ቀን እየቆጠሩ ከማስጨፈር የግለሰብ ከዚያ የብሄረሰቦችን መብት ማክበር ይቅደም::

Minilik Salsawi's photo.Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)- የወያኔን ጉጅሌ አገዛዝ ጭካኔ እና እኩይ ተግባር ብናወራው አያልቅም::በሕግ እና በሕዝብ ስም ሽፋን በርካታ አደገኛ ወንጀሎች በተደጋጋሚ እየተፈጸሙ ነው::በለውጥ ሃይሉ መካከል በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት እስካሌለ ድረስ ወያኔ ይህንኑ ክፋቱን ከሰይጣን የበለጠ ተግባሩን አስፋፍቶ ይቀጥላል::ሕዝብ እምነት የሚጥላባቸው ምርጥ የለውጥ ፖለቲከኞች ማነስ በስሮቻቸውን ያሉ አባሎቻቸው በድርጅታዊ ዲሲፒሊን/ስነስርኣት/አለመታነፅ የውስጥ ብስለት እጥረት ደንቃራ ቢሆንም የወያኔን ጉጅሌ መንግስት ለመጣል በጋራ መቆም አሁንም ችላ ሊባል የማይገባ ጉዳይ ሲሆን በቀን ቁጥር አመት እየተጠበቀ ለብሄር ብሄረሰብ ቀን ለጭፈራ እንዲወጣ የሚደረገውን ቀሪዎቹን የአመት ቀናቶች የሚደበደበውን የሚገደለውን የሚታሰረውን ሕዝብ መብት እንዲከበር እጅግ በጥንካሬ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል::
ከታህሳስ አንድ ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 28 ከአመት አመት ሕዝባችን ወገናችን እየተረገጠ እየተገደለ እየተደበደበ እየታሰረ እየተሰደደ የብሄር ብሄረሰብ ቀንን ህዳር 29 እየጠበቁ ማስጨፈር ምን የሚሉት ጉዳይ እንደሆነ ግልጽ አልሆነም:;የብሄረሰብ መብቶችን ለማስከበር ሕገመንግስት አጸደኩ የሚለው የፖለቲካ ፕሮግራሞቹን ገልብጦ ሕዝብን እያስተዳደርኩ ነው የሚለው አገዛዝ ለራሱ ሕገመንግስት ተገዢ መሆኑ ባልተረጋገጠበት በገሃድ የሕግ የበላይነት በደፈጠጠበት አገር ላይ በየትኛው ሞራሉ የብሄር ብሄረሰብ ቀን ብሎ እንደሚያከብር ግልጽ ካለመሆኑም ሌላ ከጭፈራ እና የሃገሪቱን በጀት ከማባከን ውጪ የትኛው ብሄረሰብ መብቱ ተከብሮለት ድምጹ ተሰምቶ አለ የሚባለው ሕግ እንደተተገበረ በተግባር የታየ ነገር የሌለ ሲሆን ከድብደባ ከእስር ከጭፈራ እና ከስደት ውጪ ምንም የተፈየደ ነገር አልታየም::

ሕገመንግስቱ የመደገፍ የመቃወም መብት ሰጥቷል ቢባለም የደገፈም የተቃወመም ሕዝብ በአንድነት በመሳሪያ ሃይል እየተጨፈለቀ ባለበት ሃገር የብሄረሰብ ቀን ብሎ ወያኔ ሲያከብረው ሕዝቡን በግዳን እና በገንዘብ ድለላ ሲሰበስበው ምንም አይሰቀጥጠውም:: በየአመቱ ቀን እየተቆጠረ የብሄረሰቦች ቀን በጭፈራ ይከበር እንጂ ሕዝቦች በፖለቲካ ይሁን በኢኮኖሚ ሲደሄዩ በካድሬዎች ሰበካ እርስ በእርስ እንዲባሉ ሙከራ ሲደረግ ከቀያቸው ሕዝቦች ሲፈናቀሉ የመብት ጥያቄ ያነሱ ሲገደሉ እና ሲታሰሩ ስለ አንድነት የተናገሩ ከአገር እንዲሰደዱ ሲደረግ የነጻው ፕሬስ ስለብሄር መብቶች ሲናገር በፍረጃ በመዝጋት እና በማስፈራራት የፍትህ አካላት የባለስልጣን አገልጋዮች ሆነው የፍትህ ስራን ከጨዋታ ውጪ እንዲሆን በማድረግ ሕዝቡ ጸድቆልሃል የተባለው ሕገመንግስት ባጸደቀው አካል ሲተረማመስ ሲቀዳደድ እና ሲጥመለመል እያየን ነው::ለዚህ ሁላ መፍትሄው ግን ቀን እየቆጠሩ ከማስጨፈር የግለሰብ ከዚያ የብሄረሰቦችን መብት ማክበር ማስቀደም ሲሆን የተሻለው ደሞ አገዛዙ ስልጣኑን ለቆ ለሕዝብ ቢያስረክብ ይበለጠ የተሻለ ቢሆንም በተለይ ግን መውደቂያው እየደረሰ ያለው ይህ አገዛዝ በሕዝብ ልጆች እንደሚደመሰስ ሌላኛው ትልቁ ማረጋገጫ ነው::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬