የህዝብን ዝምታ ሰብሮ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በጋራና በጽናት እንጓዝ::

Minilik Salsawi በእናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የሕወሓት አምባገነን ቡድናዊ አገዛዝ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመው የፖለቲካና የኢኮኖሚ በደል ገደቡት አልፎ ዜጎች በገዛ አገራቸው መኖር እንዳይችለ ሆነዋል:: በሃገራችን ተከስትው ይሚገኙ የፖለቲካ ጫናዎች የኑሮ ውድነት የድርቅ እና የተለያዩ ችግሮች አገዛዙ በሚፈጽመው በደል ላይ ተደራርበው ወገኖቻችንን እጅግ ለከፋ አደጋ አሳልፎ ሰጧቸዋል::ይህ ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ውርደት እየታየ ያለው አገዛዙ ለዜጎች ያለውን ንቀት እብሪት እና መንግስታዊ ሃሰተኝነት ከሽብርተኝነቱ ጋር ተቀላቅለው ሕዝቡን አንገፍግፈውታል::የአገዛዙ ግፎች ተዘርዝረው የማያልቁ ሲሆን ለዚህ ደሞ መፍትሄው አገዛዙን አስወግዶ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ብቻ ነው::

ይህንን ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በአንድነት መቆም ይኖርባቸዋል::የጋራ ጠላታችን ወያኔ ነው የሚሉ የሃገር ውስጥ ይሁን በውጪው አለም ያሉ የለውጥ ሃይሎች ለሕዝብ ነጻነት እና መብት እንታገላለን እስካሉ ድረስ እርስ በእርስ መናከስ አቁመው በመደማመጥ እና በመወያየት በመመካከር እና በመቻቻል በመግባባት እና በመፋቃር ለሃገራዊ አጀንዳ በጋራ መቆም ችላ የማይባልበት ወቅት ላይ ተደርሷል::የሕዝብን ታማኝነት ለማግኘት የለውጥ ሃይሎች እርስ በርሳቸው እየተባሉ እንዴት እኛን ነጻ ያወጣሉ የሚለውን ቅብብሎሽ ለመቁረጥ እና በሕዝብ ዘንድ አመኔታን ፈጥሮ ትልቅ የለውጥ ስራ በመስራት አገዛዙን ማስወገድ ይቻላል::በሰላማዊ ትግል ይሁን በትጥቅ ትግል የተሰማሩ ሃይሎች ሕዝብን አስተባብሮ በአንድነት ለመምራት የሁሉንም የጋራ ልብ ለመግዛት የሚችሉት በአንድነት ቆመው የህዝብ ጠላት የሆነውን ወያኔን ለመደምሰስ የፖለቲካ ቆራጥነት እና የትግል ጽናት ሲኖር ነው::ተበታትኖ ትግል አንድም ለወያኔ ክፍተት መፍጠር ሲሆን በሌላውም በር የህዝብን ዝምተኝነት ማበርታት ይሆናል::መሰራት ያለባቸው የለውጥ ስራዎች ሁሉ በመደጋገፍ እና በመቻቻል መሆን ይገባዋል::


በዚህ ግፎች እየበረቱ በሄዱበት ወቅት ላይ የሕዝቡ የለውጥ ፍላጎት አብሮ እየጨመረ ይመጣል::ሕዝቡ ዝምታው ለምንድነው? እኛ ጋር ምን ችግር አለ? መቻቻል እና መተባበር የምንችለው እንዴት ነው? ለስልጣን የሚቋምጠው እና ልለውጥ የመሰራው እንዴት ይለይ?የሃሳብ ልዩነቶችን ማግባባት እና ማቻቻል የምንችለው እንዼት ነው? የሕዝቡን ዝምታ እንዴት መስበር ይቻላል?ሕዝባዊ ታማኝነትን በጋራ ሃገራዊ አጀንዳ እንዴት መፍጠር እንችላለን? የያዝነው ስትራቴጄ አዋጭነቱ ምን ያህል ነው..ተጠባባቂ ስትራቴጂ አለን ወይ? ሁሉም የለውጥ ሃይሎች በአንድነት ማቆም የሚቻለው የትኛው ግድፈት ቢቀረፍ ነው? ሰላም እና ዲሞክራሲን ለመተግበር ተነሳሽነት ምን ያህል ነው? ባለፉ 20 አመታት የተበታተነው ትግል እና የተበታተኑ ድርጅቶች ምን ፈጠሩ ? ካለፈው የትግል ተሞክሮ ምን እንማራለን ?...ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ የለውጥ ሃይሎች ግዴታ ነው::ዋናው ነጥብ ግን በአንድነት መቆም ነው::ሃገራዊ አጀንዳ ይዞ የጋራ ጠላት የሆነውን ወያኔን በማጥፋት ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በአንድነት መቆም ችላ የማይባል ነው:: የህዝብን ዝምታ ሰብሮ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የለውጥ ሃይሎች በጋራና በጽናት እንጓዝ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬