ሕወሓት አስተምሮ ያደራጀቸውን የዲያስፖራ ዘረኞችን ድብቅ ሴራ ልናከሽፍ ይገባል::ጠባቦችንና ከፋፋዮችን ዝም ልናሰኛቸው ይገባል::‪


Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክፍለሃገር ውስጥ በተለያዩ አከባቢዎች የተከሰቱ የሕዝብ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም ከዚሁ መስመር ጋር በተያያዘ የመልካም አስተዳደር የፍትሕ ዪኮኖሚ እና መሰል ጉዳዮች ብሶት ዛረ ድረስ ቀጥሎ ይገኛል::ይህንን የሕዝብ ብሶት ለራሳቸው የፖለቲካ አጀንዳ ለመጠቀም ከሕወሓት ጀምሮ እስከ ዲያስፖራ ፖለቲከኞች ድረስ የማይቧጠጥ ሲቧጥጡ ያልበላቸውን ሲያኩ እያየን ነው::ፖለቲካው ሴራው እና ስሪያው ግቡ እና ሂደቱ ያልገባቸው ጥሬ አሸርጋጆችም በያሉበት ሆያሆዬውን ተያይዘውታል::እርግጥ አንድ ነገር ማወቅ አለበን በየማህበራዊ ድህረገጽ የሚቦተለከው እና መሬት ላይ ያለው ሕዝባዊ ሃቅ እጅግ የተለያየ እና የማይገናኝ ነው::ሕወሓት የምቃወመው ዘረኞች ሌላውን በጠላትነት ሲፈርጁ ዝም ለማለትና ሃገር እንዲበታተን ሕዝብ እንዲተላለቅ አይደለም::

በአንድነት ስም ያልበሰለ ፖለቲካ ማራመድ በሁለት ቋንቋ ሁለት የማይመሰሰሉ የፖለቲካ ማጭበርበሮች አይጥሙኝም::ዝም በሉ አትንኳቸው የሚባል ነገር ተቀባይነት የለውም::የኦሮሞ ሕዝብን ተቃውሞ ተገን አድርገው አፍራሽ ተልእኮ በማነገት በሃገር ቤት ያለውን ወጣት በዘረኝነት መርዝ እየበከሉ የሚገኙ የዲያስፖራው ዘረኞች በነማን እና እንዴት እንደተፈበረኩ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ተናግሬዋለሁ::በሕወሓት ድጋፍ በየኤምባሲወ ተወሽቀው ሲኖሩ ከርመው ሕወሓት ለአላማው ስኬት በየሚዲያው የበተናቸውን ከፋፋዮች ልንዋጋ ይገባል::ከ40 አመት በፊት የፓን አፍሪካኒzም እንቅስቃሴ ተገን በማድረግ የኦሮሞ አገር አቋቁማለው ብሎ የተነሳው ኦነግ ሳይሳከለት መበታተኑ ቢታወቅም ይህንን ያደረጉ ፖለቲከኞች የፓን አፍሪካኒዝም ጊዜው ስላለፈበት በኢኩልነት እና በአንድነት በተመሰረተ አገር ላይ መኖር ይበጃል የሚል አዲስ እና የዘመነ አስተሳሰብ ይዘው ቢመጡም ይህ ያልጣመው ሕወሓት ያደራጃቸውን ወጣቶችን በተለያዩ ዘዴዎች ወደ ዲያስፖራው በማስገባት ዘረኝነቱን እና አገር የመበታተኑን ሴራ ለማሳካት ደፋ ቀና እያለ ነው::ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መስርቶ ዜጎች እኩል የሚኖሩባት አገር ከመመስረት ይልቅ በሁለት ቢላዋ የሚኖሩ ዘረኞች እየፈሉ መተዋል::

በሁለት ቋንቋ ተጠቅመው ሕዝብን ለማታለል እና ለማሸበር የሚሞክሩ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን በመላው አገሪቱ ተዝኣዙረው ሰርተው እንዳይኖሩ ኦሮሚያ ለኦሮሞ አማራ ለአማራ ትግራይ ለትግሬ ወዘተ የሚሉ እኩይ ፖለቲከኞች አላማቸው ሕዝብን በመከፋፈል እና በማጋጨት የፖለቲካ ግባቸውን ሃገር መበጣጠስ መሆኑ እሙን ነው::ይህ የዘረኝነት መርዝ የታጠቁ እና የጎሳ ፖለቲካ ሹምባሾች ከሕወሓት በላይ ሕወሓቶች መሆናቸውን ልናውቅ ይገባል:: አንዳንድ የለውጥ ሃይሎች የሚከተሉትን የጅል ፖለቲካ ወደ ብልሃት ሊለውጡት እና ሊነቁ ይገባል::በጎሳ ፖለቲካ በተመሰረተ አገር ዜጎች ሊሸማቀቁ አይገባም::በአሁን ወቅት ዜጎች ተዘዋውረው እንዳይሰሩ ከመደረጉ በላይ በገዛ እገራቸው እንደ ባይተዋር እንዲሸማቀቁ እየተደረገ መሆኑን ይታወቃል ይህ ደገሞ ነገ ዘረኞቹ ሊገነጣጥሏት ያሰቧትን አገራችንን ሕዝብን ለባርነት እያዘጋጁት ነው::አቋም የሌላቸው በዲያስፖራው ውስጥ የተሰገሰጉ እና በዘረኝነት ላይ ተመስርተው ባፈጀና ባረጀ አስተሳሰብ ተጀቡነው ያልሰለጠነ ፖለቲካ የሚያራምዱ በሕወሓት የተደራጁ ጎጠኛና ጠባቦች ትምክህተኛና ጦረኞችኝ ድብቅ ሴራቸውን ልናከሽፍ ይገባል::የሕዝቦችን የነጻነት ጥያቄ መልስ እንዳያገኝ ድብቅ ሴረኞችን ቦታ በመስጠት ታሪካዊ ግድፈት እየፈጸምን ነው::ልንነቃ ይገባል ::ሕወሓት ታላቋን ትግራይን ለመመስረት እና ሌላውን ከጀርባ ሆኖ እርስ በእርስ ለማባላት ያቀደውን ሴራ ልናውቅ ይገባል ለዚህም ያዘጋጃቸው ዘረኞችን ድብቅ ሴራ ልናከሽፍ ይገባል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬