የሕወሓት እባቦች ዛሬም ለመከፋፈል ኣሰፍስፈዋል። ዘረኞች ያዩት የሰሙት ሁሉ ዘረኛ ይመስላቸዋል።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የኣማራና የሌሎች ሕዝቦችን ጥያቄ ለማኮላሸት ከኦነግና ኣስተባባሪዎቹ ጋር መደራደር ያስፈልጋል የሚል ፉጨት የሴራ ፕሮፖዛል ሹሩባ ከሚጎነጉኑ ኣስመሳይ ከሕወሓት ካድሬዎች ተጀምሯል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕወሓት የበላይነት በቃ በማለት የበይ ተመልካች ሆኜ በድህነት መኖር ኣልሻም ሲል ኣደባባይ በመውጣት ብሶቱን እያሰማ ይገኛል፥ የኦሮሞ ሕዝብ የጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ቀጥሎ ኣማራው ክልል በመድረስ ሕዝቦች በኣንድነት በጋራ ለመታገል ወንድማማችነታቸውን ለማጠንከር እጅ ለእግ በመያያዝ የጋራ ጠላታቸው ወያኔን ለማጥፋት ቆርጠው ተነስተዋል። የኦሮሞ ሕዝብ ኣገዛዙን ሲቃወም ኣማራ ሕዝብ ስር ሲወሸቅ የኣማራው ሕዝብ ሆ ብሎ ሲወጣነት ኦሮሞው ሕዝብ ስር የሚወሸቅ የነበረው ሕወሓት በጎጥ እየከፋፈለ ለመግዛት ያለመው እቅድ ስለተነቃበት ኣደገኛ ድንጋጤና አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።

በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ብአዴን የሚሉትን ጀሌውን ይዞ የኦሮሞን ሕዝብ ተቃውሞ ለመጨፍለቅ ያደረገው ሩጫ በሽንፈት የተጠናቀቀበት ሕወሓት ሽንፈቱን ውጦ ሳይጨርስ የኣማራው ሕዝብ ሕወሓትን ቅንድቡን ብሎት ቀልቡን ገፎታል።ይህን ተከትሎ የሕወሓት ካድሬዎችና አቀንቃኞች ኣንድ ጊዜ ፌዴሬሽኑ ፈርሶ ኮንፌዴሬሽን ይመስረት ሌላ ጊዜ ኣማራው ትጥቅ ይፍታ ደጉ ኣንዳርጋቸው ይደምሰስ ሲላቸው ደግሞ ከነኣለቆቻቸው በድርድር ስም እና በሃይማኖት እበቶች በኩል የሕዝብን ትግል ለማኮላሸት ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ።

ሕወሓትን ማመን ቀብሮ ነው ሕወሓት ድርድር ስትል ስኳር የሆነ ቅድመ ሁኔታ ስታቀርብ የተንኮል ጉድጓድ እየማሰች እንደሆነ በኣንክሮ ልናውቅ ይገባል፤ የኣማራና የሌሎች ሕዝቦችን ጥያቄ ለማኮላሸት ከኦነግና ኣስተባባሪዎቹ ጋር መደራደር ያስፈልጋል የሚል ፉጨት ከሕወሓት ካድሬዎች ተጀምሯል። በኦሮሚያ ውስጥ ያለው ችግር አሁኑኑ ዘላቂና አቃፊ መፍትሔ ይፈለግለት፤ የሚሉት የሕወሓት አቀንቃኞችና ካድሬዎች የኦሮሞን ሕዝብ ዝም ኣለማሰኘታችን በዘረጋነው የጎጥ ፖለቲካ ላይ ትልቅ ችግር ስለፈጠርን ኣደጋ ሆንኦብናል የኦሮሞን ሕዝብ በድርድር እና በተለያዩ ሰበቦች ዝም ማሰኘት ከቻንል በኦሮሞ ሕዝብ ስር ተወሽቀን ሌላውን ሕዝብ ለመምታት ይቻለናል በሚል የወረደ አስተሳሰብ ይዘው ተሰይመዋል።

ድርድር የሚጠላ ሰላም የሚገኝበትን መንገድና መፍትሄ የሚቃወም ምንም ሃይል የለም። በሕወሓት ቤት ግን ድርድር ውይይት የሚሉ ብልሃቶች ጊዜ መግዣ ጠላትን ለይቶ መምቻና ተቃውሞን ማጥፊያ ተስፋ ማስቆረጫ መሆናቸው ያለፉ ተደጋጋሚ ሂደቶች በግልጽ ይመሰክራሉ። ኣሸባሪና ጸረ ሰላም ጸረ ሕዝብ ናቸው ብሎ ከፈረጃቸው ጋር ለመደራደር መዘጋጀቱ ሕወሓት በሕዝቡ የተፈጠረበትን ጫና ያሳያል።ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን የሚችለው የኣንዱን ድምጽ ኣግልሎ የኣንዱን ድምጽ ይዞ ሳይሆን ሁሉም የሚሳተፍበት የሽግ ግር መንግስት ሲመሰረት ቢሆንም ሕወሓት እባብ እና መሰሪ ስለሆነ ሕወሓትን ማመን ቀብሮ ነው። ባለፉት ሃያ ኣምስት ኣመታት የተጫወታቹበት የከፋፋይነት ካርዳቹህ ኣሁን ላይ በሕዝብ ስለተነቃበት ተቀባይነት የለውም።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬