በሶማሊያ ስለዘመተው ጦር ማብራሪያ እንዲሰጣቸው የሰራዊቱ አባላት ጠይቁ::በወያኔ ጁንታ እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል አለመተማመን እና ጥርጣሬው መስፋቱ ተሰማ::

Minilik Salsawi- የሕዝብን መብት እና በልማት ስም በፕሮፓጋንዳ በመደለል በስልጣን ላይ ያለው በወያኔው ጁንታ እና በመከላከያ ሰራዊቱ መካከል አለመተማመን እና ጥርጣሬው እየሰፋ መምጣቱን ለምድር ጦር ክፍል ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል::ባለፉት አመታት በሰራዊት ውስጥ ወታደራዊ ደህነቶች መሰግሰጋቸውን ተከትሎ ከሰራዊቱ ጥያቄዎች ጋር ተደምሮ በተለይ በምስራቅ ደቡብ እዝ እና በሰሜን እዝ ከፍተኛ የሆነ የውስጥ ውጥረት እንዳለ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::እንዲሁም በሰራዊቱ ውስጥ በየስብሰባው ሶማሊያ ስለዘመቱ ወታደሮች ማብራሪያ መጠየቁን ታውቋል::

በሰራዊት ውስጥ በወታደራዊ ደህንነት ቦታ የሚያገለግሉ ምንጮች እንዳሉት ሰራዊቱ ውስጥ የተከሰተው አለመተማመን እና ጥርጣሬ የፈነዳ ሰአት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ በሕወሓት እና በአሽከሮቿ ላይ እንደሚከሰት ገልጸው አሁንም በየእዙ የሚጠረጠሩ መኮንኖች እስር እንደቀጠለ ተናግረዋል::ለሆዳቸው ያደሩ የሰራዊት አባላት ቢኖሩም ይህን ያህል አይደሉም የሚሉት ምንጮቹ ሰራዊቱ ግን በመፈራራት እና እርስ በርስ ጥርጣሬ ውስጥ እየተጓዘ እንደሆነ ገልጸዋል::በተልያዩ ግምገማዎች ከ10 የሰራዊቱ አባላት ሰባቱ በማስጠንቀቂያ መታለፋቸው በራሱ በሰራዊት ውስጥ ያለው ችግር አንደኛው ገጽታ መሆኑ አውስተዋል::

የተቃዋሚው ሃይል የራሱን የትግል ስልት ነድፎ ሰራዊቱ ውስጥ ገብቶ ሊንቀሳቀስ ይገባዋል ያሉት ምንጮቹ ሰራዊቱ በሆነ ባልሆነው ከአለቆቹ ጋር የሚጋጭ ከተላከበት ሳይመለስ በዛው የሚጠፋ እንዲሁም በየጫካው ራሱን አጥፍቶ የሚገኝ መሆኑን አክለው የገለጹ ሲሆን በሱማሊያ የዘመቱ ወታደሮችን በተመለከተም በሰራዊቱ እስጥ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ጠቁመዋል::በአዲስ አበባ እና ብደብረ ዘይት ባለፈው ሳምንት ብቻ በተጠሩ ስድስት የግምገማ ስብሰባዎች ላይ የሶማሊያ ዘማች ሰራዊት አባላትን በተመለከተ ጥያቄዎች መነሳታቸው እና ማብራሪያ መጠየቁም ታውቋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬