ሕወሓት እና አለቅላቂዎቹ ስለኢትዮጵያዊነት ሲነሳ ያቅለሸልሻቸዋል:ኢትዮጵያዊነት በህዝብ ልብ ውስጥ ላይወርድ የነገሰ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - ባለፉት 20 አመታት ሁላችን አንድ የታዘብነው ጉዳይ አለ::ስለኢትዮጵያዊነት ጠንካራ አቋም ያላቸው ስለሃገር የፖለቲካ ይሁን የኢኮኖሚ አንድነት የማህበረሰብ ትሥሥር ታላቅ አመኔታ ያላቸው ሰዎች ሲሰደዱ ሲወገዱ ሲሸበቡ አይተናል በአጠቃላይ አይፈለጉም:: የመንግስታዊ ፖለቲካ ጡዘት ውስጥ ሳይገቡ ስልጣን ሳይፈልጉ አሊያም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሳይደግፉ በነጻ አእምሮ ኢትዮጵያዊነትን ብቻ ስላቀነቀኑ ስለዘመሩ ካለምንም ድርድር ለካልቾ አሊያም ለእስር ሲልም ለስደት ከፍ ሲልም ለጥይት ተዳርገዋል:: ሕወሓት እንደዚህ አይነት ሰዎችን ሲያይ ያቅለሸልሸዋል:: ከብአዴን እና ኦሕዴዽ ውስጥ ደግሞ የሕወሓት አለቅላቂ ቅጥረኞች በፍጹም ድድብና ውስጥ ሆነው የታዘዙበትን ብቻ ሲያኩ አስተውለናል ይብልጡኑ ግን ከአንድ ፓርቲ ሕወሓት ብቻ የሆኑ ሰዎች በጸረ ኢትዮጵያዊነት ሲንጫጩ በስፋት እያስተዋልን ነው::

በኢሕአዴግ ድርጅቶች ውስጥ ዘለቅ ብሎ ተገብቶ ሲታይ ሙሉ በሙሉ ሕወሓት እና በከፊል የግንባሩ አባል ድርጅት ቅጥረኞች የሚያራምዱት የዘረኝነት (ጸረ-ኢትይኦጵያዊነት)አላማ ዝም ብሎ የመጣ አይደለም አንድም በባንዳዎች መጠመቅ ከቤተሰብ የተወረሰ ሌላም በፖለቲካ ጥላቻ እና ቅናት ላይ የተመረኮዘ ሲከተልም የበታችነት ስሜትና የግል ጥቅም(ሆዳምነት) ነው::በብዛት ይህ ነገር የሚታይባቸው በበታችነት ስሜት ተጠፍንገው በራስ መተማመን ስለሚያጡ ነገን የሚፈሩ ሰዎች የወለዱት የዘረኝነት አባዜ ነው:: የሕወሓት አባላት ቤተሰቦች አብዛኛዎቹ በባንዳነት ለቅኝ ገዢዎች አድረው የነበረ በበታችነት ሕይወት ተጠፍንገው ያደጉ በቅናት እና መርዘኛ ጥላቻ የተመረዙ መሆናቸው እሙን ነው::በኢትዮጵያዊነት አሊያም በሃይማኖታዊ ትውፊት ትኮትኩቶ ያደገ ሰው ሕወሓት ውስጥ የለም ::ቢኖርም ተበልቷል አሊያም ተባሯል ሲልም ስለሰብኣዊነት እና ማንነት በመናገሩ የተለየ ሃሳብ በማምጣቱ ተወግዷል::ምንጫቸውን የረሱ የጥቅም ተገዢ የሆኑ ጥቂቶች ደግሞ ለጊዜው ስለሚጠቀሙ ብቻ ትፋታቸው እየላሱ ጸረ ኢትዮጵያዊ አቋም ይዘው ተደባልቀዋል::

ሕወሓት ከተለያዩ ሕዳጣን ሰብስቦ ያሰለጠናቸው እና በአውሮፓ እና አሜሪካ ተቀምጥው ጸረ ኢትዮጵያ አቋም የሚያራምዱ ጥቂቶች የትም ላይደርሱ ቢፈራገጡ ምንም እንደማያመጡ ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ::የኢትዮጵያን መበጣጠስ የሚያልሙ ጥቂቶች የድህረገጽ ሹምባሾች ዲስኩራሞች ኢትዮጵያዊነትን በወሬ ሊንዱት አይችሉም::ኢትዮጵያዊነት እንኳን በየድህረገጹ ከሕወሓት እየተከፈላቸው ቡራ ከረዩ የሚሉ አይደለም ምእራባውያን እንኳን መናድ እንደማይችሉ የታወቀ ሲሆን ሞክረምው አልተሳካላቸውም:: ሕወሓት እንደአመጣጡ ቢሆን እስካሁን ያለማትን አገር ለመመስረት ቢያልምም እንደማይሳካ ስላወቀው ነው ስልጣኑን የሙጥኝ ብሎ የሚውተረተረው::አሁንም ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል::ስለ ኢትዮጵያ የሚያዜሙ ስለኢትዮጵያ የሚናገሩ ሁሉ ታላቅ ናቸው:: በሕዝብ ልብ ውስጥ ይነግሳሉ::ሕወሓት እና አለቅላቂዎቹ ስለኢትዮጵያዊነት ሲነሳ ያቅለሸልሻቸዋል::... እንዳቅለሸለሻቸው ወደ መቃብር ይወርዳሉ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬