የሕወሓት ጥልቅ ተሓድሶ :- የአዲስ አበባና የመቀሌ ኣንጃ የሚባል ቃል የተቃዋሚን ጆሮ ለማደንቆር የተሰራ ሴራ ነው። TPLF Reform is Lie

የሕወሓት ጥልቅ ተሓድሶ :- የአዲስ አበባና የመቀሌ ኣንጃ የሚባል ቃል የተቃዋሚን ጆሮ ለማደንቆር የተሰራ ሴራ ነው።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) - ሕወሓቶች ጓዳዊና ድርጅታዊ ፍቅራቸው ኣይጣል ነው። በኣደባባይ የተባሉ ይመስላሉ እንጂ ውስጥ ውስጡን ግን ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ዲሲፕሊን እና መደማመጥ ኣላቸው። በደጅ በሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ሕወሓት እንዳበቃላት እንደፈረሰች እንደተከፋፈለች ተደሮ የሕዝብን ስሜት ለመሳብ የሚደረጉ ውሸቶች የውስጥ እውነታውን ይደብቁታል ኣደባባይ ላይ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ኣስመሳይነት ሲታይባቸው የውስጥ ጥንካሬን ግን በተርታ ሰንሰለት እየገነቡት ይጓዛሉ።

በቅርቡ በኣማራ ክልል እና በትግራይ ክልል መካከል የሚደረገው የድንበር እና የማንኔት ጥያቄ ፍጥጫዎች ኣቶ ኣባይ ወልዱንና ኣቶ ደጉ ኣንዳርጋቸውን ሲወነጃጅሉ የከረሙት የወያኔ ፕሮፓጋንዲስቶች ስራቸውን ኣጠናቀው ኣዲስ የፕሮፓጋንዳ ኣጀንዳ ለማምጣት እየሰሩ ነው። በመቀሌ እና በባህር ዳር የተካሄደው የፓርቲዎች ግምገማ ተጠናቆ (ችግሮች ?) በሰላም እንደተፈቱ እየሰማን ሲሆን ምን ያህል በሕዝብ ትከሻ ላይ ኣምባገኖች እየዘለሉ እንደሚገኙ የመሰከረ ግምገማ ነበር። በዋናነት የሚነኩትና የሚወገዱት የብአዴን ካድሬዎች ሲሆን ሕወሓት በግምገማዋ ተማምላ እንጂ ተጣልታ ኣልተለያየችም።

በራሳችን የሰጡንን ኣጀንዳ ተከትለን በፈጠርነው የሕወሓት የኣዲስ ኣበባ ኣንጃና የመቀሌ ኣንጃ ንትርኩ በሰላም ተፈቶ ኣባይ ወልዱ ከስልጣን ኣልወርድም ብሎ ምናምን በሚል የደጅ ፕሮፓጋንዳ የውስጥ መሃላ የሕወሓት ግምገማ ተጠናቋል። ለማን ደስ ይበለው ብለን ነው ኣባይ ወልዱን የምናባርረው የሚል ውሳኔ ጸድቋል። ለዚህ ደጋፊ የሚሆን ፕሮፓጋንዳ ደሞ የፌዴራሉ ሕወሓት ኣፍሮ መመለሱ እንዲደሰኮር ተደርጓል። ሕወሓቶችን ማመን ቀብሮ ነው። በኣደባባይ በተላላኪዎቻቸው የሚያስነዙት ፕሮፓጋንዳና በጓዳ የሚሰሩት የፖለቲካ ሴራ የተለያየ ነው።ከሕወሓት ውስጥ ማንም ኣይወገድም ከስልጣን ኣይነሳም።የኣዲስ ኣበባና የመቀሌ ኣንጃ የሚባል ቃል የተቃዋሚን ጆሮ ለማደንቆር የተሰራ ሴራ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ