በበረሃ የተቀመጡት ታጋዮች ደህንነታዊ ጥንቃቄ ሲባል የቅብብሎሽ ሂደት ቢኖርም እውነት ሰአቷን ጠብቃ ነጻ ትወጣለች:: ‪Minilik Salsawi‬ብንውጠም ባንውጠውም ቢያቅለሸልሸንም ቢያስመልሰንም ፖለቲካ ውስጥ ካለ እውቀት ተዘፍቀን የምንዋልል የደረቅ ትኩሳት መርህ ተጠቂዎች እና የስሜት ፈረስ ጋላቢዎች ማወቅ ማገናዘብ ባይፈጥርብንም ካሳለፍነው ካለው የሚምጣውን እንዳቅማችን ለማንደርደር ማሰብ እንዲጠበቅብን መመከርን ባንጓጓም አንድ ነገር ግን እንድናውቅ በራሳችን የገደል ማሚቱ ውስጥ እያላተም መጎላኮስ የሚኖርብን ነገር ቢኦር እውነት ሰአቷን ጠብቃ ነጻ ትወጣለች !!! የሚለውን ሃቅ ነው:: እኛ የሚለውን በእናንተ ሂሳብ አወራርዱት::

የዚህ ሰሞን የወሬ መላምቶች ወደ ተግባር በረራ ተለውጠው ብርቱዎቹ አስመራ ከትመዋል:: በደጋፊ በተባባሪ በጠርጣሪ እና በተቃዋሚ ብልቶች መካከል በየማህበራዊ ድህረገጹ እና ፓልቶክ የጡዘት ስሪቶች እየተፈተሉ ነው::ደጋፊ በኢትዮጵያ ላይ ያለው የሰቆቃ ስርአት ከስሩ ተመንግሎ እንዲወድቅ ካለው መልካም ምኞት በሃገር ወዳድነት ስሜት ሃሳቡን ሁሉ እዚያው አድርጎ ይተነገረውን ሁሉ ተቀብሎ በመፍከንከን ላይ ሲሆን ተባባሪዎች ደሞ የነአይዞን ስራቸውን በፖለቲካው ንግድ ውስጥ እያጧጧፉት ነው::ተጠራጣሪው በዋናነት ያተኮረው በሻእቢያ ላይ ያለውን እምነት በማሰላሰል አስመራ ለከተሙት ብርቱዎቹ ኢትዮጵያውያን ደህንነት ሲሆን በለሆሳስ ጸሎቱን በማደረስ ላይ ሲሆን ተቃዋሚ የተባሉት ያው የወያኔ አሽከሮች የዘመኑ ፖለቲካ እና የለውጥ ማእበል ያልገባቸው ድፍርስ ሆዳሞች ሲያላዝኑ ማየት ምን ያህል እውቀት አልባ እንደሆኑ ሲመዘን ያሳፍራል::

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋና አጀንዳ ሻእቢያ ሳይሆን ወያኔ ነው::በኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ እንግልት እስር ሰቆቃ ግድያ ወዘተ እየፈጸመ የሚገኘው የህዝቦች ጠላት ወያኔ እና ወያኔ ነው!ይህንን ስር አት ለማውረድ በውስጥም በውጭም በስፋት ትግሉ ቀጥሎ ይገኛል:; ከበፊቱ በትሻለ ሁኔታ የተያዘው ትግል ወያኔን እያፍረከረከ በራሱ ፍርሃት እንዲሸበር አድርጎታል::ሊቀጥል የሚገባው ትግል መሆኑ እሙን ነው::በውጪው ያለው ሃይል በትጥቅ ትግል ተሰማርቻለሁ የሚሉ ቡድንኖች ከ15 አመታት በላይ በአስመራ መሽገው ይገኛሉ::እነዚህን ሃይሎች በትለያየ ጊዜ የተቀላቀሉ የጎበኙ የተገነጠሉ ወዘተ አካላት የየራሳቸውን አስተያየት በይፋ ስጥተዋል::ወያኔን ለመጣል ካላቸው ፍላጎት የመነጨ በአስመራ የመሸጉትን ታጋዮች ጎብኝተናል ያሉ ሁሉ ከበጎ ጎኑ ተነስተው ኢሳያስ አፍወርቂን እስከ ማሞገስ እና እጅ እስከመሳም ከመድረስ አልፈው ሁኔታዎችን እያጠሩ ሂደው በተመጣጠነላቸው ሰአት ላይ እውነታውን አፈንድተውታል::እውነታውን በማውጣታቸው ይህን ተከትሎ በአስመራ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ከግድያ እስከ እስር እና እንግልት ደርሶባቸዋል:;ማምለጥ የቻሉም አምልጠው ኤርትራን ለቀዋል::

ጎን ለጎንም አስመራ ከትመው የሻእቢያ ስራ አያዋጣን ደባውና ሴራው ለኢትዮጵያ ነጻነት በሚደረጉ ትግሎች ላይ ከፍተኛ እንቅፋት ነው በሻእቢያ እርዳታ ነጻነት ሳይሆን ባርነት ነው የገዛነው ታጋዮቻችን በስልተና ሳይሆን በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው ቀን እየገፋን አንችልም ሻእቢያ በበቂ ሁኔታ አደራጅቶ እንድንዘምት ሊያደርገን ሳይሆን ብስማችን ገንዘብ እየሰበሰበ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ እንጂ ውጤት የለውም ያሉ አስመራን ትተው ሃገር ቤት እስጥ የትጥቅ መሰእረታችንን ዘርግተናል ብለዋል::እንዲሁም ከጨካኙ ወያን ጋር በመቀላቀል የታጋይ ድርጅቶችን ምስጢር በመባከን በመሰለል ደባ የፈጸሙ ቅጥረኞችም የማይርሳ መጥፎ ተባሳ እና የትግል መጓተት አስከትለዋል::

የሰሞኑ አነጋጋሪ ጉዳይ ደሞ አንደ እውነት ካለ በፍጥነት ከዘገየ ደሞ ቀኑን እና ሰአቱን ተብቆ እንደሚያሰማን ራሳችንን አዘጋጅተን እየጠበቅን ነው::ሁኔታዎችን በጠራ መንገድ ተከታትለን አይተን እንዘግባለን ያሉ ብርቱዎቹ ኢትዮጵያውያን አስመራ ደርሰው በረቀቀ መንገድ ችሎታቸውን እና ክህሎታቸውን ተጠቅመው አንድ እውነት ይዘው እንደሚመጡ የታመነ ሲሆን ግን ግን ወዲያው እንደማይተነፍሱን የተረጋግጠ ጉዳይ ነው::ከዚህ በፊትም አስመራ የደረሱ ከታች እስከ አናቱ ኢሳያስ ድረስ ቃለመጠይቅ ያደረጉ ውነታውን ያጠሩት በሂደት ሲሆን እነዚህም ብርቱዎቹ እንደአካሄዳቸው ተመልሰው ያለውን ሁኔታ እና እውነታ በሂደት እንደሚያሳውቁን ተስፋ ሰንቀናል:: ሻእቢያ እና ልጁ ወያኔ በሃሰት ዶክመንተሪ እና በዉሸት ፕሮፓጋንዳ የታወቁ የፈጠራ ደራሲዎች ቢሆኑን ህዝቡ እውነታውን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በተግስት በመከታተል ትግሉ እያፋፋመ እንደሚገኝ እሙን ነው::በኤርትራ ሃገርን ከዛሬ ነገ ዘምተን ነጻ እናወጣለን ብለው ሰልጥነው በበረሃ የተቀመጡት ታጋዮች ለነሱ ሕይወት እና ደህንነታዊ ጥንቃቄ ሲባል ራሱን የቻለ የቅብብሎሽ ሂደት ቢኖርም እውንት ግን ሰአቷን ጠብቃ ነጻ ትወጣለች::ፖለቲካ የሚገባው ይገባዋል የማይገባው ጭፍን ግን አንብቦ ምራቁን ይዋጥና አርፎ ይጸልይ::

Image