ሰብዓዊነትንና ፍትሕን ከማያውቀው ከሕወሓት ኣገዛዝ የሕግ የበላይነትን መጠበቅ ቅዠት ነው።

ሰብዓዊነትንና ፍትሕን ከማያውቀው ከሕወሓት ኣገዛዝ የሕግ የበላይነትን መጠበቅ ቅዠት ነው።


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኢትዮጵያ ራሳቸውን የፍትሕ ኣካላት ብለው በሚጠሩ የሕወሓት ታዛዥ እቃዎች የሃብታሙ አያሌውን ጉዳይ ከፍትሕ ውሳኔ ይልቅ በፖለቲካ ገመድ ተብትበውት ይገኛሉ እንዲሁም በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች በኣደጋ ውስጥ ሆነው ሲገኙ የወያኔ ኣገዛዝ የፖለቲካ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ለውጥ በጠየቁ ሃይሎች ላይ የሚሰራው ግፍ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው፤የአንድ ሃገር ህግ የህዝብን ትኩሳት እና ጥያቄዎች ይዞ መጓዝ ሲኖርበት በሃገራችን ግን የህግ የበላይነትን የፖለቲካ ትኩሳቶች እያሽመደመዱት እንዳይከበር እና እንዲደፈጠጥ እያደረጉት ይገኛሉ:; አንድ ህዝብ ባላረቀቀው እና ባላጸደቀው ህግ ሲገዛ የህግን ትርጉም እንደማያውቅ ታሳቢ አድርጎ በህዝብ ነጻነት ላይ የሚደረጉ የፖለቲካ ጨዋታዎች እንኳን በበሰለው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይቅር እና በሌላውም ባልሰለጠነ ህዝብ ላይ ሊተገበር መድፈር ራስን እንደመናቅ ይቆጠራል:: ወያኔ ራሱ አርቅቆ እና አጽድቆ ህጎችን በማውጣት ከፈለገም በመሻር በመቀየር በመገለባበጥ በመተርጎም ህዝቦች የራሳቸውን መብት እና ነጻነት እንዳያገኙ በከፍተኛ ደረጃ መሸራረፎችን እየፈጠረ ነው::

ባለስልጣናት የወንበር ግዝፈታቸውን ተጠቅመው የተለያዩ ውሳኔዎችን ትእዛዞችን ተግባራትን በስልክ በደብዳቤ በቀላጤ ወዘተ የህግን ስርኣት ባልተከተለ መልኩ እያሽከረከሩት ከህግ የበላይነት ላይ በድንፋታና በትእቢት በመጓዝ ላይ ሲሆኑ ይህንን ያየ የበታች ካድሬ እንዲሁ ህግን እና ስራትን ባልትከተለ መንግድ የህዝቦችን ህልውና ገደል ከቶታል:: ከበላይ ባለስልጣናት ባልተናነሰ እንዲሁም በበለጠ ማለት ይቻላል የወያኔ ካድሬዎች እና ተባባሪዎቻቸው በአገሪቱ ላይ ስርኣት አልበኝነት እና ህገወጥነት እንዲሰፍን እየሰሩ ነው::ይህ ደግሞ ህዝብ በስርኣቱ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጎታል::

ባለስልጣናት ለህግ እና ለስርኣት ተገዢ አለመሆናቸው ህግና ስርኣት ለእነሱ ተገዢ እንዲሆን ማድረጋቸው ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው;: የህግን የበላይነት ማረጋገጥ የተሳነው ስርኣት የወለዳቸው ስብርባሪ ህወሓት መራሽ መንግስታት የህዝቦችን የመኖር መብት ደፍጥጠዋል::በሃገራችን ውስጥ ላለፉት 25 አመታት ተንሰራፍቶ ያለው የአንድ ፓርቲ ህገወጥ አገዛዝ ለህዝቦች ነጻነት የሚከፈለውን መስእዋትነት እንደ መንግስት ሳይከፍል ህዝብን በማሸበር እና በማወናበድ የህግ የበላይነትን ደፍጥጦ ለስልጣኑ ብቻ እየተራወጠ ይገኛል::በሃገሪቱ የህግ የበላይነት የተከበረ ጊዜ ስልታንህ ያበቃል የተባለ ይመስል ከበላይ ባለስልጣናት ጀምሮ እስከ በታች ካድሬዎች ድረስ የህግን የበላይነት ክደዋል::
ከህገመንግስት እንከ ምርጫ ህግ; ከፍርድ ቤቶች ህግ እስከ ዜጎች የመኖር ህልውና አጠቃሎ የተደፈጠጠባት እና መንግስታዊ አሸባሪነት በነጻነት የሚራመድባትን ኢትዮጵያ የመላው ዜጎች አገር በማድርገ እኩልነት ፍትህ እና ሰላም የሰፈነባት አገር እንድትሆን በትግላችን የምናረጋግጥበት ጊዜ ላይ መሆናችንን አውቀን በጋራ ትብብር ተከባብረን እና ተቀናጅተን ወደ መጨረሻው ምእራፍ እንድንደርስ እና የወያኔን አምባገነን ስርአት እንድንቀብር ጥሪዬን አስተላልፋለሁ::እንዲሁም ሃብታሙ ኣያሌው ኣሁን ካለበት የሕመም ስቃይ ወጥቶ ለተሻለ ሕክምና ከሃገር እንዲወጣ ሁላችንም በመረባረብ ሕይወቱን በመታደግ የዜግነት ድርሻችንን ልንወጣ ይገባል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.