ባቡሩ ስራውን ጀመረ ከተባለ መስቀል አደባባይም ለተቃውሞ ሰልፍ ክፍት ነው ማለት ነው::

Minilik Salsawi - በእግረኞች እና በተሽከርካሪዎች ላይ አደጋ የጋረጠው በተደጋጋሚም የታየው ያልተጠናው የባቡር መንገድ ስራውን ጀመረ የሚል ኢሕኣዴጋዊ የልማት ጡዘት በሰንበት ተንሾኮሾከልን:: የመስቀል አደባባይ የባቡር መንገድ ልማትን አስመልክቶ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ልማቱን በቡዳ እንዳይበሉት ይመስል የተቃውሞ ሰልፍ እንዳያደርጉ የልማት አርበኞች ግን አይናቸው ልማቱን ስለሚያፋፋ ለድጋፍ ሰልፍ ሲፈቀድ ነበር::በልማት ሰበብ ወያኔ የሚሰራው የሰብኣዊ መብት ጥሰት እጅግ የተነነባት የመስቀል አደባባይ ተመልሳ አብዮት አደባባይ ትሆንብኛለች ብሎ ስጋት ስለወጠረው ተቃዋሚዎችን ለሰልፍ ሲወጡ ደንብሮ በቆምጥ ከማባረር ጀምሮ እስከ አይናቸው ተቃዋሚ መስሎ የሚታይ ሁሉ የገዢው ፓርቲ ኮተቶች ሳይቀሩ በመስቀል አደባባይ እንዳያልፉ የፌዴራል ፖሊስ ተራውጦ ሲያራውጥ አይተናል::

ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ፍራቻ ያለው ወያኔ መስቀል አደባባይ ቋሚ የልማት ጣቢያ ሆንዋል ካላለ በስተቀር እስካሁን የሚያቀርበው ሰብብ የነበረው የባቡር መንገድ ስራ ስለተጠናቀቀ ተጠናቆ ስራም ስለጀመረ መስቀል አደባባይ ከማንኛውም የልማት ስራ ነጻ መሆኑ እየተሰማ ነው::አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ሃይል የሌለው ወያኔ ባቡሩን ስራ ጅሜረ ብሎ ሕዝቡን ችግር ውስጥ እንዳይከት::ከዚህ ቀደም ያየናቸው የወያኔ ስራዎች ሁሉ ፉርሽ ናቸው::ባቡሩ ስራውን ጀመረ ከተባለ መስቀል አደባባይም ለተቃውሞ ሰልፍ ክፍት ሆነ ማለት ነው::ልማቱ ተጠናቆ ባቡሩ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ለመድገም ያህል ከዚህ በኋላ መስቀል አደባባይ ለተቃውሞ ሰልፍ የሚከለከልበት ምክንያት አይኖርም፡፡

እርግጥ ወያኔ የአዲስ አበባን ሕዝብ ካለፈው 1997 የሚያዚያ 30 ሰልፍ በሄላ ይፈራል አያምነውም::የቡርቱካን አብዮት ያነሱብኛል ፈንቅለው ይወረውሩኛል ብሎ ስለሚፈራ ብቻ የተቃውሞ ሰልፍ ለመፍቀድ የዲሞክራሲ ቀሚስ ጠልፎ ጣለኝ ልማት አለብኝ በሚሉ ሰበቦች ይከበባል::ይህ ፍራቻ እና ስጋት ነው::ወያኔ ይፈራል ይሰጋል...ለራሱ መስቀል አደባባይን ሲጠቀም ከርሞ ለተቃዋሚዎች ልማት ላይ ነው ይላል በመስቀል አደባባይ ለመጠቀም የሚፈልግ ጸረ ልማት ብቻ ነው ይለናል::አሁን ደሞ ምን ምክንያት ሊያስታቅፈን ይሆን ? በእግረኞች እና በተሽከርካሪዎች ላይ አደጋ የጋረጠው በተደጋጋሚም የታየው ያልተጠናው ባቡሩ ስራ ጀመረ መስቀል አደባባይም ከልማት አረፈ::አሁን ስራውን መጀመር አለበት:መስቀል አደባባይ !!!!‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬