ሻዕቢያና ወያኔ አንድ ላይ ነው እንዴ ስብሰባ የተቀመጡት ?

ሻዕቢያና ወያኔ አንድ ላይ ነው እንዴ ስብሰባ የተቀመጡት ?

የመቀሌው ስብሰባ መራዘም ሲገርመን የሻዕቢያ ሰወች በመቀሌ ሆቴሎች መታየት ፤ አይቶ ኢሳያስም በትግሪኛ ንግግራቸው ጫፉን ተንፍሰዋል ፤ ድርድሩ ወደ ስምምነት መቃረቡ ወያኔን ከሞት እንደማያድን መናገር ይቻላል ።

አንቀጽ 39ን ለመተግበር ቅድመ ሁኔታ የሚያመቻች ኮሚቴ በደህንነቱ ሹም መሪነት መዋቀሩም ሌላው የመቀሌ ምንጮች ጥቆማ ነው ፤ የፖለቲካ ለውጥ ማምጣት ራስን መግደል ነው ብሎ የሚያስበው ወያኔ መጭውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እድል በደም ለማጨቅየት ቅጥረኞቹን እያሰራ ነው ።

ራሱ ባቋቋመው የፌዴራል ስርዓት ውስጥ የተፈበረከው የሱማሌ ክልልም የፌዴራል መንግስት ተብየውን ሞልጮታል ፤ ቀጣዩ ጥያቄ የሱማሌ ክልል አንቀጽ 39 ነው ፤ ከዛ በፊት በክልሉ ያሉትን ሌሎች ብሔሮች አባሮ እንዲጨርስ ተነግሮታል ፤ ይህንንም ማስተባበር የሕወሓት ስራ ነው ።

ከኦሕዴድ ይልቅ የዲያስፖራ ኦሮሞ አክቲቪስቶችን ከነሚዲያቸው ማጠናከር ተመራጭ ሆኗል ፤ ይህ ደግሞ አባዱላ ሚኒሶታ ድረስ ሔዶ የጀመረውን ለማስጨረስ ስልጣኑን ለቋል ። አገሪቷ በግጭት እንድትተራመስ መቀሌ ላይ ሴራ እየተነደፈ ነው ። የበሉባትን ቱጃር የሆኑበትን ምድር አኬልዳማ ለማድረግ ሲያሴሩ በገዛ ተንኮላቸው ተጠልፈው መውደቃቸው የማይቀር ሐቅ ነው ፤ ውደድም ጥላ እውነቱ ይህ ነው ። #MinilikSalsawi