በተገኘበት አብሮ መውቀጥ ለምን ? በነፈሰበት መንፈስ እስከመቼ ? በሚገባቸው ቋንቋ እናናግራቸው!!!

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) እስክመቼ ድረስ እያወራን እንደምንኖር አላውቅም::ይህን ሰሞን የሕወሓትን ስብሰባ ተከትሎ አስር ጊዜ የባለስልጣኖቹን ስም በመጥራት ወሬ እያጣፈጡ የሚነግሩን ተቃዋሚ ነን ባዮች በተገኘበት አብሮ መውቀጥ በነፈሰበት አብሮ መንፈስ ለምን? እስከመቼ? ልላቸው ወደድኩ::አሁን ጊዜው የአርከበ ምንቸውት ገባ የአዜብ ምንቸት ወጣ እያልን የሕወሓትን ጉዞ የምንደሰኩርበት ሳይሆን በሚገባቸው ቋንቋ የምንነግርበት ጊዜ ላይ መሆናችንን አንዘንጋው:;እረ እስከመቼ ? እንንቃ !!!

የሃገሪቱን የማፊያ መንግስት በበላይነት የሚመራው ሕወሓት መሆኑ እሙን ነው:: ሕወሓት ከስሙ ጀምሮ እንደሚያሳየን ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን የማይተኛ ድርጅት ነው:: ከሕወሓት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን አሊያም የሕዝብ ስልጣን መጠበቅ ከእባብ የእርግብ እንቁላል እንደመጠበቅ ነው::ይህ ድርጅት ከበረሃ ጀምሮ ይዞ የመጣውን ጸረ እትዮጵያ አቋሙን ለመተግበር ሃገርን እና ሕዝብን አደጋ ውስጥ ጥሎ ከፍተኛ የሆነ ወንጀል በመስራት ላይ ነው:: አመራሮቹም ቢሆኑ የሚሰሩት ግፍ ዘረፋ እና ይቅር የማይባል ተንኮል ሕዝቡን ለድህነት ሃገርን ለውርደት ዳርጓል::

የሕውሓት አመራሮች ተናከሱ አልተናከሱ ተተካኩ አልተተካኩ የሕወሓት አመራሮች ተፋቀሩ አልተፋቀሩ ዋሹ አልዋሹ ለሃገራችን እና ለሕዝባችን የማይተኙ እባቦች መሆናቸውን ልናውቅ ይገባል::ማወቅ ያለብን እነዚህን ተኩላዎች ማስወገድ ብቻ ነው በሚገባቸው ቋንቋ ልንነግራቸው ይገባል ለአለም የሚሰሩትን ግፍ በሎቢ ልናዳርስ ይገባል::ስለ ሕወሓት የፓርቲ ስራዎች ከምናፏጭ ይልቅ ለትግሉ መሆን ያለበት ተግባር በመፈጸም ሕወሓቶችን በምናስወግድበት ላይ ሁሉ ልንረባረብ ይገባል::