አዲስ አበባ በግድግዳ ላይ መፈክሮች ተጥለቅልቃ አደረች:ደፍሮ መፈክሮቹን የሚያነሳ አልተገኘም: Photos And Video


Image 


ኢወጋን - በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ ቦታዎች ላይ የቅስቀሳ መልእከቶችን ለህዝብ እይታ አብቅቷል።
የአትዮጵያ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (ኢወጋን)አባላት በአዲስ አበባ ዋና ዋና የህዝብ መገናኛ ቦታዎች እና የአውቶብስ መጠበቂያ የገበያ ቦታዎች ላይ የወያኔን ስርአት የሚያወግዙ እና ስርአቱን ለማውረድ ህዝቡ በጋራ እንዲነሳ የሚያደርጉ ጥሪዎችን ያነገኡ መፈክሮችን በመለጠፍ እንዲሁም ለፖሊስ እና ጦር ሰራዊቱ የሚገባውን የአንድነት እና የህዝብህን አድን ጥሪ በማስተላለፍ የተሳካ ስራ መስራታቸውን ከአዲስ አበባ ኢወጋን የደረሰን መረጃ ያመለክታል::በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ ቦታዎች ላይ የቅስቀሳ መልእከቶችን ለህዝብ እይታ አብቅቷል።
መላው ኢትዮጵያዊ ወጣት ከኢወጋን ጎን እንዲሰለፍ ጥሪውን በአክብሮት ያስተላልፋል።
በቭድዮ የተደገፈ ዝርዝር ዜናውን በኢትዮጱያ ወጣቶች ድምጽ በኩል ይፋ እናደርጋለን።
ያለ መስዋዕትነት ድል የለም !!! - የኢትዮጵያ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (ኢወጋን)አዲስ አበባImage