ኢሕአዴግ እየሰራ ያለው ፕሮፓጋንዳ ኪሳራ እንደሆነ ካድሬዎቹ እየተናገሩ ነው::

Minilik Salsawi - ከተለያዩ የኢሕአዴግ ካድሬዎች በተለያዩ የማህበራዊ ድህረገጽ የተሰበሰበ መረጃ እንደሚያመለክተው ኢሕአዴግ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እየሰራ ያለው ፕሮፓጋንዳ ኪሳራ እንደሆነ ካድሬዎቹ እየተናገሩ ነው::ካድሬዎቹ ድርጅታቸው የሚሰራው ዶክመንተሪ ፊልም አሊያም ቃለመጠይቅ እንዲሁም ሃተታና መግለጫ በሕዝቡ በተቃራኒው እንደሚተረጎም እና ተቀባይነት እንዳሌለው በደንብ እናውቃለን ሲሉ ድርጅቱ የሚሰራው ስራ ውስጥ ውስጡን እየገዘገዘው ነው ሲሉ ተናግረዋል::የድርጅታችን ፕሮፓጋንዳ ምንም ጠቀሜታ አለመኖሩን የሚያሳየን አብዛኛው ሕዝብ ሲያሾፍበት እና ቀልድ ሲፈጥርበት እንደሚውል የተናገሩት የወያኔ ካድሬዎች የውጪ ሃይሎችን በማሳመን ረገድ ግን ድርጅታችን የተሳካ የሎቢ ስራ ሰርቷል ሲሉ ፈርጠም ብለው ይናገራሉ:: ምእራባውያን ከተቃዋሚዎች ይልቅ በኢሕአዴግ ላይ አመኔታ ያላቸው መሆኑን በተለያየ መድረክ ገልጸዋል ያሉት የወያኔ ካድሬዎች ከዚህ ቀደም በአፍሪካ መሪዎች መውደቅ ላይ የምእራባውያንን ሚና በተመለከተ ለተጠየቁት ጥያቄ መልስ ሳይሰጡ አልፈዋል::
ባለፉት አስራሰባት ቀናት በተከታታይ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው የገዢው ፓርቲ አባላት ከመለሱት መልስ የተጨመቀው መረጃ እንደሚያሳየው አሸባሪ ተሸባሪ የሚሏት ጉዳይ እንደ አደገኛ ቦዘኔ ለድርጅታቸው ሰበብ ይዛ ልትመጣ ትችላለች ሲሉ በ1997 የተደረገውን ምርጫ አጣቅሰው ይናገራሉ::የሕዝቡን ዝምታ በተመለከተ የተናገሩት ካድሬዎች ድንገት ከህዝቡ መሃል የሚፈነዳ ችግር እንዳይኖር በሚል በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ቡድኖች ተከፋፍለው መነጋገራቸውን ሲገልጹ ምርጫ 2007 በተመለክተ ድርጅታቸው 100% የፓርላማ ወንበር አሸነፈ እንጂ የሕዝቡን ድርሻ አላካተተም የሕዝቡን ልብ አላሸነፈም ሲሉ በተዘዋዋሪ ምርጫውን እንዳጭበረበሩ አመላክተዋል::
በቅርቡ የተከሰተው የሞላ ፕሮፓጋንዳ ኢሕአዴግን ጎዶሎ አድርጎታል::ያሉት አባላቱ ጉዳዩ እንዳልገባቸው እና በመንግስት ደረጃ የሚሰራው ስራ ቀፋፊ ነው ያሉ እንዳሉ ሁሉ የድርጅታቸውን የደህንነት እና የስለላ ተግባር ያዳነቁ በስፋት ተገኝተዋል::የሞላ ጉዳይ ፕሮፓጋንዳ እንደሚሰራለት ሳይሆን በድርጅቱ ውስጥ አነጋጋሪ ሆንዋል ያሉም አልጠፉም::የወያኔ ፕሮፓጋንዳ በሞላ ላይ እና በልማት ዙሪያ የፕሮፌሰር ብርሃኑን ስም ለማጥፋት መዋሉ በጎ ነው ወይ ብላቹ ታስባላቹ ወይ የተባሉት አባላቱ ከ126 ሰዎች 111 የሚሆኑት የፕሮፌሰር ብርሃኑን ስም የማጥፋቱ ዘመቻ ሃሰት እና የወረደ ፖለቲካ ሲሉ አጣጥለውታል::የማህበራዊ ድህረገጽ ተሳታፊ የሆኑ በ100/75% ከሕወሓት አባላት የሆኑ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ እጅግ ብልግና የተሞላበት እና ያልበሰለ ከመሆኑም ውጪ ራሳቸውን እንደ ጀግና እና ሃገር ወዳ ሌላውን ከይሲ አድርገው በመልሳቸው አስቀምጠዋል::በአሁኑ ወቅት ያለው እንቅስቃሴ ሲለካ በማህበራዊ ድህረገጽ በተለያየ ስም የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ዘረኝነትን እና የከፋፋይነት ስራዎች ላይ እንዳተኮሩ ይታወቃል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬