የለውጥ ሃይሎች ካለፉት የትግል ተሞክሮዎች መማር ያስፈልገናል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - 2007 ለለውጥ ብሎ የተነሳው የለውጥ ሃይል ከትግሉ ተሞክሮዎችን እንደቀሰመ ይታወቃል::ባለፈው አመት ወያኔ ሃይል ተጠቅሞ ከፍተኛ የሆነ ችግር በለውጥ ሃይሉ ላይ ከመፍጠሩም በላይ የጠበበውን የፖለቲካ ምሕዳር ጭራሽ ደፍኖታል::ለውጥ ፈላጊ ሃይሉ ከግድያ ጀምሮ እስር እና ስደትን በሰፊው አስተናግዷል::ወያኔ በስልጣን ላይ ለመቆየት ያል የሌለ ሃይሉን ተጠሟል:: በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘው ወያኔ ትንፋሹን መሰብሰብ እስኪያቅተው ድረስ ተወራጭቷል::ምርጫውን በ100% የፓርላማ ወንበር በሃሰት እና በጉልበት አሸነፍኩ ቢልም 100% የሕዝብን ድጋፍ እንዳሌለው አረጋግጧል::ሕዝብን በጅምላ የመጨቆን አባዜውን ቀጥሎበታል::

በቂም በቀል የተሞላው ወያኔ የሕዝብ ድጋፍ እንዳሌለው ስላወቀ ብቻ ሕዝብን እየተበቀለ መኖርን መርጧል::ይህን ግፍና በለደል ለማስቆም ይሚታገሉ የለውጥ ሃይሎችን በማፈን በማሰር በመግደል በማሳደድ እርስ በእርስ በማባላት ስራውን አጧጡፎታል::ፓርቲዎችን እስከማፍረስ ጠንካራ አመራሮችን እስከማሰቃየት ዘልቆበታል::በሃገሪቱ ለውጥ እንዲመጣ የሚታገሉ ጠንካራ ታጋዮች እስር ቤት ሲታጎሮ በርካቶች ተሰደዋል::የነጻው ፕሬስ ለለውጥ ባደረገው አስታውጾ ጋዜጠኞች ተሰደዋል ታስረዋል::የሃይማኖት ነጻነት የጠየቁ ኢትዮጵያውያን መፍትሄ ከማግኘት ይልቅ ለከፍትኛ ሰቆቃ ተዳርገዋል::የተቃዋሚ ፓርቲዎች በድህረ ምርጫ እና ከምርጫ በኋላ በተደረገባቸው ጫና ከፍተኛ መስዋትነት ከፍለዋል::በተቃዋሚ ሽፋን ተመሳስለው የገቡ ሰርጎ ገቦች ከፍተኛ ጉዳት በለውጥ ሂደቱ ላይ ፈጥረዋል::ሕዝቦች በፖለቲካ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊው መስክ የበደል በደል እየተፈጸመባቸው ይጌኛል::ይህን ሁሉ ለማስቆም የለውጥ ሃይሉ በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ ትግሉን አስፍቶ ቀጥሏል::ካጋጠሙን ችግሮች እና በውስጣችን ካሉ ቅራኔዎች እና ጥንካሬዎች በተሻለ መንገድ ለመታገል እና ያለምነውን ለውጥ ለማምጣት ካለፉት ሂደቶች ተሞክሮዎችን በመውሰድ ትግሉን በአዲስ መስመር እና በነቃ ሕሊና በመቀጠል አዲስ የትግል ድሎችን ለማስመዝገም በጋራ የምንቆምበት ጊዜ ላይ መሆናችንን እና ከተናጠል ጉዞ ሁሉን ያሳተፈ አዲስ የለውጥ ሂደት ለመቀየስ ካለፈው መማር ግድ ይለናል::

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጥ ይፈልጋል ይህ በተደጋጋሚ የምናውቀው ጉዳይ ነው::ካለፈው መማር ብቻ ሳይሆን ልዩነትን አቻችሎ በጋራ ጎን ለጎን መጓዝ በጋራ መቆም ያስገድደናል::እንደ ባለፍት አመታቶች ከመጎሻሸም እና ከፖለቲካ ግልምጫ ራሳችንን ማውጣት አለብን ::እንደኔ አስብ ከማለት በዳበረ ሃሳብ በጋር ልንጓዝ ይገባል::በባዶ እና በፈጠራ ፕሮፓጋንዳ መሞላት አሊያም በውጪ ሃይሎች በኢትዮጵያ ጠላቶች በቀደዱልን መንገድ መትመም ልናቆም ይገባል::እውነተኛ መረጃ የትግል ሃይል እና መማማሪያ መሆኑን ልንዘነጋ አይገባም::ካለፈው መማር ካልቻልን የራሳችን ጠላቶች እንደሆንን መቀጠላችን ሲሆን ይህም ለጋራ ጠላታችን ለወያኔ ክፍተት ይሰጣል::የኔ ብቻ ትክክል ነው ብለን የምንጓዝ ከሆነ ለጊዜው ይመስለናል እንጂ እንደቀድሞው ሌላውን ማሸሽ እንደሚሆን ካለፈው ልምዳችን ተምረን ለመጪው ስኬትን መላበስ ያስፈልገናል::ለዚህም ነው የለውጥ ሃይሎች ካለፈው ተሞክሮዎች ተምረን በጋራ እና በአንድነት በመቆም የጋራ ጠላታችንን ወያኔን ወደ ከርሰ መቃብሩ ማውረድ ግዴታችን ነው::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬