ብሄራዊ መግባባት የሚፈጠረው ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ሲኖር እንጂ ምሁራንን ሰብስቦ በመጮህ አይደለም::

ብሄራዊ መግባባት የሚፈጠረው ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ሲኖር እንጂ ምሁራንን ሰብስቦ በመጮህ አይደለም::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎Ethiopiaprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi - Ethiopian DJ - አዲሱ የጊዜ መግዣ ዲስኩር - ብሄራዊ መግባባት መፍጠር - ወያኔ ሕዝብን ማታለል ልማዱ ስራው ተግባሩ አድርጎ ይዞታል::ወያኔ ምሁራንን ሲያወያይ ይህ ለመጀመሪያው አይደለም አዲስ አበባን በገበሬውና በኤምፔሪያሊዝም ድጋፍ ሲቆጣጠር ጀምሮ ምሁራን ሲያወያይይ ካለንበት የተበላሸ ፖለቲካ ላይ ደርሷል::ሁልግዝጥ እቅድ ነድፈናል ከማለት ውጪ አንድም ጠብ ያለ የተሻሻለ ነገር የለም::ዜጎች በአገራቸው ጉዳይ እንዳይሳተፉ እንዲሳቀቁ እንዲደነብሩ ወዘተ ከግድያ ጀምሮ እስከ እስር እና ማሳደድ ድረስ በፊት ለፊት ካለእፍረት ተግብሯል::ሕዝብ መንቃቱን እንኳን አንድም የማይባንነው ወያኔ ሁል ግዜ ማዘናጊያ እና ጊዜ መግዣ ብሎ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ያለፈባቸው እና ችግሮችን ከማባባስ ውጪ ምንም የፈየዱት ነገር የለም::ባለንበት 21ኛ ክፍለ ዘመን ፖለቲካው በስሏል አገራት ዜጎቻቸውን መወንጀል ትተው ኢኮኖሚያቸውን ሲገነቡ እያየን ነው::እንናገረው ብንል ብዙ ማለት ይቻላል ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይህ በፍጹም የለም::ግልጽነት እና ተጠያቂነት ስላሌለ አገሪቷ የመሃይማን እና የሌቦች መፈንጫ ሆናለች::

ወያኔ ተናግሮ እንደማይጠግበው እንደደርግ ሃገር ሊለውጡ የሚችሉ እና ተስፋ የሆኑ የተማሩ ወጣት ትውልዶችን በጠራራ ጸሃይ እየደፋ ይገኛል::የወያኔ ወንጀሎች ተነግረው አያልቁም አሁን ዋናው አትኩሮት ወንጀል እና ወንጀለኞችን ማስወገድ ያስፈልጋል የሚለው ጊዜ ላይ ደርሰናል::ወያኔ ከአገዛዝ ሂደቱ በጎሳ ፖለቲካ ከፋፍሎ መግዛት እንዳልተሳካለት እያየው ነው::በፕሮፓጋንዳ እና በሃሰት መግዛትም ሕዝቡን እንዳስመረረው እያየው ነው::ራሱም ወያኔ በራሱ ላይ መስክሯል::ታዲያ ም እየተጠበቀ ነው ማስተዳደር መምራት ካልተቻለ ስልጣን መልቀቅ አንድ እና ብቸኛ መፍትሄ ነው::መርጦኛል ያለው ሕዝብ አልመረጥኩህም ብሎ እስከ ሕይወት መስዋትነት ከፍሎ በተግባር ወያኔን እንደማይፈልገው አሳይቷል::ዝም ያለውም ሕዝብ ለውጥ ፈላጊ እደሆነ መዘንጋት የለብንም::ዝምታ በራሱ ከባድ እና አደገኛ ተቃውሞ ነው::

የሃገሪቱን ችግር ለመፍታት በሚል በሁለት በኩል የተሳለው የወያኔ ምላስ ሕዝብን ለማጭበርበር እና ጊዜ ለመግዛት የማይቧጥጠው ነገር የለም::ከዚህም አንዱ የሃስት ይቅርታውን ተከትሎ ምሁራን ከሚላቸው ጋር ስብሰባ መቀመጡ አንደናው የማዘናጊያ መገድ ነው:;የወያኔ አገዛዝ የምሁራንን ምክር ቢሰማ ኖሮ አሁን የምናያቸው ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ባልተፈጠር ግድያዎች እና እስሮች እንዲሁም ሕዝብ ማፈናቀል ማሳደድ እና መዝረፍ ሙሰኝነት በሃግሪቱ ልቀው አይገኙም ነበር::ወያኔ ካሁን በኋላ ጊዜው አልፎበታል::ያለው እድል ስልጣኑን ለሕዝብ ማስረከብ ብቻ ነው:; ዘረፋ እና የሕዝብ ደም መጠጣት የለመዱ የወያኔ ባለስልጣናት ሰይጣናዊ ባህሪያቸውን ይቀይራሉ ማለት አንድም የዋህነት ሌላም ሞኝነት ነው::ስለዚህ ይሃገሪቱ ችግሮች ብቸኛው አማራጭ ወያኔን አውርዶ ሕዝባዊ መንግስት መመስረት ብቻ ነው::ብሄራዊ መግባባት የሚፈጠረው ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ሲኖር እንጂ ምሁራንን ሰብስቦ በመጮህ አይደለም::ጊዜ መግዣ አጀንዳ !‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬