ሳይቃጠል በቅጠል ሊታሰብበት የሚገባ እውነታ - የጋራ ሃገራዊ ዲሞክራቲክ ኣጅንዳ ::

ሳይቃጠል በቅጠል ሊታሰብበት የሚገባ እውነታ
ዘረኝነቱ ይራገባል! ይራገባል! ይራገባል! የጋራ ሃገራዊ ዲሞክራቲክ ኣጅንዳ የለም ሁሉም እኔ ኣውቅልሃለሁ እያለ ነው ሰዎችን ማዋረድና መሳደብ ፋሽን ተደርጎ ተይዟል። የማግለል የጥላቻና የፍረጃ ፖለቲካ ስለተስፋፋ የለውጥ ሃይሉን በኣንድነት ሰብስቦ የሚያታግል ጠፍቷል።በማይረባ ኣጀንዳ ላይ የሚልፈሰፈስ ጨምሯል።

መሬት ላይ ያሌለ ሃቅ በየማህበራዊ ድህረገጹ ሲፖተለክ ይሰማል።ትላንት ስለ ኢትዮጵያ ከኛ በላይ ማንም የላትም ሲሉ የነበሩ በጥቅም ተገዝተው ኢትዮጵያ ትፈረካከስ ዘንድ ዘምተዋል። ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለመመስረት ከመድከም ይልቅ ለፍጅት ፖለቲካ ቅድሚያ ተሰጥቷል።ከሃገር ወዳዱ ይልቅ የመኖሪያ ፈቃድ ፈላጊው ያልበሰለ ፖለቲከኛ ሲያሞጠሙጥ ይውላል። የመኖሪያ ፈቃድ ፈላጊዎች ሕልማቸው ተሳክቶ ሲነሱ ሃገር ቤት ገብቶ ወያኔን ኮንዶሚኒየም እንዲሰጣቸው በመለመን የሚቀድማቸው ኣልተገኘም። ትግሉ ይህ ነው።

ሃሳብን በሃሳብ ከማሸነፍ ይልቅ ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ ሰዎችን ታግሎ ከመደምሰስ ይልቅ ፎቢያ ስር ሰዶ ነግሶ የፖለቲካ ጥላቻን ወልዷል፤ካለፈው መማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች ከመኖናችንም በላይ ትግላችን ሁሉ የሞኝ ሩጫ ኣድርገነው ፍጥነታችን ባለህበት እርገጥ ሆኗል። ሊታሰብበት የሚገባ እውነታ - የጋራ ሃገራዊ ዲሞክራቲክ ኣጅንዳ :: (#ምንሊክሳልሳዊ) Minilik Salsawi - mereja.com