የተደበላለቀበትና የማይናበበው የወያኔው አገዛዝና የሞተ የኢኮኖሚ ፕሮፓጋንዳቸው (ምንሊክ ሳልሳዊ)

".... አስረአንድ በመቶ እድገት አስመስግበናል::"የወያኔ የማያረጀው ሪፖርት

- "በየአመቱ 9.7 ከመቶ እድገት ከምታስመዘግበው ቻይና ልምድ ልመቅሰም እንፈልጋለን"ጠ/ሚ.ሐ/ማ

---"በጣም በጣም አሳሳቢ ነው::...ምንም እድገት ሳይታይበት በነበረበት እየረገጠ ነው።" አርከበ እቁባይ

---"አገሪቱ በውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ ጉድ ከመሆን የተረፈችው፣ በሁለት ምክንያቶች ነው ማለት ይቻላል ‘ዳያስፖራዎች’ ለቤተሰብ የሚልኩት ገንዘብ በመጨመሩና በአለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ በመቀነሱ። " አንድ ጸሓፊ/ በአዲስ አድማስ
 

- "ባለፉት 3 ዓመታት አቶ ኃ/ማርያም...ከአቶ መለስ የተሻሉ አፈጻጸሞችን በኢኮኖሚው ዘርፍ አስመዝግበዋል፡፡" ሪፖርተር ጋዜጣ
 

- "መንግስት የኤሌክትሪክ ሃይል ሸጦ በ9 ወር 35 ሚሊዮን ዶላር ሲያገኝ በሃገር ቤት መብራት አጥፍቶ ኢንዱስትሪውን በ6 ወር 40 ሚሊዮን ዶላር አክስሯል::" የኢኮኖሚ ባለሙያዎች
 

- "ኪራይ ሰብሳቢነት ለአደጋ አጋልጦናል::" የኢሕኣዴግ ሰዎችMinilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ለበርካታ አመታት የምንሰማው ኢትዮጵያ ሃገራችን አስረአንድ በመቶ አደገን በኢኮኖሚ ተመነደገች የሚለውን የወያኔ ሪፖርት ሲሆን ምእራባውያን የብሄራዊ ጥቅም ጥያቄ ሲኖራቸው እንዲሁ ወያኔን ሲያቆለጻጽሱት በጎን ራሳቸው በሚደጉሟቸው አጥኚ ኢኮኖሚስቶች እና ድርጅቶች በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ሙልጭ ያለች ደሃ አገዛዙ በሙስና የተዘፈቀ በባዶ ካዝና የምትመራ አገር በማለት በቻርት በሰነድ እና በፎቶ አስደግፈው ሃቁን ይነግሩናል::ይህች አስረአንድ በመቶ የኢኮኖሚ እድገት የምትባል ፋሽን በሕዝብ አእምሮ ውስጥ ለመቅረጽ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ ተሰርቶባታል::


የደሃ ደሃ የሚል ቃል የፈጠረው የአስረ አንድ በመቶ እድገት በኢኮኖሚ ዘረኝነት ላይ የተመሰረተው አገዛዝ ከነአሽከሮቹ በተደበላለቀ ፕሮፓጋንዳ እና በማይናበብ መሃይምነት ትላንት የተናገሩትን ዛሬ በማይደግሙት ባለስልጣናቱ ተከቦ ራሱን እያጋለጠ ይገኛል::ድህነትን እቀርፋለው እያለ የደሃ ደሃ መፍጠሩ በምግብ እሕል ራሳችንን ችለናል እያለ በረሃብ እና ድርቅ የሚጎዳው ሕዝብ መበራከቱ ሕዝቡ በኑሮ ውድነት መጦዙ ባለስልጣናት በሙስና ውስጥ መዘፈቃቸው ወዘተረፈ እንኳን የተማረው ሕዝብ ይቅርና ያልተማረው ህዝብ ያለውን አገዛዝ ላይ ትዝብቱን ብቻ ሳይሆን ጥላቻውን በማሳረፍ እንዲወገድለት እየጠየቀ ነው::

ትላንት አስረአንድ በመቶ አድገናል ያሉት ባለስልጣናት 9.7%ካደገችው ቻይና ልምድ መቅሰም እንፈልቃልን በማለት ቁልቁል ቤጂንግ ላይ ሂደው ሲለምኑ ተስተውለዋል::አሻንጉሊቱ ጠ/ሚ በቤጂንግ ጉብኝቱ የቻይናን ልምድ እና እርዳታ ሲለምን ሲማጽን ሰምተናል::እነዚሁ አደግን ተመነደግን የሚሉት የ11 ቁጥር አፍቃሪዎች ኢኮኖሚው ባለበት እየረገጠ ነውምንም እድገት የለም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ሲሉ እነአርከበ በገዛ አንደበታቸው ነግረውናል::ስንቱን እንስተን ስንቱን እንደምንጥል አናውቅም::በሃገር ቤት ባሉት የግል ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ በላያቸው ላይ ነጋዴ ሆኖ የተነሳው አገዛዝ የኤሌክትሪክ ሃይል በማቋረጥ ብቻ 40 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ በ6 ወር ውስጥ አድርሶ በ9 ወር ከኤሌክትሪክ ኤክስፖርት የተገኘውን 35 ሚሊዮን ዶላር "ኪራይ ሰብሳቢነት ለአደጋ አጋልጦናል::" የሚለው ኢሕኣዴግ በሙስና ተቀራምቶታል::ይህ እድገት ብለው የሚያወሩት በሌላ መንገድ ደሞ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ብለው ኢኮኖሚው ስጋት ላይ መሆኑን የሚነግሩን ችጋራም ባለስልጣኖች ሃገሪቷን እየገደሏት ነው::ብየት በኩል እንደመዘገመ በየት በኩል አፈጻጸሙ እንደተሳካ ባይታወቅም ባለስልጣናቱ አልተሳካልንም እያሉ ባሉበት ወቅት ሪፖርተር የተባለው የሕወሓት ልሳን ሃይለማርያም ሲክበው እያየን ነው ነገ አፍርጦ ካልጣለው::

አንድ ጸሃፊ በአገር ቤት ጋዜጣ ላይ በሰጡት አስተያየት ላጠናቅ:-የውጭ ምንዛሪ ምንጭ፣ የውጭ እርዳታና ብድር ነው። እርዳታው ባይቋረጥም፣ እንደታሰበው አልጨመረም። እርዳታ ሰጪዎቹ የአውሮፓና የአሜሪካ መንግስታት፣ ተጨማሪ እርዳታ የመስጠት አቅማቸው ተንጠፍጥፏል። እነሱ ራሳቸው፣ በኢኮኖሚ ድንዛዜና በበጀት እጥረት ተወጥረዋል። ብድርስ? ብድርስ አልጠፋም። ግን፣ ምን ዋጋ አለው? ብድር ሲደራረብ ያስፈራል። እንዴት ተደርጎ ከነወለዱ መመለስ እንደሚቻል እንጃ!ምንም፣ መልካም ወሬ የለም ማለት ግን አይደለም። “እድሜ ለዳያስፖራ” ብንል ይሻላል። ለቤተሰብ የሚልኩት ገንዘብ፣ ከአመት አመት እየጨመረ መጥቷል። በ2007 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ብቻ፣ ከዳያስፖራ የመጣው ገንዘብ፣ ከ1.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው። በአመት፣ ወደ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል። ከኤክፖርት ገቢ ይበልጣል ማለት ነው።በጥቅሉ ሲታይ፣ በ2007 ዓ.ም፣ አገሪቱ በውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ ጉድ ከመሆን የተረፈችው፣ በሁለት ምክንያቶች ነው ማለት ይቻላል - ‘ዳያስፖራዎች’ ለቤተሰብ የሚልኩት ገንዘብ በመጨመሩና በአለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ በመቀነሱ። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬