እያለማን ነው እየሰራን ነው በሚል ሽፋን ዜጎችን ማሳደድ መግደል ማፈንና ማሰር ላይ የተሰማራ መንግስት

Minilik Salsawi ህዝቦች እኩልነት ያልተረጋገጠባት ኢትዮጵያ : የብሄር ብሄረሰብ መብቶች ለይስሙላ በሚሰበኩባት ኢትዮጵያ ዜጎች ህግ ይከበር ብቻ ስላሉ በሌላው አለም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አሸባሪ ተብለው ወህኒ የሚወርዱባት ኢትዮጵያ የሃይማኖት ምሁራን ከአያት ቅድማያቶቻቸውን የተረከቡትን እምነታቸውን በነጻነት ለማካሄድ ሲሰሩ ታፍሰው ለ እስር የተዳረጉባት አገር ኢትዮጵያ:እያለማን ነው እየሰራን ነው በሚል ሽፋን ዘረፋ ላይ እና ዜጎችን ማሳደድ መግደል ማፈን እና ማሰር ላይ የተሰማራ መንግስት በነገሰበት አገር ውስጥ የምንኖር ተጨቋኝ ብዙሃን የህዝቦች የጋራ መተባበር እና ለለውጥ መነሳት አስፈላጊ እና እጅግ ወሳኝ ወቅት ላይ መሆኑን ማወቅ ይገባናል::

ወያኔ የያዘው መንገድ አጥፍተህ ጥፋ የሚል ጸረ ሰላም እና ጸረ ሕዝብ ከመሆኑም በላይ በጸረ አሸባሪነት ቁማር ምእራባውያንን ተገን በማድረግ ዜጎችን ለከፍተኛ እንግልት እና ሰቆቃ እየዳረገ ሲሆን በየትኛውም አለማችን ክፍል ያልታየ እና የሽብርተኝነት ውጊያ እናካሂዳለን የሚሉ ሃያላኖች እንኳን በተግብር በሃገራቸው ወንጀል እና ሽብር ሲፍጠር በፍጹም ዜጎቻቸውን የማይወነጅሉበትን ህግ ወያኔ ግን ህግ ይከበር የሰው ልጆች እኩልነት እና ነጻነት ይረጋገጥ ባሉ ዜጎች ላይ አጸያፊ እርምጃ ለመውሰድ እየተጠቀመበት ነው::

ይህ የማያዛልቅ የወያኔ ጸሎት አደገኛ ቅጽፈት ይዞበት መምጣቱ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል።ወያኔ የጀመረው የስልጣን ማስረዘሚያ ስልት ራሱን እና በክሎኒግ ያባዛቸውን ጭፍሮቹን ወደ መቃብር እያወረደ መሆኑ ለአፍታ ቆም ብሎ ማስብ አልቻለም።ካለወያኔ መኖር የማይችሉ በጥቅም የታሰሩ በደረቅ ፖለቲካ የታወሩ እውቀት አልባ ካድሬዎች እና ሹምባሽ ደህንነቶች የአገሪቱ አንጡረ ሃብት በመዝረፍ እና ዜጎችን በመግደል በዚሁ የሚቀጠል መሆኑን አስበውት ከሆነ ተሳስተዋል። በአሁን ሰአት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለውጥ ፈላጊ ሃይል መሆኑን ወደው ሳይሆን በግድ እውነትን እንዲውጡ እናደርጋቸዋለን። ነጻነት በእጃችን ነው ስለዚህ ለነገው ትውልድ እና ለዛሬው እኛነታችን ድል ተጎናጽፈን መብታችንን ለማረጋገጥ የዜግነት ድርሻችንን ማበርከት ግድ ይለናል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬