የመብት ጥያቄዎችን በሃይል ለማድበስበስ መሞከር ፍርሃት የወለደው ፖለቲካዊ እብደት ነው::Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የሃይል ሚዛን በጃችን ነው ... ምእራባውያን ለብሄራዊ ጥቅማቸው እስከተባበርናቸው ድረስ ኢትዮጵያውያንን በፈለገው መንገድ ብንረግጥ እና ብንገዛ ተቀባይነት አናጣም ... አንድ ወጥ ሃገራዊ ሳይሆን ጎሳዊ መዋቅር ዘርግተን የቀረውን ክፍል ብናሸው ብናሸብረው በራሳችን ስራ ሕዝብን ብንወነጅል ማንም ምንም የሚያመጣው ነገር የለም ... ወዘተ የመሳሰሉት እኩይ ምግባራት ብንፈጽም እና ብናስፈጽም ሰጥ ለጥ አድርገ መግዛት እንችላለ በሚል አባዜ ተጠናውተው ዜጎችን በመግደል በማሰር እና በማሳደድ በማፈን እና በማሸበር ራሳቸው አርቅቀው ያወጡትን ሕግ እንኳን ማክበር ሳይችሉ የሕግ የበላይነትን በማቅለጥ ወደ አምባገነንነት የለወጡት የሕወሓት መራሽ ገዢ መደቦች በውስጣቸው በፈጠሩት የራስ ሽብር እና ፍርሃት የመብት ጥያቄዎችን በሃይል ለማድበስበስ እና ለማክሰም የሌት ተቀን ደፋ ቀናቸው ተያይዘውታል::

ወያኔ ራሱ የፈጠረው በውስጡ የተንሰራፋውን ፍርሃት እና ሽብር ለማቀዝቀዝ አለመቻሉ የሕዝብ ልጆችን ለማሸበር እየተጠቀመበት ቢሄድም በበለጠ የራሱ ችግር እየተሟሟቀ እና እየሰፋበት ካለበት ደረጃ ላይ ሆኖ የተለያዩ ሰበቦችን በመፍጠር መራወጡን ቀጥሏል:: በፓርቲያዊ መዋቅር የተከሰተበት ችግር በደህንነቱ እና ሰራዊቱ ውስጥ እየጋለ የመጣው ጥያቄ እና መልስ ፍለጋ ሕዝቦች ለስርአት ለውጥ የሚያደርጉት ትግል የወያኔን ማንነት በገሃድ እያጋለጡት ይገኛሉ:: በሃገር ውጥ እና በውጪው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የፈጠሩት ጫና ስለሚያደናብረው ብቻ ወያኔ ያሌለበትን ሰላማዊ እና ከፖለቲካ ነጻ የሆነ ሕዝባዊ ድርጊቶችን ሁሉ ሽብር እያለ መፈረጁን ተያይዞታል;ይህ ደግሞ ፍርሃት የወለደው ፖለቲካዊ እብደት ነው::

አሁን እያንዳንዳችን ኢትዮጵያውያን ይህ በፍርሃት እና በፈጠራ ሽብር የሚደናበረውን ወያኔን በማስወገድ የሕግ የበላይነት እና የሕዝቦች ነጻነትን የምናረጋግጥበት ወቅት ላይ ነን::ወያኔ በፖለቲካ እብደት ውስጥ መሆኑን አውቀን ልዩነታችንን በማቻቻል ከነግሳንግሱ ልንቀብረው ይገባል::ሕዝብ ፍትህ ተጠምቷል:: ሕዝብ ነጻነትን ይፈልጋል:: ሕዝብ ከፖለቲካ ጫናዎች ተላቆ አንገቱ ቀና አድርጎ መኖርን ይሻል:ሕዝብ ከኑሮ ውድነት ተላቆ በተሻለ የኢኮኖሚ ሕይወት በመኖር ጥቂት የዘር ማንዘር ሃብታሞችን በማጥፋት በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ማእቀፍ ውስጥ በመኖር ድህነትን ማጥፋት ይፈልጋል:: ስርአቱ የፈጠረው ወጣቱን ትውልድ የመግደል የማህበራዊ ዝቅጠት አባዜ በማቆም ለሃገር እና ወገን ሃሳቢ ንቁ ትውልድ እንዲገነባ ሕዝብ ይፈልጋል... ወዘተ..ይህ ሁላ የኛ የኢትዮጵያውያን የለውጥ ፍላጎት እንዲሜላ በሕዝባዊ እምቢተኝነት እና አመጽ የምንታገልለት አበይት ጉዳይ ነው::ለዚህ ስኬት ደሞ በጋራ በመቆም የዜግነት ግዴታችንን በመወጣት በወያኔ ፍርሃት እና ሽብር የተፈጠረውን የመብት ጥያቄዎችን ማድበስበስ እና የነጻነት ንጥቂያ እኩይ ተግባራትን ልናከሽፍ ይገባል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬