"ባንድ ወንጭፍ አማራውን በፍጥነት!!!"ሕወሓት ብኣዴንን እየዋጠው ነው!!

ከዚህ መሃል  ቁጥር 2 አቶ ገብረዋህድ ትግሬ ናቸው 
ሕወሓት ብኣዴንን እየዋጠው ነው!!
"ባንድ ወንጭፍ አማራውን በፍጥነት!!!"

ከበረሃው ትግል ጀምረው አብረው እየነጎዱ የመጡት ሕወሓት እና ኢህዴን በኋላም ብኣዴን በአሁኑ ወቅት አጅግ ከባድ የሆነ የፖለቲካ ፊቲጫ ውስጥ መሆናቸውን በዙሪያቸው የሚደረጉት ድርጊቶች እያሳበቁ ነው::በሽግግር መንግስቱ ጊዜ ታምራት ላይኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ በነበረበት ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ዙሪያ የቀድሞ የኢህኣፓ ሴሎች መሰባሰብን ተከትሎ እንዲሁን ጣምራት የነበረው አቋም ተለክቶ በኤርትራ ጉዳይ ዙሪያ ያለው አመለካከት ተመዝኖ በወያኔ እና በሻእቢያ ጥርስ ውስጥ ገብቶ በሙስና ተፈርጆ በከባዱ አንገቱ እስኪሰብር ቀጥቅውት ከፖለቲካ ጨዋት ውጭ አድርገውታል::
እንዲሁም የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበረውን ሙሉአለምን በፈንጂ ባህር ዳር ላይ አጥፍተውታል:: የሕወሓት የፖለቲካ ቁማር በዚሁ አላበቃም መለስ ብለን ካየነው ብዙ ነው.....እያለ የቀጠለው የሕወሓት መጦ መትፋት እነ አዲስ ለገሰን እነ ተፈራ ዋልዋን እና ሌሎች የብኣዲን አባላትን ከህዝብ ጋር ከተቀላቀሉ በሁዋላ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሸተዋል በሚል መርዛዊ ጥላቻ በጡረታ በጤና ሰንክ በአምባሳደርነት ከአጠገቡ አባሯቸዋል::ለሃገራቸው ይሰራሉ ተብለው የተገመቱ የተጠበቁ የብኣዴን ታጋዮችን ወዴት እንደደረሱ እንኳን ሳይታወቅ አንጠባጥቧቸዋል:: በተጨማሪም በወታደሩ ክፍል የነበሩትን የብኣዴን ጀነራሎች እና የበታች መኮንኖች ለስልጣን ያሰጋሉ በሚል በተለያዩ እስር ቤቶች በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እና በፖለቲካ ስም አስሮ ይገኛል::በቱረታም አባሯል::
ይህን ይህን ያን ያን  ...እያልን ያለንበት ላይ ስንደርስ ደሞ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በስልጣን ሽኩቻ ዙሪያ የተለያዩ መፋጠጦች እንደነበሩ እንዲሁም እንዳሉ ይታወቃል::ያ መፋጠጥ እና መሿኮት ቀጥሎ በኢህኣዴግ ስብሰባ ላይ በጡዘት ወቶ የነበረ ቢሆንም አልስፈላጊ አደርባይ ሙሰኛ በሚል አደገኛ እንደ ጌታቸው ሴኩትሬ አባባል "የገማ ቂቤ" እየተቀቡ አፋቸውን እንዲይዙ ተደርጓል ብኣዴኖች::
ሕወሓት ለያዘው አላማ እንቅፋት እንደሚሆንበት ከጅምሩ በብኣዴን ላይ የሾሉ ጥርሶቹን እየደጋገመ ሲሞርድ እንደነበር ይታወቃል:; ብኣዴኖች በተለያየ ጊዜያት በሙስና እንዲዘፈቁ እና ማስረጃ እንዲያዝባቸው በአጠገባቸው በሚመደቡ የህወሓት አባላት ከፍተኛ የሆነ ውስወሳ እና ክትትል በማድረግ መዝገባቸውን በሙስና ሰነዶች በመሙላት ለማስወገድ ሚናውን ተጫውቷል:: አሁንም እየተጫወተ ነው:: እንዲሁም ይህንን የፖለቲካ ቁማር በደቡብ ግንባር ላይም እየተጫወተ ይገኛል::
ሕወሓት ነባር የብኣዴን ታጋዮችን ሰብሰቦ ካስወገደ በኋላ በአማራው ክልል የተወለዱ አማርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያንን እና የትግራይ ተወላጆችን በመሰግሰግ ጉዞውን ሊቀጥል እየተራወጠ ይገኛል::

ህወሓት በዚህ ሰሞን ደሞ በብኣዴን ባለስልጣናት ላይ ዘመቻ ከፍቷል:: ዘመቻው ሁለት አላማዎችን የያእ ነው እንጂ በፍጹም ሙስና አይደለም::በእርግጥ ሙስና የለም ብለን አንናገርም ሆኖም ሊበሏት ያሰቧትን... እንደሚባለው በፖልርቲካው ላይ ችግር እየፈጠሩ ያሉትን ባለስልጣናት ማስወገድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ሙስናን እንደቀዳሚ ተደርጎ ለህዝብ ማስነገር አስፈላጊ ነው ...ለመሆኑ በሙስና ረገድ ከፍተኛውን የሙስና ባላባቶች የሆኑ የሕወሓት ባለስልጣናት እና የጦር ጄኔራሎች ለምን አይከሰሱም ? አይባረሩም? አይጠየቁም??...ባለፈው ጊዜያት ከጸረ ሙስና ኮሚሽን ዘሎ የወጣ መረጃ እንደጠቆመው የህወሓት አባላት በሙስና መዘፈቃቸውን የሚያሳይ እውነተኛ ምስክር ነው::
ሕወሓት ውስጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የሙስና ድርጊት እንደት ነው ሊወገድ የሚችለው?? ለምንስ የህወሃት ሙሰኞች ለፍርድ አይቀርቡም ስልጣናቸውንስ አይነጠቁም?? የጦር ጄኔራል የሆኑ የሕወሓት ቅምጥ መኮንኖችስ ለስልታን ጥበቃ በሚል ሰበብ ለምን ዝም ይባላሉ?? ይህን እና ተመሳሳይነት ያላቸው ጥያቄዎች ለመመለስ የሚከብድ ነው ለወያኔ::
በዚህ ሳምንት ደሞ እንደፋሽን የተያዘው ነገር ቢኖር ብኣዴኖችን መግቢያና መውጫ አሳጥቶ አፋቸውን በማስያዝ ምንም አይነት ጥያቄ እንዳይጠይቁ እና አንገታቸውን እንዲሰብሩ ማድረግ ነው::
ትላንት እና ጠዋት የደረሱን ማስረጃዎች እንዳመለከቱን ከሆነ መገናኛ አከባቢ በሚገኘው የጉምሩክ ዋና መስሪያቤት ውስጥ ሲቭል በለበሱ ደህንነቶች እና በፌዴራል ፖሊስ የታጀበ ኦፕሬሽን እየተደረገ እንደሆነ ቢያመለክትም በውስጥ የነበሩ ከ200 በላይ ሰራተኛች የሃገር ጉዳይ ነው ተብለው እንደወጡ እና አቶ መላኩ ብጫውን ታግቶ እንደነበር እና በኋላም በምን እንደሆነ ሳይታወቅ አቶ ገብረዋህድ እና ሌሎች የመምሪያ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተነግሮ ነበር :; ይህንን ለማጣራት በተደረገ ሙከራ መረጃ የሚሰጡን የብኣዴን እና አንዳንድ የሕወሓት አባላት ስልካቸውን እስከ ማታ ድረስ እንዲዘጉ ታዘው ነበር::
መረጃዎች እንደጠቆሙት በአቶ መላኩ ፈንታ እና በአቶ ገብረዋህድ መካከል ምንም አይነት መግባባት እንደሌለ እና በኣንድነት ሙስና ይፈጽማሉ ሊያስብል የሚችል አንድም ሁኔታ የለም ይላሉ እንደውስጥ አዋቂዎች እምነት:: ገብረዋህድ በጉምሩክ ባለስልጣን ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ ሲሆን አቶ መላኩ እንደበላይነታቸው ሙሉ ስልጥኣን አልነበራቸውም:: አቶ መላኩ የፈረሙትን ገብረዋህድ ይሽር እንደነበር እና ይህም ጉዳይ ጥቆማ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደርሶ ውሳኔ ደፍሮ የሰጠ አልነበረም::ገብረዋህድ ማለት እጅግ ቀንደኛ ዘረኛ የሆነ ሰው እንደሆነ ይታወቃል ስለዚህ ኢትዮጵያ ከሚለው መላኩ ጋር ተስማምቶ ሙስና ይሰራል ማለት ዘበት ነው::ታማኝነትም የለውም ::ገብረዋህድ ባንድ ወቅት በመስሪያ ቤቱ እነና ስርኣቱ ህልውናችን አንድ ነው ያለ ደፋር እና ዘረኛ ሰው ነው በሙስና ተብሎ ዘብጥያ መውረዱ አጠያያቂ ሲሆን እንደኔ ብኣዴኖችን ለመጥለፍ የተሸረበ ሴራ ነው::
ገብረዋህድ ከወይዘሮ አዘብ ጋር ቀረቤታ እንዳለው ይታማል:: ከላይ እስከ ታች በጉምሩክ ውስጥ የሞሉት የትግራይ ተወላጆች በሙስና ተጨማልቀዋል::እንዲሁም ስርኣቱ እጅግ ከሚንከባከባቸው ሰዎች አንዱ ነው:: በተለያየ ጊዜ የህወሃት ባለስልጣናት እና የጦር ጄኔራሎች በተለያየ ጊዜ ከውጪ የሚያስገቧቸውን ማንኛውም ነገሮች ጉምሩክ በነጻ እንደሚያሳልፍላቸው ሲታወቅ የህ ደሞ የገብረዋህድ ተትእዛዝ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ::
በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ጸሃፊ ሆና የምትሰራ አንዲት የመሃል አገር ሰው የሆነች ትግሪኛ ተናጋሪ እንደነገረችኝ በተለያየ ጊዜያት ከጄኔራሎቹ አልፎ እሷ ራሷ ከተለያዩ አገሮች የምታስገባቸው እቃዎች በነጻነት ቤቷ ድረስ ተጭነው እንደሚመጡ አጫውታኛለች::
ይህን ተከቶ አቶ ብርሃነ ሃይሉ እና አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው በአማራነት ከህወሃት ተባረዋል :: ህወሓት ወዴት እያመራች ነው?? አማራውን እያደነዘዘች ማጥፋት :: ይህ ሊታገሉት የሚገባ ጉዳይ ነው:: ምክንያቱም ባለፉት ጊዜያት የተደረጉ ጉዞዎች ያልጣሟቸው ባለስስልታናት ጥያቄ እያቀረቡ ባሉበት በዚህ ወቅት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች መመልከት እና ማመዛዘን የራሳችን ድርሻ ነው::

ህገመንግስቱን ማክበር ከገዢው ፓርቲ ይጀመር!!!


ህገመንግስቱን ማክበር ከገዢው ፓርቲ ይጀመር!!!
ምንሊክ ሳልሳዊ
ዞን 9 ኢ-መደበኛ የአራማጆች እና የጦማሪያን ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ማኅበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ የተለየ እና ወገናዊ ያልሆነ ታረክ ለመፍጠር እየሠራ የሚገኝ የወጣቶች ኢትዮጵያውያን በ2005 ዓ.ም ሊደረጉ ከታቀዱት አራት የበይነመረብ ዘመቻዎች ሦስተኛው የፊታችን ረቡዕ ሚያዝያ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አርብ ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ያካሂዳል::
ሶስተኛው የበይነ መረብ ዘመቻ "ዲሞክራሲን በተግባር እናውል፤ የሰላማዊ ሰልፍ መብታችን ይመለስ!" በሚል መሪ ቃል ይካሐዳል:: ሦስተኛው ዘመቻ መንግሥትን እና ሁላችንንም በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 30 የሰፈረውን ‹ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት እንድናከብር› የሚጠይቅ ነው፡፡
*********************************************************************
 በዚህ ጉዳይ ላይ የራሴን አጠር ያለ አስተያየት ማስቀመጥ ስላለብኝ ይህንን ለማለት እወዳለሁ::
በሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የዲሞክራሲ ጮራ እንዲፈነጥቅ በተለያዩ ጊዜያት የተነሱ ኢትዮጵያያን ላለፉት 21 አመታት የትግል አስታውጾ አድርገዋል:: እንዲሁም የኢሕኣዴግ ሰራዊት የተሰዋለት አላማም ይህንን የህዝቦች ነጻነት እና እኩልነት ለማረጋገጥ ነበር::በህዝቦች የትግል ሂደት እና መስእዋትነት ተረቆ ጸድቋል የተባልነው ህገመንግስት ግን ከዚህ በተለየ መልኩ የወረቀት ላይ ጀብደኛ ሲሆን በማንም መመሪያ እና የስልክ ቴዛዝ ሲሻር እየተመለከት ነው::
ህገመንግስቱ በወረቀት ላይ ብቻ ህይወት ሳይዘራበት በተድፈነፈነ መልኩ አስፈጻሚ አቶ በግለሰቦች ያውም የህግን ምንነት ባልተማሩ እንደፈቀደ እየተተረጎመ የዜጎችን ህልውና ከመፈታተን አልፎ ማንነትን እስከማሳጣት ድረስ ዘልቋል:: ህገመንግስት የማፈኛ መሳሪያ እንዲሁም የማሰሪያ የመወርወሪያ የመግደያ መሳሪያ ከመሆን አልፎ ጥልቅ አምባገነንነት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል:: ይህ ማለት ህገመንግስቱ በተግባር አለመተርጎሙ ይህንን ፈጥሯል ማለት ነው::
ማንኛውም በሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ዜጋ በህገመንግስት መናድ እና መጣስ ጉዳይ እየተከሰሰ ወደዘብጥያ ማውረድ የተለመድ የየእለት ተግባር ሆኗል:;ከ1997/2005 ምርጫ በኋላ ደሞ የባሰ በረቀቀ መንገድ አዲስ ህግ ወቶለት አሸባሪ በሚል ዉንጀላ ህገ መንግስቱ እስከመረሳት ደርሷል::
የሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ዲሞክራሲያዊ መብቶች ሃገራችን ከተቀበለችው አለማቀፍ ድንጋጌዎች አንዱ ነው::ይህ ማለት ደሞ ሰዎች በማንኛውም ጊዜ የሚደግፉትንም ሆነ የሚቃወሙትን ጉዳይ በአደባብይ ወተው ድምጻቸውን ማሰማት ይችላሉ ማለት ነው :: ተረጋግጧል በተባለው  በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 30 የሰፈረውን ‹ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት እንድናከብር› በሚል ሰፍሮ ይገኛል::
ይህ አንቀጽ 30 ግን እንደ በላይ ህግ ሳይተይ ከ1997/2005 ጀምሮ በበታች ህጎች ተገድቦ ይገኛል:: የበላይ ህጎች የበታቾቹን በሚገድቡበት እንጅ የበታቾች የበላያቸውን በሚሸረሽሩበት ሂደት ዉስጥ አልም አልፋበት ባለማወቋ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዜጎቿን እያጣችበት እየተገፈፈችበት ነው::
የገዢው ፓርቲ እሱን ብቻ የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎችን እንዲደረጉ ከመፍቀድ ዉጪ የተቃውሞ ሰልፎችን በማኮላሸት ተቃዋሚዎችን ወደ እስር ቤት ያግዛል:: አሁን እንኳን በቅርቡ አለማቀፍ ማህበረሰብ የሚያወግዘው የፋሺስቱ ግራዚያኒን ሃውልት ግንባታ ለመቃወም የወጡ ዜጎች በጋራ ሃገራዊ ጉዳይ አብሮ መስራት የሚገባው ገዢው ፓርቲ ፖሊሶችን በማሰማራት አፍሶ ወደ እስር ቤት ወስዶ ካሰራቸው በሗላ ፈቷቸዋል :;ይህ የሚያሳየው እንግዲህ ምንን እንደሆነ እርሶው ይደምድሙት::
ስለዚህ  ይህንን የሰው ልጆች የማይገሰስ ህገመንግስታዊ መብት ገዢው ፓርቲ ማክበር ከራሱ እንዲጀምር እናሳስባለን::አመሰግናለሁ::ምንሊክ ሳልሳዊ
***************************************************************
ከዚህ በታች የምታነቡት የዞን 9 ሦስተኛው የበይነ መረብ ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው::ዲሞክራሲን በተግባር እናውል፤ የሰላማዊ ሰልፍ መብታችን ይመለስ!
ሦስተኛው የበይነ መረብ ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ

ዞን 9 ኢ-መደበኛ የአራማጆች እና የጦማሪያን ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ማኅበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ የተለየ እና ወገናዊ ያልሆነ ታረክ ለመፍጠር እየሠራ የሚገኝ የወጣቶች ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ ይህንን የምናደርግበት ዋና ዓላማ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገሪቷ ጉዳይ ያገባኛል ብለው ውይይት የማድረግ ባሕል እንዲያሳድጉ በማድረግ ሀገሪቷን በሁሉም መስኮች ወደተሻለ ደረጃ የሚያደርሱ ሐሳቦች እንዲወለዱ ለማመቻቸት ነው፡፡

የተከበራችሁ የዞን9 ነዋሪዎች፣ በ2005 ዓ.ም ሊደረጉ ከታቀዱት አራት የበይነመረብ ዘመቻዎች ሦስተኛው የፊታችን ረቡዕ ሚያዝያ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አርብ ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል፡፡ ሦስተኛው ዘመቻ መንግሥትን እና ሁላችንንም በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 30 የሰፈረውን ‹ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት እንድናከብር› የሚጠይቅ ነው፡፡

ሰላማዊ ሰልፍ እና ስብሰባ የማድረግ መብት ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ የተደረገለት ዜጎች ድጋፋቸውን ወይንም ተቃውሟቸውን ከመሰሎቻቸው ጋር በመሆን ሐሳባቸውን መግለጽ እንዲችሉ እና ያገባናል የሚሉት ጉዳይ ላይ ሐሳብ እዲለዋወጡ እና እንዲወያዩ ነው፡፡

የ1997 ዓ.ም ምርጫ ቅስቀሳ አካል የነበሩት የሚያዝያ 29 እና 30 ሰልፎች በኋላ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እና መሰብሰብ መብት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተወሰነ ጊዜ ተገድቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ከዛ በኋላ የተካሄዱ ጥቂት ሰላማዊ ሰልፎች የአንድ ወገን ሐሳብ የሚንጸባረቅባቸው እና ለዚያም ሲባል ይሁኝታን ያገኙ ብቻ ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ ከሚያዝያ 30፣ 1997 ወዲህ ተቃውሞን አስመልክቶ የተደረገው ሰልፍ የወ/ት ብርቱካንን መታሰር አስመልክቶ የተካሄደ ሲሆን 250 ሰዎችን ብቻ ያሳተፈ ነበር፡፡ በወቅቱ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች በሰልፉ ላይ ለሚኖረው የደህንነት ችግር ኃላፊነት እንዲወስዱ መጠየቃቸው የተሳታፊዎችን ቁጥር ለመቀነስ መገደዳቸው ይታወሳል፡፡

ፖለቲካዊ በሆኑ ጉዳች ዙሪያ የሚደረጉ ስብሰባዎችም ቢሆኑ በግልጽ ተአቅቦ ባይደረግባቸውም የተለያዩ አስተዳደራዊ ጫናዎችን በመፍጠር እንዳይካሄዱ የእጅ አዙር ክልከላ ይደረግባቸዋል፡፡ ከመንግሥት የእጅ አዙር ክልከላ ሲያልፍም የመሰብሰቢያ ቦታ አቅራቢዎች ከሚደርስባቸው ቅድመ ማስፈራራርያ ወይንም ይደርስብኛል ብለው ከሚያስቡት አስተዳደራዊ በደል የተነሳ መሰብሰቢያ አዳራሾችን ይከለክላሉ፡፡
የሦስተኛው ዘመቻ ዓላማ መሣሪያ ሳይዙ ሰላማዊ ሰልፍ እና ስብሰባ የማድረግ ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ላይ የተጣሉ ቀጥተኛ እና የእጅ አዙር ገደቦች እንዲነሱ መጠየቅ ነው፡፡

ዘመቻው በዋነኛነት የሚካሄደው ‹‹ፌስቡክ›› እና ‹‹ትዊተርን›› (#Assembly4Every1 እና #Demonstration4Every1 የሚሉ ኃይለቃሎችን) በመጠቀም ይሆናል፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ እና ስብሰባ የማድረግ ሕገ መንግሥታዊ መብታችንን በተመለከተ የተለያዩ ጽሑፎች በጦማራችን የሚወጡ ሲሆን በፌስቡክ እና በትዊተርም ላይም ይለቀቃሉ፡፡ በሁለቱ (የዞን9 እና የሕገ-መንግሥቱ ይከበር!) የማኅበረሰብ ገጾች ላይ ለዚሁ ዘመቻ ሲባል የተዘጋጁ አጫጭር ጽሑፎች ይሰራጫሉ፡፡ ዘመቻውን የሚመለከት ‹ባነር› ተዘጋጅቶ ዘመቻው በሚቆይባቸው ቀናት የተለያዩ ፕሮፋይል ምስሎችም ተዘጋጅተው የሽፋን ምስል እና የፕሮፋይል ፎቶ ይሆናሉ፡፡

በዚሁ አጋጣሚ ለመላው የዞን9 ነዋሪዎች እና በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት ተከብሮ ማየት ለምትፈልጉ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ጉዳዩ ላይ ያላችሁን አመለካከት፣ መብቱ የተጣሰባቸውን ክስተቶች በማካፈል በጉዳዩ ላይ በመወያየት እንዲሁም የፕሮፋይል ፎቷችሁን በመቀየር በዞን9 ጦማር እና በ‹ዞን9› እና ‹ሕገ-መንግሥቱ ይከበር› የፌስቡክ ገጾች የዘመቻው ንቁ ተሳታፊ እንድትሆኑ በትህትና እንጋብዛለን፡፡

ስለሚያገባን እንጦምራለን!!!
ዞን9