ኢሳት እንደሚዲያ ጥፋት የለውም::ቦርዱ ጉዳዩን ሊያየው ይገባል:: Minilik Salsawi

ሰዎች ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብት አላቸው::የህዝቦችን ነጻነት መጋፋት ጋዜጠኛ አያሰኝም::
ጥፋተኛው የኢሳት ኢዲቶሪያል ሳይሆን የጥቂት ግለሰቦች የማናለብኝነት እና በስሜት የመነዳት ፖለቲካ ነው:: አዎን ምናልባት አንዳንዶች በልቅ የፖለቲካ ስድነት ያሸበረቁ ግለሰቦች ስማቸውን የቀያየሩ ሰውን በየድህረገጹ የሚዘልፉ የኢሳት ጋዜጠኞች ይህ ጽሁፍ ላይመቻቸው ይችላል::

ኢሳት ገና ከጅምሩ ሲመሰረት ህዝባዊ አላማ አንግቦ እና ህዝባዊ ስራዎችን ለመስራት እንደተቋቋመ የማይካድ ሃቅ ነው::ኢሳት የሰራቸው በጎ ተግባራት እንደተጠበቁ ሆነው እጅግ ሊሻሻሉ እና ሊታረሙ የሚገባቸው ጥፋቶችም በገሃድ አይተናል እያየን ነው::አብዛኛው ጥፋቶች የሚከሰቱት ዲሲ ከሚገኘው እና የግንቦት ሰባት አመራሮች በስሜት ፖለቲካቸው ከሚነዱት ስቱዲዮ መሆኑን ስንመለከት ደሞ ራሳችንን እንድንጠይቅ አድርጎናል::

ለኢሳት ስኬት አስፈላጊውን አስታውጾ እና ድጋፍ እስካደረኩ ድረስ የኢሳት ጉዳይ ያገባኛል ይመለከተኛል:: አንዳንድ ኢሳት የነሱ ብቻ የሚመስላቸው አዋቃጭ ግለሰቦች በደመነብስ የሚናገሩትን አልባሌ ቦለቲካቸውን ወደ ጎን በመተው ኢሳት ሊጠናከር የሚችለው ያለበትን ሲያርም እና በውስጡ የተወሸቁ ስሜታዊ እና ልቅ ጋዜተኞችን ሃይ ማለት ሲችል ብቻ ነው::አንድ ሳው አስተያየት በሰጠ ሰአት ሁሉ እየተነሱ የኒዛለፉ እና የሚሳደቡ ባለጌ ጋዜጠኞች እና አዋቃጭ ተባባሪዎቻቸውን ሊያርማቸው ይገባል::ጥላቻን ማራመድ በቀረበት በዚህ ስልጡን ዘመን ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያውያን ላይ ጥላቻ እንዲያራምዱ የሃገር ጉዳይ ተረስቶ ግለሰቦች እንዲዘረጠጡ በተራ አሉባልታ እና የስድብ ናዳ ጊዜ እንዲጠፋ የሚያደርጉ ሰዎችን ታቅፎ መጓዝ ከተጠያቂነት አያድንም::

የኢሳት ጋዜጠኞች በሃገር ውስጥ እና በውጪ ሃገር የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችን ወደ አንድነት እና የጋራ አጀንዳ እንዲመጡ መስራት ሲገባቸው እየከፋፈሉ የህዝብ የለውጥ ጥያቄ እና የነጻነት ጥማት እንዲዘገይ አድርገዋል::በሃገር ቤት የሚገኙ ፓርቲዎችን አንዱን ከፍ አንዱን ዝቅ በማደረግ በየፕሮግራሞቻቸው እኩልነትን ባላስተናገደ መልኩ በመዝለፍ እጅግ አሳፋሪ የሆነ የጋዜጠኝነት ስራ ስውርተዋል::በስሜት የሚነዱ ጥቂቶች የህዝብ ቤት ይሆናል የተባለውን ኢሳትን የራሳቸው የስሜት ሃሳብ መጋለቢያ አድርገውታል::በውጪ ሃገር የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማግለል የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ስም ገኖ እንዲወጣ ተግተው ሲሰሩ በተግባር እያየን ነው::ስለዚህ ኢሳት የኔ ነው እስካልን ድረስ የኢሳት ጉዳይ ይመለከተናል እንዲታረምም ሂስ የመስጠት መብታችን የተጠብቀ ነው::ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ብዙ ማለት ይቻል ነበር ግን የኢሳት ቦርድ ሁኔታውን አይቶ ሊያስተካክል ይገባል::
Image