የፖለቲካ ጫና እና የኢኮኖሚ ድቀት አብዮቱን ማፈንዳቱ አይቀርም።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) :-ኢትዮጵያ ሃገራችን በተረገሙ ሰይጣኖች የሕወሓት ባለስልጣናት አጅ ከገባችበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያውያን በሃገራችን ባዳዎች በመሆን በፖለቲካ ጫና እና በኢኮኖሚ ድቀት አየተንገላታን አንገኛለን። ከግድያ አስከ አስር የሚደርሱ ኣንድ መንግስት በዜጎቹ ላይ የማይፈጽመው መንግስታዊ ሽብር አየተፈጸመብን ከመሆኑም ባሻገር በአሸባሪነት ታርጋ ከፖለቲካ መሪዎች እስከ ሃይማኖት መሪዎች ከጋዜጠኞች አስከ ጦማርያን ድረስ በማወቅ ይሁን ባለማወቅ ብሶት ኣደባባይ ያሰለፈቻው ሰብአዊ መብት የሚያንገበግባቸው ወዘተ ዜጎች ታስረዋል ተሰደዋል ይህም እድገት ኣሳይቶ በኣደባባይ ተገድለዋል። 

የፖለቲካ ጫናው የወለደው መጭበርበር የፈጠረው የኢኮኖሚ ድቀት በዜጎች ሕይወት ላይ የማይሽር ጠባሳ ትቶ እያለፈ ነው።ሕዝቡ በዕለት ኑሮው የሚያጋጥመውን አንገብጋቢና ጊዜ የማይሰጥ ችግር በገሃድ ኣግጥጦ እየታየ ዝምታን በመምረጥ የግል ኪስን ብቻ ለመሙላት ባለስልጣናት በዘረፋ ላይ ተሰማርተው ጥቂት የደለቡ ቱጃሮች ሲፈጠሩ በርካቶች ለድህነት ተዳርገዋል።ጥራቱን ባልጠበቀ ብልጭልጭ ነገር ልማት በሚል ሽፋን ሕዝብ ለማታለል መሞከር ወንዝ አንደማያሻግር ሕዝቡ መንቃቱን በግልጽ አየተናገረ ነው።የሃገሪቱ የውጪ ምንዛሪ ከመዘረፉም በላይ የተረፈዉን ምንዛሬ በሕዝብ መሰረታዊ ፍጆታ ለማስመጣት ከማዋል ይልቅ እንደ መጠጥ እና ሲጋራ የመሳሰሉ ትውልድ ገዳይ ሸቀጦችን በማስገባት በኢኮኖሚ ድቀቱ ላይ የማህበራዊ ቀውስ በመፍጠር በበደል ላይ በደል የከሳው መግደል የሚል አኩይ ድርጊት ሕዝብ ላይ አየተፈጸመ ነው።

ስርአቱ ለየመስሪያ ቤቱ የሚመድበውን በጀት ለብዝበዛ በሚመቸው መልኩ ኣላስፈላጊ ግዢዎችን በማድረግ ከልክ በላይ የሕዝብን ገንዘብ በማባከን እንዲሁም ከሃገር ውስጥ ባለሃብቶች መግዛት የሚቻለውን ለዘረፋ በሚመች መልኩ የውጪ ምንዛሪ በማሸጋገር ወጣቱ በሃገሩ ስርቶ አንዳይኖር የስራ ኣጥነት እንዲሰራፋ በማድረግ በሃገሪቱ ላይ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍተኛ ድህነት እንዲፈጠር ተደርጓል።በሃገራችን ላይ አየተፈጸመ ያለው ከባድ መንግስታዊ ሽብር ደባ የፖለቲካ ጫና እና የኢኮኖሚ ድቀት አብዮቱን ማፈንዳቱ አይቀርም።የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል ለውጡ ሊመጣ የሚችለው በሕዝባዊ እምቢተኝነት እና ኣመጽ መሆኑ እውን የሆነበት ወቅት ላይ ስለሆን እያንዳንዳችን ለነጻነታችን መረጋገጥ በኣንድነት ልንተም ይገባል።