አትኩሮታችን ከፖለቲካ ጥላቻ ወጥቶ ሕወሓትን በመደምሰስ ላይ መሆን አለበት(እውነትን የመዋጥ ግዴታ)

Minilik Salsawi በለውጥ ሃይሎች መካከል ልዩነቶች አሉ ይኖራሉ ይህ አዲስ ነገር አይደለም::ልዩነት ለዘላለም ይኑር::የለውጥ ሃይሉ በርካታው የፖለቲካ ብስለት ስላለው ይህን ያህል የትግሉ ችግር ባይሆንም አልፎ አልፎ በሚከሰቱ ክስተቶች ቀጥታ የፖለቲካ ጠጁን አይበጠብጥብ ባልበሰሉ እና እዚህ ግቡ በማይባሉ የገደል ማሚቱዎች ተጠቅሞ የፖለቲካ ጥላቻ ማራገብም ሌላው የትግሉ ጎታች አካል ነው::እያየን ያለነውም ይህንን ነው::እንዲህ ብላችሁ ጻፉ ከሚባሉ ጀምረው እንዲህ ብላችሁ ጻፉልን ብለው እስከሚታዘዙ የፖለቲካ አሽከሮች ተከበን ከፖለቲካ ጥላቻ መውጣት አልቻልንም::የፖለቲካ ባህል ለውጥ እና የጋራ ትብብር የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ መሆናችንን አንዘንጋ::በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ወሳኝ ወቅቶች ሳንጠቀምበት አምልጠውናል::

መታወቅ ያለበት ግዴታ ቢኖር በአሁኑ ወቅት ትግሉ ያለው በሕወሓት ዘረኛ ጉጅሌ መንግስት እና ነጻነትና ለውጥ በሚፈልገው የኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል መሆኑ የማይካድ ነው::ሕወሓት በተባለው የማፊያ ድርጅት ውስጥ ያለው የስልጣን ሽኩቻ ለለውጥ ሃይሉ የሚጠቅመው አሊያም ለወገን የሚፈይደው አንዳችም ነገር የለም::ለሁላችን የሚጠቅመን አሊያም የሚፈይድልን በፖለቲካ ጫና እና በኑሮ ውድነት እያንገላታን ያለውን የሕወሓት አገዛዝ መደምሰስ ብቻ ነው::ታዲያ አትኩሮታችን የት ላይ እንዳለ ራሳችንን መጠየቅ ግድ ይለናል::ሕወሓት የተባለው ድርጅት ተሰብስቦ አውርቶ ተመራርጦ ወደ ኢሕኣዴግ ስብሰባ መቶ ያንኑ ደግሞ ተደላድሎ እያለ እያለ ይቀጥላል::እኛ ደሞ ከዚህ ሂደት ውስጥ ተለቅመው የሚወጡ ሆኖም የጡዘት ወሬ የሆኑ ጉዳዮችን ይዘን እናላዝናለን::ሃገር ትዘረፋለች ህዝብ ይታሰራል ይገደላል እንሰድዳለን ይህ ሁሉ ሲሆን የፖለቲካ አሽከሮቻችንን ይዘን በፖለቲካ ጥላቻ ታጅበን በያለንበት ሆነን እናላዝናለን::አትኩሮቶቻችንን አለማወቃችን የምንህድበትን መንገድ እየተንፏቀቅን እንድንሄዽ አድርጎናል::እውነትን የመዋጥ ግዴታ አለብን::

የሕወሓትን የማዘናጊያ አጀንዳ ከማራገብ አንድ ሃገር አንድ ትግል በአንድ ሕዝብ የሚለውን የጋራ ትስሥር ይዘን ታሪክ ልንሰራ ይጠበቅብናል::በሕወሓት ውስጥ ያልተከሰቱ እና ያሌሉ የፖለቲካ ጡዘቶችን በምናባችን እና በጭረቶች እየፈጠን እያጋነንን ብናወራው ለትግሉ ምንም ፋይዳ የለውም::ትግሉን ሁሉ ለድርጅቶች መተው የለብንም እኛም እንደዜጋ ማድረግ ያለብን ሁሉ ማድረግ አለብን::ለውጥ እስከፈለግን ድረስ በየምናምኑ እየተወሸቅን ከምናወራ በተግባራዊ ስራዎች ላይ መሳተፍ እና ለነገው ትውልድ ታላቅ ስራ የመስራት ግዴታ እና ሃገራዊ ሃላፊነት እንዳለብን ልናውቅ ይገባል::ትግሉ በስራ ላይ ውሎ የተለያዩ የለውጥ ሃይሎች ካለው አገዛዝ ጋር በተለያዩ መንገዶች እየታገሉ ይገኛሉ:አትኩሮታችን መሆን ያለበት ሕወሓትን በመደምሰስ እና ለትግሉ የሚሆኑ መረጃዎችን በመለዋወጥ ላይ መሆን አለበት:ከኔ በላይ አዋቂ የለም በሚል ባልበሰለ የፖለቲካ ባዶነት ውስጥ እየዋኙ የሚደፈቁትን መመልከት የለብንም ::በሕዝቡ ላይ ጫና ከሚያሳድሩ እና የፖለቲካ ሃይል ሚዛን ከሚሰቅሉ መረጃዎች ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል::ትግሉን አስፍተው ሕዝቡን የሚያነሳሱ የሚያደራጁ የሚያታግሉ ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል::እንንቃ::አትኩሮታችን በሕወሓት የስልጣን ሽኩቻ ላይ ሳይሆን ሕወሓትን በመደምሰስ ላይ መሆን አለበት::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬