በፍርሃት የሚኖር ፈሪ ኣገዛዝ – 11,607 ሰዎች ታስረዋል።

በፍርሃት የሚኖር ፈሪ ኣገዛዝ

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ኣምባገነኑ ሕወሓት ኮማንድ ፖስት ብሎ በገዳይ ወታደሮቹ ያደራጀው ቡድን 11,607 ሰዎችን ማሰሩን ስንሰማ ስርዓቱ ምን ያህል የሕዝብ ፍራቻ ውስጥ እንደሚገኝ ቁልጭ ኣድርጎ ያሳያል። በራሳቸው የማይተማመኑ ለስልጣናቸው ጥም ሲሉ ያልታጠቁ ንጹሃንን ከየቤታቸው በመውሰድ ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ መክተታቸው የሕዝብ ተቃውሞ ስጋት ውስጥ እንደጨመራቸው ኣመላካች ሲሆን ኣገዛዙ የሕዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ኣፈናን መፍትሄ ማድረጉ ከባድ ፍራቻ ውስጥ መዘፈቁን ይመሰክራል።

ከየቤታቸው የታፈኑ ለዝብ ተቆርቋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ ሲሆን የዞን ዘጠኝ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ዛሬ ማለዳ 12 30 ገደማ ኮማንድ ፓስት ይፍለግሃል በሚል ሰበብ ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ሃይሎች ተይዞ እዛው መኖሪያ ቤቱ አካባቢ በሚገኝው 06 ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩ ታውቋል። ኣሰርነው ብለው ያመኑትን በኣስር ሺዎች ቁጥር ኣሳንሰው ሲሆን ቁጥራቸው ውስጥ ያላስገቧቸው በሺዎች የሚቆጠር የታፈኑ ወጣቶችን ቤት ይቁጠራቸው።

ኣገዛዙ በፍርሃት የሚኖር ፈሪ በመሆኑ ብቻ ኢትዮጵያውያንን እያፈሰ በየማጎሪያ ካምፑ ኣስሮ ይገኛል። የሕዝብ ንቅናቄ ቀጣይነት ለስርዓቱ ኣደጋ መሆኑን ስለሚያሳይ የሕዝብ የጋራ ተቃውሞ በርትቶ ሊቀጥል ይገባዋል። የለውጥ ፈላጊ ሕዝቦችን ንቅናቄ ግድያ እስርና ኣፈና ኣይመልሰውም። ሕዝብ ኣሸናፊ ነው ሕዝብ ትክክል ነው። ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል። #Miniliksalsawi