የፖለቲካ አስተዳደሩ ካልተወገደ ድህነትን እና የኑሮ ውድነትን መቅረፍ አይቻልም::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - የኑሮ ውድነትና የፖለቲካ አስተዳደር እጦት ተወራራሽ ናቸው:: በሃገሪቱ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ከ2008 መግቢያ ጀምሮ በተለያዩ ምግብ ነክ በሆኑ እና ምንብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ በነሃሴ ወር ከጀመረው ጭማሪ በላይ የሆነ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ ከ7 በመቶ በላይ እንደሚከሰት ጥናቶች ጠቁመዋል:: እንደኔ እንደኔ አዲስ አመት ከመናፈቅ አዲስ ስርአት መናፈቅ ከአዲስ ማእረጋችን የደሃ ደሃ ክሚለው ወደ ላይ አንድ እርከን ከፍ ብለን የተሻልን እንሆናለን ለምን ከተባለ አዲስ ስርአት አዲስ ነገር ይዞ መምጣቱ ስለማይቀር ቢያንስ ስለ ነጻነታችን እና መብታችን ለየት ያለ ግንዛቤ ስለሚኖረን አዲስ ሕይወት ለመፍጠር ብዙም አያስቸግርም::እርግጥ ሕዝቡ ታማኝነቱን የሚጥልበት የፖለቲካ አመራር ባለመኖሩ ዝምታን መምረጡ እሙን ነው::ያለው አምባገነን የወያኔ ጉጅሌ ቢያንገፈግፈውም የሕዝቡ ትእግስት ግን እየተሟጠጠ የባለስልጣናቱም መፍረክረክ እየሰፋ እየተስፋፋ መጥቷል::በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባው የወያኔ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሕዝቡን ለድህነት አቀባብሎ በመስጠት የድሃ ደሃ የተባሉ በርካታ ባዶ እጅ ዜጎች እንዲፈጠሩ ጥቂት ቱጃሮች በሃገሪቱ እንዲሰራፉ አድርጓል::
Minilik Salsawi's photo.
በሃገራችን የተከሰተው ድርቅ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የሆነ የምግብ ዋጋ መናር ከመከሰቱም በላይ አውዳመቱን አስታኮ ከጀርባቸው የወያኔ ባለስልጣናትን ያዘሉ ነጋዴዎች በምግብ ዋጋዎች ላይ ከነሃሴ መግቢያ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ በማድረግ ሕዝቡን ለስቃይ ዳርገውታል::ብነሃሴ ወር ምጀመሪያ ጀምሮ በአፋር እና አማራ በኦሮሚያ እና አዲስ አበባ እንዲሁም ብደቡብ አንዳንድ አከባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የምግብ ዋጋ ጭማሪዎች ታይተዋል::11.6 በመቶ ጭማሪ ያሳየው የምግብ ዋጋ እና በ8.9 በመቶ ጭማሪ ያሳየዩት ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች ሕዝቡን በኑሮ ውድነት መሃል አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የወያኔው አስተዳደር አሁንም ስህተቱን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደለም::አውዳመቱን አስታከው የሚሸጡ ሸቀጦች ከፍተኛ ጭማሪ ሲያሳዩ ለአውደአመቱ የማይፈለጉ እቃዎች ደግሞ ወርደው ታይተዋል::

የኑሮ ውድነት የአንድ ሃገር የፖለቲካ አስተዳደር መበላሸት አካል መሆኑ ይታወቃል፡፡ የወያኔው ስርአት የሚያራምደው ቅጥ ያጣ የንግድ አተገባበር ባለስልጣኖች እና ወገኖቻቸው ከፈጠሯቸው ጥገኞች ጋር በማበር ከፍተኛውን የዘረፋ እና የንግድ ሂደቱን የመቆጣተር ስራዎችን እየሰሩ ነው:: አምባገነኖች ቡድን ፈጥረው የገነቡት የቡድን ዝርፊያዎች እና ጐጠኝነት ሙስና/ጉቦ እና የፍትህ እጦት በኢትዮጵያ እየተንሰራፋ ለመጣው የኑሮ ውድነት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ የኑሮ ውድነትና የፖለቲካ አስተዳደር እጦት ተወራራሽ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡የፖለቲካ አስተዳደሩ ካልተወገደ ድረስ የኑሮ ውድነትንም መቅረፍ የማይቻለው ከዚህ ተወራራሽነት መነሾ መሆኑ አይካድም::የፖለቲካ አስተዳደሩ መወገዱ በሂደት ስራዎች የኑሮ ውድነትን ሊቀርፍ ይችላል::የወያኔው አገዛዝ የሚያራግበው የ11 በመቶ አመታዊ የኢኮኖሚ እድገት በገሃዱ እውነታ በሚታየው ድህነትና ጉስቁልና እርቃኑን የወጣ ስለሆነ የአገሪቱ ፈታኝ እና ዋነኛው ችግር የኑሮ ውድነት መሆኑን ሁላችንንም ሊያሳስበን የሚገባ ጉዳይ ነው::የወያኔው ስርአት በሚፈጥረው ውዥንብር ነጋዴውን እና ሸማቹን ለማናከስ በሚፈጥረው ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ በሌላ በኩል በአለም የምጣኔ ሃብት መዋዠቅ ነው ቢል የራሱን ስህተቶች በመደበቅ የተንኮል መርዞችን ቢረጭም የሚቀበለው እና የሚያምነው አይገኝም:: የኑሮ ውድነት ከመስፋፋቱም በላይ የምግብ ዋጋዎች ንረት እና የአላቂ እቃዎች ከአቅም በላይ ዋጋ መጨመር ዝቅተኛውን የህብረተሰብ ክፍል ከመጉዳቱም በላይ በመካከለኛ ኑሮ ላይ ያለውን ህብረተሰብ ወደ ዝቅተኛው በመቀላቀል ለድህነት ዳርጎታል::ስለዚህ የወያኔን የፖለቲካ አስተዳደር ማስወገድን ከቻልን የኑሮ ውድነቱ ለመቅረፍ ጊዜ የማይወስድብን መሆኑ እሙን ነው::ሁላችንም ወያኔን ለማስወገድ እንረባረብ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬