የበሰበሰውን ስርአት ለማስወገድ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጉልህ ድርሻ ይጠይቃል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) :- እኛ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ነጻነት ተጠምተናል::...ፍትህን ናፍቆናል::..ሰላማችን ደፍርሷል::...ብደረድራቸው ሊያልቁ የማይችሉ እና በምናውቃቸው የጭቆና ሰቆቃ ውስጥ እየተንገሸገሽን ነው::ይህ ደግሞ ሁሉ ሰቆቃ ፈጣሪው እና ድርጊቱን የሚፈጽመው በስልጣን ላይ ያለው ቡድናዊ አምባገነን መንግስት ነኝ የሚለው የማፊያ ቡድን መሆኑ የሚካድ አይደለም::ይህ ቡድናዊ አምባገነን በዲሞክራሲ ሽፋን በወረቀት ሕጎች ከለላ በኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ የሆነ የአካል እና የስነልቦና ጉዳይ በማድረስ ላይ ይገኛል::የውስጥ ችግሮቹ በፈሉ ሰአት ሁሉ መበስበሱ እያገጠጠ ሲወጣ የዜጎችን መብት እና ነጻነት በመግፈፍ ከባድ ሽብር እና ወንጀል በመፈጸም ላይ ስለሚገኝ ይህንን የበሰበሰ ስርአት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ገርሥኦ ለመጣል የእያንዳንዳችን ጉልህ ድርሻ ይጠበቅብናል::

ሕዝቦች ትክክለና ፍትህ እና ነጻነት እስካላገኙ ድረስ አንድ ሃገር ሰላም ሊኖረው ስለማይችል የተነጠቀ መብቱን ለማስመለስ ማንነውም ዜጋ ቢታገል ፍትሃዊ መሆኑ ይታወቃል::እያንዳንዳችን ኢትዮጵያውያን ለመብታችን እና ለነጻነታችን የምናደርገው ትግል በሙሉ የሌላውን መብት እስካልነካን ድረስ ፍትሃዊ መሆኑ ሃቅ ነው::ፍትሃዊ ትግል ሕዝቦች ከጨቋኝ አገዛዝ ነጻ ወጥተው ፍትህን እና ነጻነት በማረጋገጥ የሃገር ሰላም የሚያሰፍኑበት ስልት ነው:: እኛም ኢትዮጵያዊያን የበሰበሰውን የወያኔን ስርአት ለመጣል የምናደርገው ትግል ፍትሃዊ መሆኑ የአደባባይ እውነት ነው::ይህ ቡድናዊ የወያኔ አምባገነን የማፍያ ጁንታ እስካልወደቀ ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ዲሞክራሲ ፍትህ እና ነጻነት ይገኛል ማለት ዘበት ነው::

ይህ ውስጡ በስብሶ በፕሮፓጋንዳ ብቻ እየኖረ የሚገኘው የወያኔ ስርአት ለመጣል እያንዳንዳችን ለሃገራችን እና ለኛነታን ነጻ መውጣት ያበረከትነውን አስታውጾ ራሳችንን ልንጠይቅ የሚገባን ወቅት ላይ መሆናችንንን አውቀን ለሃገሬ እና ለወገኔ እንዲሁም ለራሴ መብት እና ነጻነት መከበር ምን ሚና አለብኝ? ምን ተወጣሁ? ምን ይጠበቅብኛል? ወዘተ የሚሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ለራሳችን ጠይቀን ራሳችን ተግባራዊ እና አርኪ ምላሽ ልንሰጥበት ይገባል::ይህን ጊዜ የበሰበሰውን ስራት ለመጣል እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ድርሻችንን እንረዳዋለን::በተገቢው የትግል ስልት ሁሉ የድርሻንን መወጣት ከቻልን ለፍትሃዊ ትግል ስኬት እና ለነጻነትና ለፍትህ ታላቅነት መረጋገጥ የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ::በበሰበሰ ነገር ውስጥ መኖር ይብቃን::ጊዜው የለውጥ መሆኑን አንዘንጋ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬