አጠቃላይ ጉባኤውን ፀረ – ማኅበረ ቅዱሳን አቋም ለማስያዝ ፓትርያርኩና ጥቂት አማሳኞች በዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ ጫናቸውን አጠናክረዋል

Zekarias Addis a day light robber
የጫናው ዋነኛ አስተባባሪ ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ፤ የአጠቃላይ ጉባኤው ተሳትፏችኹ የታዛቢነት ብቻ ነው! ‹‹የቅዱስ ፓትርያርኩ መብት ተጥሷል›› እያላችኹ ጉባኤተኛው ውድቅ ባደረገው የቅስቀሳ አጀንዳ ማኅበረ ቅዱሳንን ለማስወገዝ ‹‹መድረክ ይከፈትልን›› በሚል በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ የምታደርጉት ግፊት ሀገረ ስብከቱን ይኹን የሀገረ ስብከቱን ገዳማትና አድባራት አይወክልም!
 • አማሳኞቹ በአጠቃላይ ጉባኤው የሚሳተፉት በታዛቢነት ብቻ ኾኖ ሳለ ‹‹መድረኩ ለምን አይለቀቅልንም›› በሚሉ የጽሑፍ መልእክቶች ግፊት የውይይት መርሐ ግብሩን ተጠቅመው የፓትርያርኩን ‹‹የቅኝ ገዥ ነው!›› ቅስቀሳ ለማጠናከርና ፀረ – ማኅበረ ቅዱሳን መግለጫ እንዲወጣ በዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ የሚያካሒዱት በዛቻና ማስፈራሪያ የታገዘ ጫና እንደማይወክላቸው የአዲስ አበባ ልኡካን እየገለጹ ነው፡፡
 • ‹‹ሰሞኑን መቅሠፍት አለ›› በሚል ከንቱ ማስፈራሪያ በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ በተለያየ መንገድ ጫና ከመፍጠር አልፈው አካላዊ ጥቃት ለማድረስም እየተሰናዱ መኾኑ ተጠቁሟል፡፡ የአማሳኞች እንቅስቃሴ አይወክለንም ያሉት ተሳታፊ ጉባኤተኞችና ብዙኃኑ የአ/አ ገዳማትና አድባራት ልኡካን ለአጸፋ እንቅስቃሴ እየተዘጋጁ መኾኑ ተጠቅሷል፡፡
  ???????????????????????????????
  ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ
  ???????????????????????????????
  የ፴፫ኛው የመ/ፓ/አጠ/ሰ/ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ተሳታፊ የአህጉረ ስብከት ሓላፊዎች
  ???????????????????????????????
  የዓመታዊው ስብሰባ የአህጉረ ስብከት ልኡካን በከፊል
 • የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች በሪፖርታቸው፣ ማኅበረ ቅዱሳን÷ በተለይ በጠረፋማ አህጉረ ስብከት አዲስ አማንያንን አስጠምቆ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ባደረገበትና የምእመናንን ቁጥር በጨመረበት፤ በተለያዩ ቋንቋዎች የተተኪ መምህራንና ካህናት ሥልጠና ባካሔደበት፤ የአብነት የአዳሪ ት/ቤቶችን እንዲኹም የዘመናዊ ት/ቤቶችን ግንባታ በጀት መድቦ የዲዛይንና ክትትል ሥራ በሠራበትና የግንባታቸውን ጠቅላላ ወጪ በሸፈነበት፤ በቅዱሳት መካናት የልማት ፕሮጀክቶች ቀረፃና በሕግ የማማከር አገልግሎት በሰጠበት፤ በ341 የመንግሥትና የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባደራጃቸው ግቢ ጉባኤያት 200,000 ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎችን በትምህርተ ሃይማኖት ባሠለጠነበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከፍተኛ ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡
 • በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አጠቃላይ ሪፖርትና በአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ሪፖርት ስለማኅበረ ቅዱሳን ኹለንተናዊ አገልግሎት በአጽንዖት በተጠቀሰው ከፍተኛ ዕውቅናና ብዙኃን ጉባኤተኞች ለዕውቅናው በሰጡት ደማቅ ድጋፍ÷ ‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ ነው›› ክሣቸው በተጨባጭ የተስተባበለባቸውና የ‹‹ተቆጣጠሩት›› ቅስቀሳቸው ውድቅ የተደረገባቸው ርእሰ መንበሩ ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ በዓመታዊ ጉባኤው መክፈቻ ዕለት ጫማቸውን ትተው በባዶ እግራቸው ከአዳራሹ እስከ መውጣት ድረስ ስሜታዊ እንደነበሩ ተስተውሏል፡፡ በአኳኋናቸው ያዘኑት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ‹‹ብክይዎ እለ ታፈቅርዎ ለአባ ማትያስ›› በሚል ‹‹አላበድኹም›› ስላሉት ፓትርያርክ እያዘከሩ ነው፡፡
Nebured Elias Abreha, special secretary of the patriarch Aba Mathias
የፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ
 • ዛሬ እንደሚጠናቀቅ በሚጠበቀው የአጠቃላይ ጉባኤው የስብሰባ መርሐ ግብር፣ ፓትርያርኩ በመክፈቻ ቃለ በረከታቸው በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያሰሙትንና ብዙኃን ጉባኤተኞች ለማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት አስተዋፅኦ በሰጡት ደማቅ ድጋፍ የተስተባበለባቸውን ‹‹የቅኝ ገዥ ነው›› ቅስቀሳ የሚያጠናክር ንግግር በልዩ ጸሐፊያቸው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ መረቀቁ ተሰምቷል፡፡