"ተግባራዊ እንቅስቃሴ እስካላየን ተቃዋሚዎችን መርዳት አንችልም።" የምእራብ ዲፕሎማቶደህንነቱ እና የጦር ሰራዊቱ የሃገሪቱ ቢሆኑ ኖሮ ገዢው ፓርቲ እድሜ አይኖረውም ነበር።
Minilik Salsawi
በአዲስ አበባ ያለውን እና በዲያስፖራው ዘንድ ያለውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ አስመልክቶ በዋና ከተማዋ ያሉ የምእራባውያን ዲፕሎማቶች ተቃዋሚዎች ያላቸውን ሃይል አሰባስበው በተገኘው መንገድ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እስካላደረጉ ድረስ በውጪም በውስጥም ያሉትን ለመርዳት እና ለማበረታታት ከብሄራዊ ጥቅም አንጻር እንደማይቻል መናገራቸውን ምንጮች ጠቆሙ።የሀገሪቱን የደህንነት እና የመከላከያ እንዲሁም የደህንነት ተቋማት ማሳመን ያልቻሉ አሊያም ገዢውን ፓርቲ በህዝብ ተከታታይ አመጽ ማስደንገጥ የማይችሉ ተቃዋሚዎችን መደገፍ እንደማያዋጣ አስምረውበታል።
በአዲስ አበባ ውስጥ በየሳምንቱ አትላስ ሆቴል አከባቢ በሚገኝ አንድ የውጪ ድርጅት አደራሽ ውስጥ ልምድ ለመለዋወጥ በሚሰበሰብ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የመወያያ መድረክ ላይ በተደረገ ውይይት በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ አስመልክቶ የተናገሩት ዲፕሎማቶች ለምህዳሩ መጥበብ ገዢውን ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ትቃዋሚዎችንም ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን ከንግግር ውጪ ሕዝብን ይዘው ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማድረጋቸውን እንዲሁም የጠራ አመለካከት እና አቅጣጫ ያሌላቸው አማርጭ ሳይሆን ተመሳሳይ አቋም ይዘው እርስ በ እርስ የሚናከሱ እንዲሁም በፓርቲ ስራ የተተበተቡ ሃገራዊ አጀንዳቸውን ማስተካከል ያልቻሉ ሲሉ ወርፈዋቸዋል።
በቂ የሆነ የመረጃ ስራ የማይሰሩ አንዱ ከአንዱ ጋር በፖለቲካ አስተሳሰብ ክብር ያልተካኑ በሃገራዊ ግብ እና ራ እይ ሳይሆን በግለሰብ ንግግር የሚያምኑ ስትራቴጂ ማሳካት ሳይሆን በአጉር ዘለል እና በአሉባልታ የታጀሉ ናቸው ሲሉ ገዢውን ፓርቲ ጨምረው ሲወርፉ ገዢው ፓርቲ የደህንናእት እና የጦር ሰራዊቱ ያራሱ የፓርቲው መሆናቸው እንጂ የሃገሪቱ ቢሆኑ ኖሮ እስካሁን እድሜው እንደማይቆይ በግልጽ አስቀምጠዋል።
የመወያያ መድረኩ የሚዘጋጀው በምስራቅ አፍሪካ የኢትዮጵያውያን መያድ ማህበር ሲሆን ውይይቱ ለሚዲያ ዝግ እንደሆነ ታውቋል።ውይይቱ ልምድ እና የለውጥ ሂደትን ለመማማር የተዘጋጀ በመሆኑ መቅዳትም ይሁን መቅረጽ የተከለከለ ሲሆን ማህበሩ በቅንጅት ምርጫ ወቅት ክፍተኛውን የለውጥ ሚና የተጫወተ እንደነበር ምንጮቹ ገልጸዋል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬