳይሳካ ቀርቷል ::

የዓመቱ ዓረናን ኣፍርሶ ኣዲስ ድርጅት የመፍጠር እቅድ ከባለፈው የወረዳና ያከባቢ ምርጫ ህወሓት በትግራይ መፍጠር ግድ ሁኖ በማግኘቱ ነው ::በዚህ መሰረት በ 4ቱ ዙር ዓረና የማፍረስ ዘመቻ የተሳተፉና የተጠቀመባቸው በአዲስ ድርጅት ምስረታ ብሎ መሰብሰብ ጀምረዋል :: ይህም ዓረና ባለፈው ታህሳስ ወር በመግለጫው  ማሳወቅ መኖሩ የሚታወስ ነው :: ይህ ተለጣፊ ፓርቲ በመመስረት ሂደት ዋና ተዋናዮች ካሉት መካካል ጉዕሽ ገ/ፃድቅ ከአዲስ አበባ ፣ ገብሩ ሳሙኤል ፣ ሽሻይ ኣዘናው ፣ ገ/ኣረጋይ ኣስናቀ ከትግራይ የሚገኙባቸው ናቸው ::
የታህሳስ ወር የትግራይ ስብስቡ በጂጁ ሆቴል ተሰብስበው እቅዳቸው የህወሓትና የደህንነት ሰዎች ባሉበት ኣውጥተዋል ::