የወያኒዎች ድርጊት ለጊዜው ጅግንነት ይምሰላቸው እንጂ በኋላ ውርደቱ የከፋ ነው።

ወያኔ በገዛ እጁ እየገባባቸው ያሉ አዘቅቶች አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎UDJ‬ ‪#‎Ginbot7‬ ‪#‎Blueparty‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬
የወያኒዎች ድርጊት ለጊዜው ጅግንነት ይምሰላቸው እንጂ በኋላ ውርደቱ የከፋ ነው።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የወያኔ ባለስልጣናት በአውሮፓ እና በአሜሪካ በሚጓዙባቸው አገራት ላይ ከባድ ውርደትን እየተሸከሙ ነው። ይህ ጉዳይ ሳያሳስባቸው አልቀረም ፡፤ በዲያስፖራው ላይ ስብሰባ ተቀምጠዋል ውጤት አልባ መሆናቸውን አላወቁትም አሁንም። የመፍርክከሳቸው ነገር እየጨመረ በሄደ ሰአት አምባገነንነታቸው እየጎለበት ሲፋፋ የማይከስም መስሏቸው አሁንም የዲያስፖራውን ተቃውሞ በተመለከተ ለምን ብለው መጠየቅ እና ሕዝባዊ መልስ መስጠት ሲገባቸው እንዴት ተደፈርን ብሎ መሰብሰብ የትም አያደርስም የባሰ ነገሩን እያሰፉ ውርደትን ከመከናነብ ውጪ።
በዲያስፖራው የሚደርስባቸውን ውርደት ሲያስቡ ያሰሩትን መፍታት ሙስናቸውን ማስውገድ የኑሮ ውድነቱን ማስተካከል በሃገሪቱ የሰብ አዊ መብቶችን በተመለከተ ያሉትን ጥሰቶች ማስተካከል። ይህ እና የመሳሰሉትን ቀድሞ ማሰብ ያስፈልጋል ሃገር ውስጥ ለዜጋ ቀጋ ሆኖ ውጪው አገር ላይ አልጋ በአልጋ መሆን እንደማይቻል የመገንዘብ ግዴታ አለባቸው።
የወያኔ ሚዛን ያጣው አስተሳሰቡ ወደ ሌላኛው የ እዳ ክፍል ይዞት እየተመመ ነው። ጋዜጠኞችን የፖለቲካ ሰዎችን የሃይማኖት ምሁራንን ጦማሪያንን ወያኔ ያልያዘው ያልከሰሰው በነጻነት ሃሳቡን የገለጸ ዜጋ ማን ይሆን ? ? ? አሁን ደሞ ፊቱን ወደ ጠበቆች እያዞረ ነው። የኢትዮጵያን ህዝብ ከፋፍሎ እና በታትኖ ካለተከራካሪ ካለ አደግ ጊዜ ተጠር እና ካለሃግ ረግጦ ለመግዛት በፍርድ ቤት አቤት የሚሉ ጠበቆችን ለተቃዋሚዎችም ይሁን ለተበደሉ ዜጎች እንዳይቆሙ ማስፈራራት ጀምሯል። ካለሰብ አዊ መብት ተቆርቋሪ ዜጎችን አፍኖ ለመግዛት እና የስነልቦና ጫና በማድርግ መብት እንዳይጠየቅ የሚሰሩ አምባገነናዊ ስራዎች በስፋት እየተሰሩ ናቸው። ይህም ወያኔ በላዩ ላይ እየሰራ ያለው አደገኛ እዳ ነው።
ይህን አደገኛ ወያኒያዊ የአፈና አስተሳሰብ አስቀርቶ ህዝባዊ መፍትሄ መፈለግ ሲገባ ዜጎችን ሰበብ እየፈጠሩ በአሸባሪነት ስም ወህኒ ማጎር አያዛልቅም ፡፤ለጊዜው ጅግንነት ይመስላል እንጂ በኋላ ውርደቱ የከፋ ነው። ወያኔዎች ሊቋቋሙት የማይችሉት አዘቅት ውስጥ እንደገቡ የሚፈጽሙት ድርጊት ማሳያ በቂ ማስረጃ ነው። የኢትዮጵያ ማሕጸን በቂ እና የተማረ ሃይል የመፍጠር አቅሙ ሰፊ እንጂ ጠባብ አይደለም የታሰሩት ሁሉ ባይፈቱን እነሱን ሊተኩ ያዉም በ እጥፉ ሊያጥፉ የሚችሉ ሃይሎች በየጊዜው ከ እናት ሃገር ማሕጸን ይወለዳሉ። ወያኔን እንቅልፍ የሚነሱ ኢትዮጵያውያን አሁንም እየተፈጠሩ መሆኑን ወያኔ ሊገንዘብ ይገባዋል። በሃይል የህዝቦችን ጥያቄ አዳፍናለሁ ማለት ራስን አዳፍኖ ማስቀረት እንደሆነ ወያኔ ሊረዳው ይገባል። አሁንም ትግሉ ይቀጥላል ።