የቆሸሸው የበሰበሰው ኢሕአዴጋዊ አስተሳሰብ እንጂ ሕዝብና ግድያ ይቁም ያሉ ግለሰቦች አይደሉም::

 Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - አንድ መቶ በአንድ መቶ ምርጫውን አሸንፌአለሁ የሚለው ኢሕኣዴጋዊ ማጭበርበርን ተከትሎ በተለያዩ አከባቢዎች ሕዝባዊ ብሶቶች መፈንዳት ከጀመሩ ወራቶች ተቆጥረዋል:: መርጠ ውኛል ያላቸው ሕዝቦች ገና የምርጫው ቆጠራ ስምምነት ፊርማ ሳይደርቅ አመት ሳይሞላው ወያኔን ውረድልን በቃኽን ማለት የተጀመረው እንቅስቃሴ በርትቶ ቀጥሏል::ሕዝቡም ትግሌን ጫፍ ሳላደርስ ወያኔ ሳላወርድ ወደቤቴ አልገባም በማለት ጥርሱን ነክሶ እየታገለ ይገኛል::ማንኛውም አምባገነን በድዳችን እንገዛለን ሲል የነበረውን አፄ ሃይለስላሴን ጨምሮ በአለማችን አወዳደቃቸው ውርደት ነው::በዚህ በሰለጠነ ዘመንም የወያኔ አውዳደቅ የውርደት ውርደት እንደሚሆን ሕዝቡ በትግሉ ለማስመስከር ከጫፍ ደርሷል::

በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ኢሕኣዴግ መራሹ ሕወሓት በሚፈልገው መልኩ ኦሕዴዽ የተባለው አሽከሩን እያሽከረከረው ይገኛል::ኦሕዴዽ በዚህ ሳምት ባደረገው ግምገማ የተለያዩ አባሎችን ከስልጣናቸው እያነሳ እያገደ እያባረረ በተዘዋዋሪ ደግሞ እነዚሁኑ አዳዲስ ስልጣን እየሰጠ ይገኛል::የሕዝብ ብሶት ሲገነፍል የድርጅቱ አመራሮች የብቃት ማነስ ነው የሚለው ወያኔ የሕዝብ ጥያቄን ከማዳመጥ ይልቅ አመራሮቹ ሲወነጅል ይውላል::የሚወነጀሉት ደግሞ ሕዝብን መርገጥ መግደል ይቁም በዚህ ጉዳይ በዚህ ተግባር መሳተፍ አንፈልግም የሚሉ አመራሮቹን ማስደንገጥ ባህሪው መሆኑ ይታወቃል::ችግር ሲፈጠር አመራሮች ላይ ከመሳበብ እና በግምገማ ከመጠቃቆም የሕዝብን ችግር እና ጥያቄ ወደ ጠረጴዛ አምጥቶ በመገምገም የተሻለ መፍትሄ መስጠት የፖለቲካ ውጤቱ እጅግ ግቡን ይመታል::

ወያኔ ችግሯ ሕዝብ ከሷ ቀድሞ መሰልጠኑን አለማወቋ ነው::ኦሕዴዽ የተባለው የሕወሓት ገረዶች ስብስብ እንዳሽከረከሩት የሚሽከረከር ሕልውናው በሕወሓት ሕልውና ላይ የተመሰረተ ስለሆነ እንዳዘዙት እየሆነ ይገኛል::ኦሕዴድ ከሁሉም በፊት መስመራችን ያስመዘገባቸውን አንፀባራቂ ድሎች ያቆሸሹ የግለኝነትና ጥገኝነት፣ እንዲሁም የጎራ መደበላለቅን በጥልቀት በመመርመር ከሥራ አስፈጻሚና ከማዕከላዊ ኮሚቴ ጀምሮ በከፍተኛ አመራሮች ላይ ያለምንም ርህራሔ ዕርምጃ ተወስዷል ሲል ውሳኔ ማሳለፉን ሰምተናል:: በኢሕኣዴግ ይሁም በኦሕዴዽ መስመር የተመዘገበ አንጸባራቂ ይሁን የማያንጸባርቅ ድር በፍጹም አላየንም::ሕዝብ በመልካም አስተዳደር በፍትሕ እና ተዛማጅ እጦቶች ሲንገላታ ሲያለቅስ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ሲኮረኮም ነው ያየነው ለዚህ ደሞ ሩቅ ሳንሄድ የዚህ ሰሞን የሕዝብ ብሶት ፍንዳታው ብቻ በቂ ነው::

የቆሸሸው በግለኝነት እና በጥገኝነት እየኖረ ያለው የፖለቲካ ትሉ ኢሕኣዴግ መሆኑን ሊያውቁት ይገባል::ሌላውን በጎራ በመደበላለቅ የአንድ ብሄር የበላይነት በሕወሓታዊ ዝምድና እና ወዳጅነት ተገንብቶ በኢኮኖሚ የበላይነት ሌላውን ለመቆጣጠር በሚሮጥበት በዚህ ጊዜ ላይ ሕዝብ ነቅቻለሁ በቃኝ እያለ ይገኛል::

ኢሕኣዴግ አሁን የያዘው መስመር ይሁን ይዞ የመጣው መስመር የቆሸሸ እና የበሰበሰ ነው:;ሕዝብን ከማዳመጥ ይልቅ ሕዝብን መግደል የሚቀናው ፓርቲ በፍጹም በስልጣን ላይ ተቀምጦ ይመንግስት አስተዳደር ሊሆ አይችልም::በአንድ ብሄር የበላይነት ተመርቶ በቂም በቀል እና በጎሳ ፖለቲካ ሕዝብን ለማስተዳደር መልፋት ነገ ላይ የሚወልደውን ሕዝባዊ ምላሽ መሸከም እንደሚያቅት ከወዲሁ ለመናገር እፈልጋለሁ::መከልከያውን ደህንነቱን እስከ መንደር ኮንዶሚኒየም በሕወሓት ነባር እና አዳዲስ ካድሬዎች ቁጥጥር ስር አድርጎ ሌላውን በመግፋት ለመኖር ማቀድ ጥርሱን ነክሶ ለሚኖረው ሕዝብ ትርፉ በቀልን ማስተማር እንጂ ምንም ፋይዳ አይኖረውም:: ስለዚህ ስልጣን መልቀቅ እና ሕዝባዊ መግስት የእኩልነት ሃገር መመስረት ትልቁ እና ብቸኛው አማራጭ ነው::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬