ተጨማሪ ሕዝብ የረሃብ አደጋ ስለተጋረጠበት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል::

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ቢሮ (UNOCHA)ባወጣው አዲስ ሪፖርት እንዳመለከተው በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ከተራበው በድርቅ ከተጎዳው ሕዝብ በተጨማሪ በዚህ ወር ውስጥ ብቻ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የረሃብ አደጋ ተጋርጦበት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው አትቷል::በግማሽ አመት የሚያስፈልጉ የሰብአዊ እርዳታዎችን በተመለከተ የኢትዮጵያን መንግስት እና ለጋሾች በተገኙበት ይህ ሪፖርት ይፋ ሆኗል::

ሪፖርቱ እንዳለው ለምግብ እርዳታዎች እና ምግብ ነክ ላልሆኑ እርዳታዎች እስከ 386 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ እና እስካሁን 158 ሚሊዮን ዶላር በግማሽ አመት እንደተገኘ አሳውቋል::ለመጪው ስድስት ወራት ብቻ የሰብአዊ እርዳታ ፈላጊው እጅግ ከሚፈለገው በላይ እንደሚጨምር እና በመጀመሪያው 6 ወራት እንደተደረገው ሁሉ የዝናብ እጥረት በተከሰተባቸው ቦታዎች ሁሉ የምግብ እርዳታዎችን ለማድረግ የታለመ እንደሆነ ጠቅሶ የተረጂዎች ቁጥር እንደሚጨምር በሪፖርቱ ገልጿል::Minilik Salsawi