የሃይል ሚዛን በፕሮፓጋንዳ ጡዘት ውስጥ የሚኖረውን የፖለቲካ ሚና ልናውቅ እንገደድ !!!

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) : በማይጠቅም የጠላትን ሃይል የማጋነን ስራ ላይ ከመጠመድ የራሳችንን የትግል ስራ በመስራት ሕዝብን በማስተባበር በመቀስቀስ እና በማደራጀት ላይ ያተኮሩ አመርቂ ስራዎች ብንሰራ ማንን ገደለ?ስለ ሕወሓት መተካካት እና ስለ ብአዴን መሰነባበት ከምንደሰኩር ትግላችንን አጠናክረን በጋራ በአንድነት ሆነን ለሚፈናቀለው ለሚታሰረው እና ለሚገደለው ሕዝባችን እንድረስለት::የጠላቶቻችንን ስብሰባ እያጋነንን እያሞካሸን ሲለን እያሰፋን እያንጠራራን እና እየሰቀለን የምናወራበት ጊዜ ላይ አይደለንም::ደግሜ እናገራለሁ ጠላቶቻችንን የምናንበረክክበት እና በሚገባቸው ቋንቋ የምናናግርበት ጊዜ ላይ ነን::የሚገባን ካለን::ሰሞን ሰሞን እየጠበቁ በተገኘው አጀንዳ ላይ ማጨብጨብ ይቁም!!!

አርከበ ተመለሰ ተተካ አዲሱ ተሰናበተ ለለውጥ ሃይሎች ምንም የሚጠቅም አጀንዳ አይደለም::የመከላከያ ባለስልጣኖች የደህንነት ባለስልጣኖች የአንድ ፓርቲ አባል እና የስብሰባ አካል ሆነው በአይናችን እያየን ባለንበት በዚህ ሰአት ላይ ሕዝባዊ መንግስት ሕዝባዊ የመከላከያ ሰራዊት ብሄራዊ የደህንነት ተቋም እንዲኖረን ማድረግ የምንችለው በኛው በራሳችን ትግል እንጂ የሕወሓትን ፕሮፓጋንዳ በማጦዝ አይደለም::የሃይል ሚዛን በፕሮፓጋንዳ ጡዘት ውስጥ የሚኖረውን የፖለቲካ ሚና ልናገናዝብ ግድ ይለናል::ስለ ሕወሓት መተካካት ስለ ሽማግሌዎቹ እና ዘራፊዎቹ ብኣዴን አመራሮች መሰናበት ባወራ አዲስ ትኩስ የፖለቲካ እድል በፕሮፓጋንዳው መስክ ፈጥረን የሃይል ሚዛኑ እንደተጠናከረ የሚያገጥ ስራ እየሰራን እንደሆነ አንዘንጋ::ስለ ሕወሓት ስብሰባና ጉዳይ በምናወራበት ጊዜ ሁሉ ሕዝብ ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ተጽእኖ ከግንዛቤ ልናስገባ ይገባል::ሕዝቦች በስቃይ ወላፈን እየተመቱ ባለበት በዚህ ወቅት ትግሉን አጠናክሮ ወያኔን መደምሰስ ሲገባን የቅጥረኞቹን የሪፖርተር እና መሰሎቹን ስራ ማራገብ ለትግሉ የሚፈይደው አንድም ነገር የለም::

የሕወሓት ማፊያ ቡድን ወራዳ ነው::የሕወሓት ማፊያ ቡድን ከምድረገጽ መጥፋት አለበት::ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳትኖር የሚመኝ ይህ አሸባሪ ድርጅት ለማንም አይበጅብ::ብናወራለት ተተካኩ ተባሉ ተፋቀሩ ብንልለት ምም አይበጅም::የሚበጀን ነገር ቢኖር ትግሉን በአራቱም አቅጣኛ በማጠናከር ሕዝቦችን በማስተባበር በመቀስቀስ እና በማደራጀት ይህንን ከይሲ የማፊያ ቡድን ማስወገድ ብቻ ነው:: እስኪ ራሳችን እንጠይቅ? ስንቶቻችን ነን ለራሳችን አላማ እና ግብ ጠላቶች የሆንን?በወሬ ናዳ እያሽካለልን ትግሉን የጎተትን?እርስ በራሳችን በተራ የመንደር ወሬ ተቧድነን የምንወነጃጀል? ከትግል ይልቅ በሃሜት እና በፍረጃ ላይ በፕሮፓጋንዳ ላይ የተተከልን ስንቶቻችን ነን? ከዚህ አይነቱ ጋሬጣ ራሳችንን አላቀን ሕዝብን አስተባብረን የሕወሓትን ጉጅሌ አገዛዝ በተገኘው መንገድ ሁሉ በጋራ እና በአንድነት ሆነን መደምሰስ አለብን ? ከፕሮፓጋንዳ ጡዘት እንላቀቅ!!!የሃይል ሚዛን በፕሮፓጋንዳ ጡዘት ውስጥ የሚኖረውን የፖለቲካ ሚና ልናውቅ እንገደድ !!! ( ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬ )