Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - የኑሮ ውድነት የአንድ ሃገር የፖለቲካ አስተዳደር መበላሸት አካል
መሆኑ ይታወቃል፡፡ የወያኔው ስርአት የሚያራምደው ቅጥ ያጣ የንግድ አተገባበር ባለስልጣኖች እና ወገኖቻቸው ከፈጠሯቸው ጥገኞች ጋር በማበር ከፍተኛውን የዘረፋ እና የንግድ ሂደቱን የመቆጣተር ስራዎችን እየሰሩ ነው:: አምባገነኖች ቡድን ፈጥረው የገነቡት የቡድን ዝርፊያዎች እና ጐጠኝነት ሙስና/ጉቦ እና የፍትህ እጦት በኢትዮጵያ እየተንሰራፋ ለመጣው የኑሮ ውድነት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ የኑሮ ውድነትና የፖለቲካ አስተዳደር እጦት ተወራራሽ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡የፖለቲካ አስተዳደሩ ካልተወገደ ድረስ የኑሮ ውድነትንም መቅረፍ የማይቻለው ከዚህ ተወራራሽነት መነሾ መሆኑ አይካድም::የፖለቲካ አስተዳደሩ መወገዱ በሂደት ስራዎች የኑሮ ውድነትን ሊቀርፍ ይችላል::

በኢትዮጵያ ያለውን የጅምላ ስርጭት በሞኖፖል የያዘው የወያኔው የንግድ ድርጅት የሆነው ኤፈርት መሆኑ በይፋ የምናየው ጉዳይ ነው:: ንግዱን በሞኖፖል ተቆጣጥሮት በመንግስት የገበያ ተቋማት ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ወያኔ ራሱ የገንዘብ አቅርቦት እና የዋጋ ትንበያዎችን በማስፋፋት በሃገሪቱ ላይ የኑሮ ውድነት እንዲስፋፋ በጭፍን እየሰራ ይገኛል::ስለሃገር እና ስለ ህዝብ ደንታ የሌለው ይህ ስርአት ከልክ በላይ ገንዘቦችን በማተም እና በማሰራጨት መንግስት ከባንኮች በመበደር የውጭ ምንዛሬን በማከማቸት ወዘተ የሃገር ኢኮኖሚ ከሚችለው በላይ የኢኮኖሚ ውዥንብሮችን በመፍጠር በልማታዊ መንግስትነት ስም የኑሮ ውድነት እንዲንሰራፋ በማድረግ ከፍተኛ ችግርን ለህዝብ አሸክሞ በህዝብ ትከሻ ላይ በመቀመጥ እኩይ ብዝበዛውን እያደረገ ይገኛል::
የኑሮ ውድነቱ እያሻቀበና ህዝቡን እያስደነገጠ ነው፡፡አጠቃላይ የምግብ ፍጆታዎች ሰሞኑን ዋጋቸው አሻቅቧል፡፡ የኑሮ ውድነቱ ችጋር/ድህነት ችጋሩ ደግሞ ጐጠኛ አስተሳሰብና አሠራርን ልቅ ሙስናን የፍትህ እጦትን በተግባር ፈጥረዋል::የፖለቲካ ሥርአቱም አደጋ ላይ መውደቁን በተግባር እያየን ነው::ከዚህ የኑሮ ውድነት መገላገል የምንችለው ከድህነት አለንጋ ራሳችንን ማዳን የምንችለው በአንድነት ሆነን የበሰበሰውን የወያኔን ስር አት መደምሰስ ስንችል ብቻ ነው:;የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት አንድ እና አንድ ነው ወያኔ ነው:: ወያኔን ደሞ በጋራ በአንድነት ቆመን ልናስወግደው እና በመቃብሩ ላይ ነጻነታችንን በማረጋገጥ በህዝባዊ ምጣኔ ሃብት ስኬት ከኑሮ ውድነት መላቀቅ የምንችል መሆኑን ለመናገር እወዳለሁ::