የደብል ዲጅቱ የኢኮኖሚ እድገት ፕሮፓጋንዳ እርቃኑን እየወጣ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - 11% የተባለ የኢኮኖሚ እድገት ሕዝቡን ከድህነት ሊያወጣ ቀርቶ ጭራሽ የደሃ ደሃ የሚል አዲስ የቋንቋ ስያሜ ወልዷል::የኑሮ ውድነቱ እያሻቀበና ህዝቡን እያስደነገጠ ነው፡፡አጠቃላይ የምግብ ፍጆታዎች ዋጋቸው እጅግ አሻቅቧል፡፡በሚቀጥሉት ስድስት ወራት የኢትዮጵያ ሕዝብ በከፍተኛ ድህነት እንደሚመታ የሚጠቁሙ መረጃዎችን ተከትሎ የወያኔ ባለስልጣናት የደብል ዲጂት የኢኮኖሚ እድገቱ እንዳልተሳካ በመናገር ላይ ናቸው:: የኑሮ ውድነቱ ችጋር/ድህነት ችጋሩ ደግሞ ጐጠኛ አስተሳሰብና አሠራርን ልቅ ሙስናን የፍትህ እጦትን በተግባር ፈጥረዋል::የፖለቲካ ሥርአቱም አደጋ ላይ መውደቁን በተግባር እያየን ነው::ከዚህ የኑሮ ውድነት መገላገል የምንችለው ከድህነት አለንጋ ራሳችንን ማዳን የምንችለው በአንድነት ሆነን የበሰበሰውን የወያኔን ስር አት መደምሰስ ስንችል ብቻ ነው::ንግዱን በሞኖፖል ተቆጣጥሮት በመንግስት የገበያ ተቋማት ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ወያኔ ራሱ የገንዘብ አቅርቦት እና የዋጋ ትንበያዎችን በማስፋፋት በሃገሪቱ ላይ የኑሮ ውድነት እንዲስፋፋ በጭፍን እየሰራ ይገኛል::ስለሃገር እና ስለ ህዝብ ደንታ የሌለው ይህ ስርአት ከልክ በላይ ገንዘቦችን በማተም እና በማሰራጨት መንግስት ከባንኮች በመበደር የውጭ ምንዛሬን በማከማቸት ወዘተ የሃገር ኢኮኖሚ ከሚችለው በላይ የኢኮኖሚ ውዥንብሮችን በመፍጠር በልማታዊ መንግስትነት ስም የኑሮ ውድነት እንዲንሰራፋ በማድረግ ከፍተኛ ችግርን ለህዝብ አሸክሞ በህዝብ ትከሻ ላይ በመቀመጥ እኩይ ብዝበዛውን እያደረገ ይገኛል::
የወያኔ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በሃስት ፕሮፓጋንዳ ላይ ብቻ የተገነባ በመሆኑ ባለስልጣናቱን በፊት ለፊት እያጋፈጠ ይገኛል::የሃገሪቱን ኢኮኖሚ በምክር ይዘውራሉ የሚባሉት የወያኔ ኢኮኖሚስቶች ተብየዎች በሃገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እንዳሌለ በመናገር ላይ ናቸው::ይህ ደሞ የፈጠረው ራሳቸው በሚያራምዱት የሙስና እና የዘረፋ ተግባራት ነው::የሃገሪቱ ጂዲፒ እያሽቆለቆለ ከመህዱም በላይ የማኑፋክቸሪው ዘርፍ አውላላ በረሃ ላይ ካለደጋፊ ተንጋሎ ቀርቷል::ላኪዎች ሆነው በተለያዩ የሃገር ውስጥ ምርቶችን በመላክ ላይ የተሰማሩት ወያኔዎች ከነዘመድ አዝማዶቻቸው ከሚልኩት እቃዎች የሚገኙትን የውጪ ምንዛሬዎች በዛው ሃገር ቤት ሳያስገቡ በውጪ ባንኮች መጨመራቸው እንዲሁም በተለያዩ ሻንጣዎች የተሞሉ የውጪ ምንዛሬዎችን ማሸሻቸው በሃገሪት ላለው የውጪ ምንዛሬ ካዝና ባዶነት ራሳቸው ተጠያቂ ናቸው::የኤክስፖርት ስራም ይሁን የውጪ ምንዛሬ ባዶነት መንስኤዎች ራሳቸው ባለስልጣናቱ ናቸው::የውጪ ንግድ ስራዎችን አቀላጥፎ በማካሄድ ሊገኙ የሚችሉ የውጪ ምንዛሬዎችን መመንተፍ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአገዛዙ ሰዎች ያልሆኑ ነጋዴዎች እንዳይሰሩ ጋሬጣ መፍጠር ሌላኛው የወያኔ ሌቦች ትልቅ ችግር ነው::
በሃገሪቱ የተከሰተው ድርቅ የዝናብ እጥረት ቢሆንም ችግሩ በሰው ሰራሽ መንገድ መከላከል እየተቻለ በውሸት እናእውነታን ልመሸፋፈን በመሞከር ወገንን ለከፋ አደጋ እያዳረጉ ያሉት እነዚሁ ባለስልጣናት ናቸው::በምግብ እሕል ራሳችን ችለናል በሚል የውሸት ፕሮፓጋንዳ ለተራቡ ለተጎዱ ወገኖች የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አለ በማለት ያሌለውን እንዳለ ያልተሰራውን እንደተሰራ በማድረግ በባዶ ሜዳ የሃሰት ንግግሮችን በመደስኮር ከሕዝብ ለመደበቅ ቢሞክሩም ተጋልጠዋል:: ተጠባባቂ የምግብ ዝግጅት እንኳን ሊኖር ይቅርና ከአመት በፊት እንደሚመጣ በጥናት የታወቀውን ድርቅ እንኳን ሊያስተካክል እና ሊቋቋም የሚንል ሃይል አልተዘጋጀም::በምግብ እህል ራሳችን ችለናል እየተባለ ከ15 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ሲራብ የአለም ሚዲያዎች ሲቀባበሉት ወያኔ ግን ክዶታል ይህ የሚያሳየው የአገዛዙ ፖሊሲዎች ብልሹ እና የተጭበረበሩ መሆናቸውን ነው::ሃይለማርያም ደሳለኝ በምግብ እህል ራሳችንን አልቻልንም የሚሉት ይህ ነው እንግዲህ በግብርና ላይ የተመሰረተው ደብል ዲጂት እድገት እና የአንድ አመት ድርቅ ሊቋቋም ያልቻለው ኢኮኖሚ::
ይህ ሁሉ እና ተመሳሳይ ያልተጠቀሱ ጉዳዮች ተደማምረው በገሃድ ይወያኔን ማንነት እያሳዩን ነው::የደብል ዲጂት እድገት እያለ ወያኔ የሚያላዝንለት የ11% የኢኮኖሚ እድገት ሕዝብን ለድህነት ከመዳረጉም በላይ የደሃ ደሃ የሚባል አዲስ የቋንቋ ስያሜ ወልዷል::የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ሕዝብ ከማገልገል ይልቅ አገልግሎታቸውን አቋርጠው በሕዝብ ላይ ሲያሾፉ ነው የሚውሉት::ለዚህ ሁላ መፍትሄው ያለው የወያኔ አገዛዝ አስወግዶ በአዲስ ሕዝባዊ መንግስት መተካት ብቻ ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬